የአድቬንቲስት ቤት
ምዕራፍ ሃምሳ—ስድስት ፍች
ትዳር የዕድሜ ልክ ውል ነው፦ በወጣትነት አስተሳሰብ ትዳር በፍቅር ልብስ የተጀቦነ በመሆኑ ምናብ ከሸፈነው ከዚህ ዋነኛ ጠባዩ ነጥሎ የጋብቻ ቃል-ኪዳን ይዟቸው የሚመጣውን ከባድ ኃላፊነቶች አዕምሮ እንዲገነዘብ ማድረግ አስቸጋሪ ነው። ይህ ቃልኪዳን ሞት ብቻ ሊበጥ ሰው በሚችል ሰንሰለት ሁለቱን ያጣምራቸዋል። 1 AHAmh 245.1
የጋብቻ ጥምረት በጥንቃቄ ሊጤን የሚገባው ነው፤ ትዳር ለዕድሜ ልክ የሚጓዙት መንገድ ነውና። በኑሮ ውጣውረድ ውስጥ ሲያልፉ በሕይወት እስካሉ ድረስ እርስ በእርሳቸው መጣበቅ የሚችሉ መሆናቸውን ሴትዋና ወንዱ ሁለቱም በጥንቃቄ መመርመር አለባቸው። 2 AHAmh 245.2
የጋብቻን የተሳሳተ አመለካከት ክርስቶስ አስተካክሎታል፦ በአይሁድ ዘንድ ባል እዚህ ግባ የማይባል ጥፋት የሠራችን ሚስት ለመፍታት ይፈቀድለት የነበረ ሲሆን ሴቲቱም ሌላ ለማግባት ነፃ ትሆን ነበረች። ይህ ተግባር ለታላቅ ውድቀትና ኃጢአት ዳርጓቸዋል። የሱስ በተራራ ላይ ባደረገው ስብከት ለጋብቻው ቃል-ኪዳን ታማኝነት ከማጉደል ጥፋት በቀር ትዳርን ሊያፈርሰው የሚችል ነገር እንደሌለ በግልጽ አስቀምጦታል። እላችኋለሁ “ሚስቱን የፈታ ሁሉ ያለዝሙት ምክንያት እርሱ አመንዝራ አደረጋት የፈታችውንም ያገባ አመነዘረ።” AHAmh 245.3
በፍጥረት ጊዜ ተቀድሶ ስለተቋቋመው ጋብቻ አመላከታቸው:- “ሙሴ ስለ ልባችሁ ደንዳናነት ምሽቶቻችሁን ትፈቱ ዘንድ አዘዛችሁ” አላቸው “ጥንት ግን እንዲህ አልነበረም።” እግዚአብሔር ሁሉን ነገር “እጅግ መልካም” እንደሆነ ያወጀባቸውን የተቀደሱትን የኤደን ቀናት ለሕዝቡ አስታወሳቸው። ለሰው ጥቅም ለእግዚአብሔር ክብር ተብለው የተመሠረቱት ሁለቱ ተቋማት ጋብቻና ሰንበት መነሻቸው ያኔ ነበር። ከዚያም ፈጣሪ የሁለቱን ቅዱሳት እጆች በጋብቻ ሲያጣምር ሰው “እናት አባቱን ይተዋል በምሽቱም ይጣበቃል ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ” በማለት የጋብቻን ሕግ ለአዳም ልጆችና እስከ ዘመኑ መጨረሻ ላሉ ሁሉ ተናገረ። ዘለዓለማዊው አባት ራሱ መልካም ብሎ ያወጀው እጅግ የከበረው የበረከት ሕግ ሲሆን ለሰው እድገት አስቦ አቋቋመው። 3 AHAmh 245.4
ስህተቶችን ሊያስተካክል የእግዚአብሔርን የግብረ-ገብነት ምሣሌ በሰው ዘንድ ሊያድስ ክርስቶስ ወደ ዓለማችን መጣ። በጋብቻ ዙሪያ ያለው የተሳሳተ አመለካከት በእስራኤል መምህራን ዘንድ ቦታ አግኝቶ ነበር። የተቀደሰውን የጋብቻ ተቋም ተግባራዊ አላደረጉትም ነበር። ሰው ልቡ እጅግ እየደነደነ ሄዶ ከቁጥር የማይገባ ጥፋትዋን እንደ በቂ ምክንያት በመቁጠር ከሚስቱ ይለይ ነበር። ሲፈልግም ከልጆችዋ ለይቶ ይሰድዳት ነበር። ይህ እንደ ታላቅ ውርደት የሚቆጠርና ለተጠላችው ሴት አሰቃቂ መከራን የሚያመጣ ነበር። AHAmh 245.5
ክርስቶስ ይህንን ክፋት ሊያስተካክል መጣ፤ የመጀመሪያው ታምሩን በጋብቻ ሥነሥርዓት ላይ ፈጸመ። ሳይበከል በንጽህና ከተጠበቀ ጋብቻ የተቀደሰ ተቋም እንደሆነ ለዓለም አስታወቀ። 4 AHAmh 246.1
ምክር ለመፋታት እያቅማሙ ላሉ፦ ስለ ጋብቻ ግንኙነት ያለሽ/ህ አስተሳሰብ የተሳሳተ ነው። ከራሱ ከጋብቻው መሠረት በቀር የጋብቻ ቃል-ኪዳንን ሊሰብር ወይም ሊሽር የሚችል ነገር የለም። አደገኛ በሆኑ ጊዜያት ነው የምንኖረው፤ ምንም ነገር አስተማ ማኝ ባልሆነበት በዚህ ወቅት በጥብቅና በማያወላውል የየሱስ ክርስቶስ እምነት ጽኑ። በፀሎት የማትተጋ ከሆነ በሰይጣን መሣሪያ ከእግዚአብሔር ልትለይ የማትችል ነፍስ የለችም። AHAmh 246.2
አዕምሮአችሁ ቢያርፍና ሠላም ቢኖረው ጤናችሁ እጅግ በተሻለ ሁኔታ ይገኝ ነበር፤ ሆኖም ግራ የተጋባና ሚዛን ያጣ ሆኗል፤ ስለ ፍች ጉዳይ የሰጠኸው/ሽው ምክንያት ትክክል አይደለም። ሰዎች የእግዚአብሔርን ሕግ ወደ ጎን ትተው የራሳቸውን ዝንባሌ ሊከተሉና ለራሳቸው የሕግ ደረጃ ሊቀርጹ ነፃነት አልተሰጣቸውም። የእግዚአብሔር ጽድቅ ወደሚጠይቀው የግብረ-ገብነት ደረጃ መምጣት ያስፈልጋቸዋል…. ሚስት ባልዋን እንድትተው፤ ባልም ሚስቱን እንዲፈታ እግዚአብሔር የሰጠው አንድ ምክንያት ብቻ ነበር እርሱም ምንዝር ነው። ይህ የጋብቻ መሠረት የሆነው መርህ ከፀሎት ጋር በአንክሮ ሊታሰብበት ይገባል። 5 AHAmh 246.3
ምክር ለተለያዩ ጥንዶች፦ ወንድሜና እህቴ ሆይ ለተወሰነ ጊዜ ተለያይታችሁ ኖራችኋል። ይህን መንገድ መከተል አልነበረባችሁም፤ የፈጸማችሁት በባልና በሚስት መካከል መኖር ያለበትን ታጋሽነት፣ ቸርነትና ይቅር-ባይነት በሚገባ ስላላዳበራችሁት ነው። ሁለታችሁም የየራሳችሁን ፈቃድ በመገንባት ለሚመጣው መዘዝ ሳትጨነቁ የየግል ሐሳባችሁንና እቅዳችሁን ለመተግበር አትነሡ። ሁለታችሁም እንደፈለጋችሁ የማድረግ ቁርጠኛነታችሁን ተዉ። የሚያለሰልሰውና የሚያሸንፈው የእግዚአብሔር መንፈስ በልባችሁ ሠርቶ ልጆቻችሁን ለማሠልጠን ላለባችሁ ሥራ ገጣሚ ያድርጋችሁ…. ሚስት ለባልዋ፣ ባል ደግሞ ለሚስቱ እርስ በርሳችሁ ትዕግሥት ላጣ ሸካራና ችኮ አነጋገር እጅ እንዳትሰጡ እንዲረዳችሁ የሰማይ አባታችሁን ተማፀኑት። የሁለታችሁም ባህርይ ጎደሎ አለበት። በእግዚአብሔር ቁጥጥር ሥር ስላልነበራችሁ ለእርስ በእርሳችሁ የምታንፀባርቁት ባህርይ ጥበብ የጎደለ ው ነበር። AHAmh 246.4
እራሳችሁን በእግዚአብሔር ቁጥጥር ሥር እንድታደርጉ እለምናችኋለሁ። በሚያስቆጣ አነጋገር እንድትናገሩ ሲገዳደራችሁ ትንፍሽ አትበሉ። በዚህ ነገር ትፈተናላችሁ፤ ምክንያቱም ልትቃወሙት የሚገባችሁን ባህርይ አሸንፋችሁት ስለማታውቁ ነው። ሆኖም እያንዳንዱ የተሳሳተ ልማድ መሸነፍ አለበት። ሙሉ ለሙሉ እጆቻችሁን ለእግዚአብሔር ስጡ። በቋጥኙ በየሱስ ክርስቶስ ላይ ወድቃችሁ ተለወጡ። እንደ ባልና ሚስት እራሳችሁን ሥነ-ሥርዓት አስይዙት፤ ለእርዳታ ወደ ክርስቶስ ሂዱ፤ መለኮታዊ ርኅራኄውንና ነፃ ፀጋውን በደስታ ያቀርብላችኋል…. AHAmh 246.5
ላለፈው መንገዳችሁ እግዚአብሔርን ይቅርታ ጠይቁት፤ ወደ መስማማት ኑና እንደ ባልና ሚስትነታችሁ እንደገና አንድ ላይ ሁኑ። ያልተስማማችሁባቸውን ደስታ-ቢስ የሆናችሁባቸውን ያለፉ የሕይወት ልምዶቻችሁን ተዋቸው። በጌታ የበረታችሁ ሁኑ። ወደ ምድር የተከፈተውን የነፍስ በር ዘግታችሁ ወደ ሰማይ ክፈቱት። ፀሎታችሁ ወደ ሰማይ ወጥቶ ጮራ እንዲፈነጥቅላችሁ ብትጠይቁ ብርሃንና ሕይወት፣ ሠላምና ደስታ የሆነው ጌታ የሱስ ለቅሶአችሁን ይሰማል። የጽድቅ ፀሐይ የሆነው እርሱ በአእምሮአቸሁ ጓዳ ያንፀባርቃል፤ የነፍሳችሁ መቅደስ በብርሃን ይሞላል። የመገኘቱን የፀሐይ ብርሃን በደስታ ብትቀበሉት ደስታ-ቢስ ስሜትን የሚፈጥር ንግግር ከአፋችሁ አይወጣም። 6 AHAmh 247.1
ተስፋ አስቆራጭ በሆነ ሁኔታ ለተበደለች ሚስት፦ ደብዳቤሽ ደርሶኛል፤ መልሴም ቁርጠኛ ለውጥ እስካላየሽበት ድረስ ወደ ዲ(D) እንድትመለሺ አልመክርሽም የሚል ነው። ለሚስት ይሆንላት ዘንድ የሚገባትን የሚያንፀባርቁ አይደሉምና ከአሁን በፊት ባሉት ሐሳቦቹ እግዚአብሔር አልተደሰተባቸውም…. [እርሱ] ባለፈው አቋሙ ከፀና የወደፊቱ ካለፈው የተሻለ አይሆንልሽም። ሚስት እንዴት መያዝ እንዳለባት አያውቅም፤ ይህ ጉዳይ አሳዝኖኛል። ለዲ(D)ም በእውነት አዝንለታለሁ፤ የራስሽን ውሳኔ በተቃረነ መልኩ ግን ወደርሱ ሂጂ ብዬ ልመክርሽ አልችልም። እርሱን ባነጋገርሁበት ቅንነት ነው አንችንም የማናግርሽ፤ በእርሱ እዝ ሥር እንደገና ራስሽን ማስቀመጥ ለአንቺ አደገኛ ነው። ይለወጣል ብዬ ተስፋ አድርጌ ነበር…. AHAmh 247.2
እግዚአብሔር ያለፍሽባቸውን ገጠመኞች ሁሉ ይረዳል…. በጌታ የበረታሽ ሁኚ እርሱ አይተውሽም፤ አይጥልሽምም። ጥልቅ የሆነ ልባዊ ርኅራኄ ለአንቺ ይሰማኛል። 7 AHAmh 247.3
ለተተወ ባል - “መስቀልህን ተሸከም”፦ ከዚህ የተሻለ ምን ሊሠራ እንደሚችል የሚታየኝ ነገር የለም፤ ያለህ ብቸኛ አማራጭ ሚስትህን መተው ይመስለኛል። ከአንተ ጋር ላለመኖር ከወሰነች፣ አብራችሁ እንድትሆኑ ብቻህን ብትጥር ሁለታችሁም የሰቆቃ ኑሮ ውስጥ ትሆናላችሁ። እርስዋ በአቋምዋ ሙሉ በሙሉ እንደ ፀናችና ድርሻዋን እንደ ወሰነች ሁሉ ያለህ አማራጭ መስቀልህን በመሸከም ወንድነትህን [ጥንካሬህን] ማሳየት ነው። 8 AHAmh 247.4
ቢፋቱም በእግዚአብሔር እይታ እንደተጋቡ ላሉ፦ አንዲት ሴት በአገሩ ሕግ መሠረት በሕጋዊ ፍች ከባልዋ ጋር ተፋትታ ይሆናል፤ ሆኖም እንደ እግዚአብሔር ዕይታና እንደ ከፍተኛው የሰማይ ሕግ አልተፋታችም። በእግዚአብሔር ዕይታ ሚስትን ወይም ባልን ከገባችው/ከገባው የጋብቻ ቃል ኪዳን ነፃ የሚያደርጋት/ገው ያው አንድ ኃጢአት - ምንዝር ብቻ ነው። የምድር ሕግ ፍች ለግሷቸው ቢሆንም እንኳ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ እውነትና እንደ እግዚአብሔር ሕግ ግን ሁለቱ አሁንም ተጋብተው ያሉ ባልና ሚስት ናቸው። AHAmh 248.1
አይቻለሁ--ያቺ እህት ሌላ ወንድ ለማግባት ገና መብት የላትም፤ ሆኖም እርስዋ ወይም ሌላ ማንኛዋም ሴት በባልዋ አመንዝራነት ምክንያት ሕጋዊ ፍች አድርጋ ከሆነ የመረጠችውን የማግባት ነፃነት አላት። 9 AHAmh 248.2
ከማያምን አጋር መለያየት፦ ባል ያገባች የማታምንና ተቃዋሚ ብትሆን በእግዚአብሔር ሕግ መሠረት በዚህ ጉዳይ ብቻ ተመርኩዞ ሚስቱን መፍታት አይችልም። ከይሖዋ ሕግ ጋር ለመስማማት ከፈለገ በራስዋ ፍላጎት ልትለቀው ካልፈለገች በስተቀር ሊለያት አይችልም። በተቃውሞዋ ሊሰቃይ፣ ሊጨቆንና በብዙ ነገር ሊበሳጭ ይችላል፤ ሆኖም ይህ አስቸጋሪሁኔታ በተፈጠረ ጊዜ የሚበጀውን ኃይል መፅናናትና እርዳታ ፀጋን ከሚለግሰው ከእግዚአብሔር ዘንድ ያገኛል። ንፁህ ጭንቅላት ቁርጠኝነትና ጠንካራ መርህ ያለው ሰው ይሁን፤ የትኛውን መንገድ መከተል እንዳለበት ያውቅ ዘንድ ጥበብ ይሰጠዋል፤ ፍላጎቱ ማገናዘቡን አይቆጣጠረውም። ጠንካራ ስሜቱ አገናዛቢነቱን አይቆጣጠረውም፤ እንዲያውም አመዛዛኝነቱ የፍላጎቱን ልጓም በጠንካራው እጅ ይዞ የሥጋ ስሜቱ ከቅንጣት ሳይበልጥ ጭጭ እንዲል ማድረግ ይቻለዋል። 10 AHAmh 248.3
የጋብቻ ሁኔታዋን ሳይሆን ጠባይዋን እንድትለውጥ የምትበረታታ ሚስት፦ ከባለቤትሽ ደብዳቤ ደርሶኛል። ልለው የምችለው ነገር ቢኖር ባልም ከሚስቱ ሚስትም ከባልዋ በሕጋዊ መንገድ ሊለያዩ የሚችሉበት ምክንያት አንድ ነው፤ እርሱም ምንዝር ነው። AHAmh 248.4
ግብርሽ የማይወደድ ከሆነ ለእግዚአብሔር ክብር ስትይ እነዚህን ባህርያት አትለውጫቸውምን? AHAmh 248.5
ባልና ሚስት አክብሮትና ፍቅር ለእርስ በርሳቸው ማጎልበት አለባቸው። የሚያናድድ ወይም የሚያስቆጣ ምንም ዓይነት ነገር እንዳይባል መንፈሳቸውን፣ ንግግራቸውንና ሥራቸውን በጥንቃቄ መጠበቅ ይገባቸዋል። አንዱ ለሌላው ጥንቃቄ ያድርግ፤ ያላቸውን ኃይል ሁሉ ተጠቅመው የጋራ ፍቅራቸውን ያጠናክሩ። AHAmh 248.6
ሁለታችሁም እግዚአብሔርን እንድትፈልጉት እመክራችኋለሁ። በፍቅርና በቸርነት ለእርስ በርሳችሁ ያለባችሁን ኃላፊነት ተወጡ። ቤተሰቡን በመርዳትና የተቻለውን ሁሉ በማድረግ ባል የታታሪነት ልምድ ማዳበር አለበት፤ ይህም ባለቤቱ ለእርሱ ክብር ያላት እንድትሆን ያደርጋታል…. AHAmh 248.7
እህቴ ሆይ አሁን ያለሽን ጠባይ ይዘሽ እግዚአብሔርን ደስ ልታሰኝ አትችይም። ለባለቤትሽ ይቅርታ አድርጊለት። እርሱ ባለቤትሽ ነው፤ አፍቃሪና ቁም ነገረኛ ሚስት ለመሆን በምታደርጊው ጥረት ትባረኪያለሽ። የቸርነት ሕግ በከንፈርሽ ላይ ይሁን፤ ጠባይሽን መለወጥ ትችያለሽ፤ የግድ መለወጥ አለብሽ። 11 AHAmh 249.1
ከመለያየት ይልቅ እንዴት እንደምትመሳሰሉ ማጥናት አለባችሁ.… መጠነኛና ለስለስ ያሉ ዘዴዎችን ብትጠቀሙ በሕይወታችሁ የሚያስገርም ለውጥ ይመጣል። 12 AHAmh 249.2
ዝሙት ፍችና የቤተ-ክርስቲያን አባልነት፦ በተጎዳችው እህት በኤ.ጂ (A.G) ጉዳይ ላይ ለጥያቄዎቹ መልስ ስንሰጥ የምንለው፡- በኃጢአት የተሸነፉ አብዛኛዎቹ የሚያደርጉት ዓይነት ነው፤ ልክ ባልዋ እንዳደረገው የጥፋታቸውን መጠን በውል አይገነዘቡትም። ወደ ቤተ-ክርስቲያን እንዲመለሱ ይፈቀድላቸዋል፤ የሚፈቀድላቸው ግን ባልተዘረዘረ ኑዛዜ የእግዚአብሔርን ሕዝቦች አመኔታ ሲያተርፉና ልባዊ የሆነ የፀፀት ጊዜ ሲወስዱ ነው። ይህ ጉዳይ በአንዳንዶች የሚከሰት ችግር ሊሆን ይችላል፤ ስለሆነም የሚከተሉትን ብቻ ጨምረናቸዋል። AHAmh 249.3
1. ሰባተኛው ትዕዛዝ ሲጣስና የተላለፈው ወገን እውነተኛ ፀፀት ካላሳየ፣ በመፋታታቸው ምክንያት የተጎዳው ወገንና የልጆቻቸው ሁኔታ የሚባባስ ካልሆነ መለያየትና ነፃ መሆን ይሻላቸዋል። AHAmh 249.4
2. በመፋታታቸው ምክንያት ራሳቸውንና ልጆቻቸውን የባሰ ሁኔታ የሚጥሉ ከሆነ ያልበደለውና ያልተፋታው ወገን ሳይለያይ በመቅረቱ ምክንያት ጥፋተኛ የሚያደርገው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል አናውቅም። AHAmh 249.5
3. ጊዜ፣ ጥረት፣ ፀሎት፣ ትዕግሥት፣ እምነትና እግዚአብሔር የሚፈልገው ሕይወት መኖር መታደስን ሊያመጣ ይችላል። የጋብቻ ቃል-ኪዳን ካፈረሰው የኩነኔ ፍቅር ውርደትና ሐፍረት ሙሉ በሙሉ ከሸፈነው ይባስ ብሎ ደግሞ ስህተቱን ከማያስተውለው ሰው ጋር አብሮ መኖር ቀስ በቀስ እየበላና እያሰለሰለ ነፍስን እንደሚጨርስ በሽታ (ተቀጥላ) ነው፤ ይህም ሆኖ ፍች የዕድሜ ልክ ልባዊ ቁስል ነው። ላልበደለው ወገን እግዚአብሔር ይዘንለት! ጋብቻ ከመፈጸሙ በፊት በአፅንኦት ሊመረመር ይገባዋል። AHAmh 249.6
4. ኦ! ለምን? ኧረ ለምን? ክቡርና መልካም የሚሆኑ በመጨረሻም ሰማይ የሚደርሱ ሴቶችና ወንዶች፣ ለምን እራሳቸውን በማይረባ ዋጋ፣ በርካሽ ለሰይጣን ይሸጣሉ? ለምን የልብ ወዳጆቻቸውን ያቆስላሉ? ለምን በቤተሰባቸው ላይ ሐፍረትን ያመጣሉ? ለምን በተጋድሎው ላይ ውርደትን አትርፈው በመጨረሻ ወደ ሲኦል ይወርዳሉ? እግዚአብሔር ሆይ ማረን! ለምን እነዚህ የተሸነፉ ሰዎች ወደ ክርስቶስ በመብረር የጥፋታቸውን አሰቃቂነት በሚተካከል ፍጹም ፀፀት ንስሐ ገብተው፤ ምህረት ከእርሱ ጠይቀው፤ በሚቻላቸው መጠን ያመረቀዙትን ቁስል አይፈውሱም? 13 AHAmh 249.7
5. ዳሩ ግን እንደዚያ የሚያደርጉ ከሆነና ተበዳዩ ያለውን የመፍታት ሕጋዊ መብት በመተው ኃጢአቱ ከታወቀ በኋላ እንኳን ከበዳዩ ጋር ለመኖር ከፈቀደ ጥፋተኛ ያልሆነው ወገን ባለመፋታቱ ኩነኔ ሊያርፍበት አይችልም፤ ባለ መፋታትዋ ምክንያት በጤናዋና በሕይወትዋ ከፍተኛ ጉዳት የማይደርስ ቢሆንም እንኳ እርሱን ባለመልቀቋ የግብረ-ገብነት መብትዋ ጥያቄ ውስጥ የሚገባ ይመስላል።* 13 AHAmh 250.1