የአድቬንቲስት ቤት
የአድቬንቲስት ቤት
መቅድም
የአድቬንቲስት ቤት፣ የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት [ቤ/ክ] ስነ-ሥርዓትና ምግባር የሚተገበርበትና ትምህርት የሚሰጥበት፤ እንዲሁም የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት አባቶችና እናቶች የቤተሰባቸውን አባላት ክርስቲያን እንዲያደርጉ ክርስቶስ የወከለበት ቦታ ነው። ይህንንም ሥራ በአግባቡ ለመፈፀም የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ወላጆች ማግኘት የሚችሉትን እርዳታ ሁሉ በመፈለግ ላይ ናቸው። AHAmh .0
ኤለን ጂ. ኋይት እጅግ ጠቃሚ የሆኑ ብዙ ምክሮችን ለወላጆች ጽፋለች። እያንዳንዱን የትዳር ምዕራፍም በመዳሰስ በአሁኑ ጊዜ አሳቢና ተጨናቂ ለሆኑ ወላጆች፤ ለሚያሳስቧቸው ብዙ ችግሮቻቸው ልዩ የሆኑ መመሪያዎች ሰጥታለች። ከመሞትዋ ጥቂት ዓመታት ቀደም ብሎ እናት በልጆችዋ ላይ ያላትን ኃላፊነትና ተጽዕኖ የሚያስረዳ “መጽሐፍ ለክርስቲያን ወላጆች” የሚል መጽሐፍ ማሳተም እንደምትፈልግ ጠቁማ ነበር። ይህንንም ተስፋ ለመፈጸም በዚህ ሥራ ጥረት ተደርጓል። AHAmh .0
ይህ የምቱ ተጠባባቂዎች ቤት በሚል ርዕስ የታተመው መጽሐፍ ሥራ ለሚበዛባቸው ወላጆች እንደ መመሪያ የእጅ መጽሐፍ ወይም ማኑዋል የሚሆን፤ ትዳር ምን መሆን እንደሚችልና ምን ዓይነት መሆንም እንዳለበት የሚያሳይ ንድፍ ወይም ተምሣሌት ነው። ለብዙ ጥያቄዎቻችሁ መልስ ከሰማይ አባት የሆኑ የጥበብ ቃላት እነሆ። AHAmh .0
ይህ መጽሐፍ የተዘጋጀው ኤለን.ጂ.ኋይት ለሰባት አስርተ ዓመታት ከጻፈቻቸው በተለይም ለኃይማኖት ድርጅቱ ከተዘጋጁት መጽሔቶች (ማስታወሻዎች) የተወሰዱ በብዙ ሺህ ከሚቆጠሩ ጽሑፎችዋ (articles) ነው። ለእያንዳንዱ ምዕራፍ ተአማኒ የሆነ ምንጭ ተሰጥቷል። ጽሑፎቹ የተካተቱት በተለያዩ ጊዜያት ከተጻፉ የተለያዩ ምንጮች ተውጣጥተው ቅደም ተከተላቸውን እንዲጠብቁ ጥረት ተደርጎ ከመሆኑ የተነሣ አልፎ አልፎ ለማስተካከል የሚያስቸግር የሐሳብ ወይም የአገላለጽ መቆራረጥ ሊኖር ይችላል። ይህም አዘጋጆቹ ትምህርቶቹን ከመምረጥና ከማደራጀት፣ ርዕሶችን ከመስጠት በተያያዘ ካለባቸው ግድድሮሽ የተነሣ ነው። AHAmh .0
ይህ መጽሐፍ የተዘጋጀው በኤለን.ጂ. ኋይት ህትመት (Ellen G. White Publications) ቢሮ ነው። ለጽሑፍ ክምችቶችዋ ማሳተሚያ ከእጅ ጽሑፎችዋ ተወስዶ እንዲቀርብ ኤለን ጂ. ኋይት ለባለአደራዎችዋ ከሰጠችው ትዕዛዝ ጋር እንዲጣጣም ተደርጎ የተዘጋጀ ሥራ ነው። ጽሑፎችዋ “ጌታ ለሕዝቦቹ የሰጠኝን ትዕዛዛት (መመሪያዎች) የያዙ” ናቸው በማለት እራስዋ እንደተናገረችው ሆነው ቀርበዋል። AHAmh .0
እንደዚህ ዓይነት መጽሐፍ በዓለም ታሪክ ውስጥ እንደ አሁኑ ዘመን እጅግ አስፈላጊ የሆነበት ጊዜ የለም። ወላጆችና ልጆች ለሚያስጨንቋቸው ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት የጓጉበት እንደዚህ ያለ ጊዜም አልነበረም። ቤተሰብ እንደ አሁኑ ጊዜ ለአደጋ የተጋለጠበት ዘመንም አልነበረም። AHAmh .0
ሁላችንም እንደምናውቀው በማህበረሰቡ ውስጥ ያለው ገጽታ በየቤቱ ውስጥ ያለው ሁናቴ ነፀብራቅ ነው። በቤት ውስጥ የሚደረግ ለውጥም በማህበረሰቡ ውስጥ ተደግሞ እንደሚታይ እናውቃለን። ለዚህም ዓላማ ይህ መጽሐፍ - ለምፅአቱ ተጠባባቂዎች ቤት - ተዘጋጅቷል። የክርስቲያኖች ቤተ-መጻህፍት (Christian Home Library) አካል ሆኖ አስፈላጊውን ሚሲዮናዊ ሥራ እንዲሠራ ተልኳል። AHAmh .0
የተላከውም በአሳታሚዎችና በኤለን ጂ. ኋይት ጽሑፎች አደራ ጠባቂዎች AHAmh .0
(THE TRUSTEES OF THE ELLEN G. WHITE PUBLICATIONS) ነው።
ዋሽንግተን ዲ.ሲ.
ግንቦት 8/1952 እ.ኤ.አ.