አእምሮ፣ባሕርይና ማንነት፣ክፍል 1
ምዕራፍ 3—በስነ-ልቦና ትምህርት ውስጥ ያሉ አደጋዎች
ሰይጣን የአእምሮ ተማሪ።--ሰይጣን ለብዙ ሺህ አመታት በሰብአዊ አእምሮ ባሕርያት ላይ ሙከራ ሲያደርግ ስለኖረ እንዴት እንደሚያውቀው ተምሯል። በእነዚህ የመጨረሻ ቀናት ውስጥ ብልጠት ባለበት ስራው ሰብአዊ አእምሮን በራሱ ሀሳቦች በመሙላት ከራሱ አእምሮ ጋር እያገናኘ ነው፤ ይህን ሥራ እየሰራ ያለው እጅግ አታላይ በሆነ ሁኔታ ስለሆነ የእርሱን ምሪት የሚቀበሉ ሰዎች እርሱ በፈቃዱ እየመራቸው እንደሆነ አያውቁም። ታላቁ አታላይ ከእርሱ ድምጽ በቀር የማንም ድምጽ እንዳይሰማ የወንዶችንና የሴቶችን አእምሮ ለማደናገር ተስፋ ያደርጋል።--Lt 244, 1907. (MM 111.) {1MCP 18.1} 1MCPAmh 17.1
ሰይጣን የብልጠት ተግባራት መምህር ነው። ሰይጣን በብልጠት ተግባራቱ አማካይነት ሰብአዊ አእምሮዎች ላይ ተጽእኖ ለማሳደር ያለማቋረጥ እየሰራ ነው። ከእግዚአብሔር የተሰጠው ነገሮችን የሚያቀነባብር አእምሮ አለው፣ ነገር ግን የልዑልን ምክሮች ለመቃወምና ዋጋ ቢስ ለማድረግ እነዚህን የከበሩ ችሎታዎቹን አረከሳቸው። --ST, Sept. 18, 1893. (HC 210.) {1MCP 18.2} 1MCPAmh 17.2
እርሱ በድብቅ ይመጣል።--የሰይጣን እቅዶችና ዘዴዎች በሁሉም አቅጣጫ እያባበሉን ናቸው። እርሱ ወደ እኛ የሚመጣው ድርጊቱን የሚፈጽምበትን ምክንያትና የፈተናዎቹን ባሕርይ በመደበቅ በስውር መሆኑን ሁል ጊዜ ማስታወስ አለብን። እርሱ ወደ እኛ የሚመጠው ማንነቱን ለይተን እንዳናውቅ ንጹህ የሆነ የመልአክ ልብስ ለብሶ በብርሃን ልብስ ነው። እንዳንታለል የእርሱን ዘዴዎች በደንብ መመርመር እንድንችል በጣም መጠንቀቅ አለብን። --MS 34, 1897. (HC 88.) {1MCP 18.3} 1MCPAmh 17.3
ከአእምሮ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ሳይንሶች ያለ አግባብ መጠቀም።-- ጥራዝ ነጠቅነትና ክህደት በሳይንሳዊ ልብስ ተሸፍነው በሚቀርቡባቸው በእነዚህ ቀናት በሁሉም አቅጣጫ ከማታለያ መጠበቅ አለብን። በዚህ መንገድ ትልቁ ጠላታችን በሺሆች የሚቆጠሩትን እያሳሳተ እንደ ፈቃዱ እየመራቸው ነው። የሰብአዊ አእምሮ ሳይንሶችን በተመለከተ ከሳይንሶች እያገኘ ያለው ጥቅም እጅግ ብዙ ነው። በዚህ ቦታ፣ በእባብ ተመስሎ፣ የእግዚአብሔርን ሥራ ለማበላሸት ቀስ ብሎ ይገባል። {1MCP 19.1} 1MCPAmh 17.4
ይህ የሰይጣን በሳይንሶች አማካይነት መግባት በደንብ የተሰላ ነው። የአእምሮ ቅርጽንና መጠንን በሚያጠና ሳይንስ፣ በስነ-ልቦና ሳይንስና ሰውን በሰመመን ውስጥ የማስገባት ሳይንሶች አማካይነት [ሰይጣን ሰብአዊ አእምሮን ለመያዝ የአእምሮ መጠንና ቅርጽ የሚያጠና ሳይንስን፣ የስነ-ልቦና ሳይንስን እና በሰመመን ውስጥ የማስገባት ሳይንስን እንደ መልካም አጋጣሚዎች እንደሚጠቀም መጥቀስ የወቅቱን ሥነ-ጽሁፍና ትኩረቱን ለማያውቅ ሰው ግልጽ ያልሆነ ነገር ይመስላል። ለስነ-ልቦና ትምህርት እና ለህመምተኞች ጥንቃቄ ስለማድረግ የተለዩ ሳይንሳዊ ሥራዎች ለሕዝብ ያለውን ስነ-ጽሁፍ በመንገርና በማስተዋወቅ ከኋላ በመሆን ሥራን እየሰሩ ናቸው። በእነ ፈውለርስ እና በእነ ዌልስ በ1850 ዓ.ም የታተመው የውኃ ፈውስ መመሪያ የሚል የዚህ ዓይነት አንድ ሥራ (284 ገጾች ያሉት) የአካልና የአእምሮ ጤናን የሚመለከቱ ስልሳ አምስት የተለያዩ አይነት ሥራዎችን ዝርዝር የያዘ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ ሃያ ሶስቶቹ ለአእምሮ መጠንና ቅርጽ ጥናት፣ ለስነ-ልቦና ትምህርት፣ ሰውን በሰመመን ውስጥ ስለማስገባትና ከተራ ስሜት ወጥቶ የወደፊቱን ማወቅን ለመሳሰሉ ነገሮች ተሰጥተው ነበር። እዚህ ላይ ጥቂት ነገሮችን መልሰን አዘጋጅተናል፡- 12.5 ዶላር ዋጋ የሚያወጣ የእንስሳ መሳሳብ (ማግኔታዊነት) ባሕርያት፤ ወይም ሰብአዊ ስቃይን ለማስታገስ የሚረዱ ሂደቶችና ተግባራዊ ሥራ የሚል ጽሁፍ፣ በጥሩ ሁኔታ መግለጫ የተሰጠው በአእምሮ ቅርጽና መጠን እና በስነ-ልቦና ላይ የቀረቡ እውቅ ትምህርቶች አንድ ቅጽ። የህይወት መርሆዎችን የሚገልጽ መግለጫ ያለው ሁለት ዶላር ዋጋ ያለው፣ የማስደነቅ፤ ወይም የማስደሰት (ማግኔታዊነት) ፍልስፍና። 40 ዶላር ዋጋ ያለው፤ በሰመመን ውስጥ ስለማስገባትና ከተፈጥሮአዊ ስሜት ወጥቶ የወደፊቱን ማወቅን በተመለከተ የቀረቡ ትምህርቶች። ሂደቶቹንና ተግባራዊ አሰራሩን በተመለከተ መመሪያ ያለው ሃያ አምስት ዶላር የሚያወጣ፣ ሳይኮሎጂ ወይም የነፍስ ሳይንስ። የተቀረጸ የነርቭ ሥርዓትን የሚያሳይ። በጆሴፍ ሃዶክ የተዘጋጀ ሃያ አምስት ዶላር የሚያወጣ፣ የአእምሮ መጠንና ቅርጽ ጥናት እና ቅዱሳት መጻሕፍት (ያላቸውን ስምምነት የሚያሳይ)። በክቡር ጆን ፒርፖንት የተዘጋጀ 12.5 ዶላር ዋጋ ያለው የኤሌክትሪካዊ ሳይኮሎጂ ፍልስፍና። በጆን ቦቪ ዶድስ የተዘጋጀ አምሳ ዶላር የሚያወጣ፣ ዶክተር ሲልቬስተር ግራሃም በ1865 ዓ.ም. የሰው ሕይወት ሳይንስን ‹‹ከደራሲው የሕይወት ታሪክ›› ጋር ባቀረባቸው 650 ገጽ በሚሆኑ ትምህርታዊ መግለጫዎች ውስጥ ተመሳሳይ ከሆኑ ስራዎች መካከል ብዙዎች እንዲታወቁ ተደርገዋል፣ በዚህን ጊዜ እንዲታወቁ የተደረጉት ‹‹በጭንቅላት ውስጣዊ ቅርጽ ጥናት የተሰሩ ሥራዎች፣›› ‹‹የውኃ ሕክምና፤ ወይም የውኃ ፈውስ፣›› ‹‹ሰመመን ውስጥ የማስገባት የስነ-ልቦና ትምህርት፣›› ወዘተ.. በሚባሉ ርዕሶች ተመድበው ተቀምጠው ነበር፤ ይህ የቀረበው ወደ አንድ ሙሉ ገጽ የሚጠጋው ‹‹የጭንቅላት ውጫዊ ቅርጽ ጥናት መግለጫ›› ለሚለው ከተሰጠው ስምንት ገጽ ከሚሆን ‹‹የሲልቨስተር ግራሃም ሕይወት›› ጋር በተገናኘ ሁኔታ ነበር። ስለዚህ ኤለን ኋይት እየጻፈች የነበረችው በዚያን ጊዜ በሕዝብ ፊት እጅግ ይታወቁ በነበሩ ጉዳዮች ላይ ነበር።-- የጽሁፉ አሰባሳቢዎች።] እርሱ (ሰይጣን) በዚህ ትውልድ ወዳለው ሕዝብ በቀጥታ በመምጣት በአመክሮ ጊዜ መዝጊያ አካባቢ የሚኖሩ ጥረቶቹን በሚገልጽ ኃይል ይሰራል። ከዚህ የተነሣ በሺሆች የሚቆጠሩ ሰዎች አእምሮአቸው ተመርዞ ወደ እምነት የለሽነት ተመርተዋል። {1MCP 19.2} 1MCPAmh 17.5
የአንድ ሰው አእምሮ የሌላኛውን ሰው አእምሮ እንዲህ አስደናቂ በሆነ ሁኔታ እንደሚነካ የሚታመን ሲሆን እያንዳንዱን አጋጣሚ ለመጠቀም ዝግጁ የሆነው ሰይጣን ራሱን በማነሳሳት በግራና በቀኝ ይሰራል። ለእነዚህ ሳይንሶች ራሳቸውን የሰጡ ሰዎች በእነርሱ አማካይነት ተሰርተዋል በማለት ማረጋገጫ ከሚሰጡአቸው ታላላቅና ጥሩ ሥራዎች የተነሣ እስከ ሰማይ ድረስ ከፍ እያደረጉአቸው ሳለ እንዴት ያለ የክፉ ኃይልን እየተንከባከቡ መሆናቸውን አያውቁም፤ ነገር ግን በፍቅር እየተንከባከቡ ያሉት ኃይል በምልክቶችና በውሸት ተአምራቶች በኃጢአት ማታለል ሁሉ የሚሰራ ኃይል ነው። ውድ አንባቢ ሆይ፣ በክርስቶስና በሰይጣን መካከል ያለው ጦርነት ገና ስላላበቃ የእነዚህን ሳይንሶች ተጽእኖ ልብ በል። {1MCP 20.1} 1MCPAmh 19.1
ጸሎትን ችላ ማለት ሰዎች በራሳቸው ችሎታ እንዲደገፉ በመምራት ለፈተና በር ይከፍታል። በብዙ ሁኔታዎች ሀሳባቸው በሳይንሳዊ ምርምር ስለተያዘና ያሉአቸውን ኃይሎች ከማወቃቸው የተነሣ ይታለላሉ። ከሰው አእምሮ የሆነውን (የሚመነጨውን) ነገር የሚያጠኑ ሳይንሶች እጅግ በጣም ከፍ ከፍ ተደርገዋል። እነዚህ ሳይንሶች በቦታቸው ጥሩ ቢሆኑም ሰይጣን ነፍሳትን ለማታለልና ለማጥፋት እንደ ኃይለኛ መሳሪያዎቹ አድርጎ ይዞአቸዋል። ዘዴዎቹ ከሰማይ እንደሆኑ ተደርገው ስለተወሰዱ ለእርሱ የሚስማማውን አምልኮ ይቀበላል። ከጭንቅላት መጠንና ቅርጽ ጥናት እና ከእንስሳት መሳሳብ ብዙ ጥቅም ያገኛል ተብሎ የተገመተው ዓለም እንደ አሁን ተበላሽቶ አያውቅም። በእነዚህ ሳይንሶች አማካይነት መልካም ባሕርይ ተበላሽቶ መናፍስትን የመጥራት መሰረቶች ተጥለዋል። --ST, Nov 6, 1884. (2SM 351, 352.) {1MCP 20.2} 1MCPAmh 19.2
የሰውን አእምሮ ለመቀልበስ የእርሱ ሥራ።-- ሰይጣን በቀጥታ ጣልቃ በመግባት ራሱን በእግዚአብሔርና በሰው መካከል አስቀምጧል። የሰብአዊ አእምሮን መቀልበስ ሥራው ስለሆነ በእግዚአብሔር እና በግብረገብ ጨለማና ብልሽት እንዲሁም በዓለም ላይ ባለው ጅምላ በደል መካከል ያለውን ልዩነት ለይተን እንዳናውቅ በመንገዶቻችን ላይ ጥቁር ጥላውን ያጠላል። ስለዚህ ጉዳይ ምን ማድረግ ነው ያለብን? ጨለማው እንዲቀጥል እንፈቅድለታለን? አናደርገውም። {1MCP 21.1} 1MCPAmh 19.3
ወደ ጨለማው ዓለም የሰማይን ብርሐን የሚያመጣልን ኃይል እዚህ አለ። ክርስቶስ በሰማይ ስለነበር የሰማይን ብርሐን በማምጣት ጨለማውን ያባርርና የእርሱ ክብር የፀሐይ ብርሐን እንዲገባ ያደርጋል። ያኔ በብልሽት፣ በብክለትና በእርኩሰት መካከል የሰማይን ብርሐን እናያለን። {1MCP 21.2} 1MCPAmh 19.4
በሰብአዊ ዘር ውስጥ ባለው እርኩሰት ተስፋ መቁረጥም ሆነ ያን በአይነ ህሊናችን ማስቀመጥ የለብንም። ያን መመልከት የለብንም።…ታዲያ ምን ማድረግ አለብን? ሥራችን ምንድር ነው? የእኛ ሥራ ‹‹አብ እንዴት ያለ ፍቅር እንደሰጠን እዩ›› (1 ዮሐ. 3፡ 1) የሚለውን መተግበር ነው። --MS 7, 1888. {1MCP 21.3} 1MCPAmh 20.1
ብልጠት ያለበት ማታለልና ግልጽ የሆነ የድፍረት ጥቃት ሲነጻጸሩ።-- ሰይጣን በክርስትና ላይ ግልጽ የሆነ የድፍረት ጥቃት ቢከፍት ኖሮ ክርስቲያንን በአንዴ ጠላቱን ሊያባርርለት ከሚችለው ብርቱ ነጻ አውጪ እግር ሥር ያመጣው ነበር። በአጠቃላይ ሲታይ ይህን አያደርግም። ብልህ ስለሆነ እቅዶቹን ለመፈጸም እጅግ ውጤታማ የሆነው ዘዴ ምስኪን ወደ ሆነውና ወደ ወደቀው ሰው በብርሃን መልአክ ተመስሎ መምጣት እንደሆነ ያውቃል። በዚህ ሽፋን አደጋ ከሌለበትና ከትክክለኛው መንገድ ለማሳሳት በአእምሮ ላይ ይሰራል። የክርስቶስን ሥራ በማስመሰል የራሱን ኃይልና ፍላጎት ማጽናት የሁል ጊዜ ፍላጎቱ ነበር። ክርስቶስ የሰራቸውን ሥራዎችና ተአምራቶች ሳይንሳዊ መርሆዎችን ተከትሎ እንደሰራ አድርገው እንዲቀበሉ የተታለሉ ሟቾችን ይመራል፤ የሰብአዊ ጥበብና ኃይል ውጤቶች ተደርገው እንዲታዩ ያደርጋል። ከዚህ የተነሣ በመጨረሻ ከብዙ አእምሮዎች ክርስቶስ መሲህ፣ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ የተቀበሉበትን እውነተኛ እምነት ያጠፋል።--ST, Nov 6, 1884. {1MCP 21.4} 1MCPAmh 20.2
የእርሱ ልዩ ዓላማው ወጣት አእምሮዎችን መያዝ ነው።-- በእነዚህ የመጨረሻ ቀናት የወጣቶችን አእምሮዎች መቆጣጠር፣ ሀሳቦችን መበከል፣ እና በስሜቶቻቸው እንዲቃጠሉ ማድረግ የሰይጣን የተለየ ሥራው ነው። ሁሉም ነጻ የሆኑ የሞራል ወኪሎች ስለሆኑ ሀሳቦቻቸው በትክክለኛ መስመር እንዲሄዱ ማድረግ አለባቸው። --Und MS 93. (HC 337.) {1MCP 22.1} 1MCPAmh 20.3
ሰይጣን በመንፈስ ቅዱስ የማይመራ አእምሮን ይቆጣጠራል።--ሰብአዊነት እጅግ መዝቀጡን፣ ፈጽሞ መጥፎ ነገር እንዳለው ወይም መጥፎ መሆኑን፣ በአሳዛኝ ሁኔታ የእግዚአብሔር ተቃዋሚ እንደሆነ የሚያምኑት ጥቂቶች ናቸው። ‹‹ሥጋዊ አእምሮ የእግዚአብሔር ጠላት ነው፡-ለእግዚአብሔር ሕግ አይገዛም፣ መገዛትም አይችልም›› (ሮሜ 8፡ 7)። {1MCP 22.2} 1MCPAmh 20.4
አእምሮ በቀጥታ በእግዚአብሔር መንፈስ ተጽእኖ ሥር በማይሆንበት ጊዜ ሰይጣን እንደሚፈልገው ይቀርጸዋል። እርሱ የሚቆጣጠራቸውን የማሰብ ኃይሎችን በሙሉ ሥጋዊ እንዲሆኑ ያደርጋል። ግለሰቡ በፍላጎቱ፣ በአመለካከቱ፣ በምርጫዎቹ፣ በሚወዳቸውና በሚጠላቸው ነገሮች፣ በሚመርጣቸውና በሚከተላቸው ነገሮች በቀጥታ የእግዚአብሔር ተቃዋሚ ይሆናል፤ እግዚአብሔር ለሚወዳቸው ወይም ለሚቀበላቸው ነገሮች ፍላጎት አይኖረውም፣ ነገር ግን እርሱ በሚጠላቸው ነገሮች ይደሰታል፤ ስለዚህ እግዚአብሔር የሚጠላው መንገድ እንዲቀጥል ይደረጋል። {1MCP 22.3} 1MCPAmh 21.1
ይህ በእግዚአብሔር መንገድ ለመራመድ እየሞከሩ ካሉት ጋር ወደ መጋጨት ይመራል። እነርሱ [እውነትን የሚቃወሙት] ብርሃንን ጨለማ፣ ጨለማን ደግሞ ብርሃን ብለው ይጠራሉ፤ ጥሩ የሆነውን መጥፎ፣ መጥፎ የሆነውን ደግሞ ጥሩ ነው ይላሉ።--Lt 8, 1891. {1MCP 22.4} 1MCPAmh 21.2
ከአዳም ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ።--ሰይጣን ሄዋንን ካሳሳተ በኋላ አዳምን በኃጢአት ለማጥመድ መሳሪያ አድርጎ የተጠቀመባቸውን ውሸቶች የተቀበሉትን አእምሮዎች በሙሉ እስኪቆጣጠር ድረስ እየሰራ ነበር። ከዚያን ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ሰይጣን ውሸትን እውነት የማስመሰል ሥራውን ቀጥሎበታል። --MS 19, 1894. {1MCP 22.5} 1MCPAmh 21.3
እውነትን የሚያውቁት ልዩ የጥቃት ኢላማዎች ናቸው። ሰይጣን ወደ ስህተት የሚመሩ አስተሳሰቦችንና ምሳሌዎችን በማምጣት እውነትን የሚያውቁ ሰዎችን አእምሮ ግራ ለማጋባት በድብቅ በመስራት ላይ ይገኛል። የተከፋፈለ ሕይወት የሚኖሩ ሰዎች፣ እግዚአብሔርን እንደሚያገለግሉ እየተናገሩ በተመሳሳይ ጊዜ የራሳቸውን እቅዶች ለመፈጸም ዘዴዎችን የሚቀይሱ ሰዎች--ክርስቶስ ለመፈጸም ሕይወቱን የሰጠለትን ሥራ እንዲያዘግም የሚያደርግ እቅድ የሚያዘጋጁ ሰዎች--ካልተናዘዙና ካልተለወጡ በቀር በነፍሳት ጠላት ይታለላሉ። --Lt 248, 1907. {1MCP 22.6} 1MCPAmh 21.4
ሰይጣን እርስ በርሳቸው በሚቃረኑ ርዕሶች አእምሮዎችን ወደ ሌላ አቅጣጫ ይመልሳል።--እርሱ [ጠላት] የአመለካከት ልዩነቶችን መፍጠር ወደሚችልበት ወደ ማንኛውም ርዕሰ ጉዳይ አእምሮዎችን በመመለስ ሕዝባችንን ወደ እርስ በርስ ግጭት ወይም ታቃርኖ መምራት ሲችል ይደሰታል። --MS 167, 1897. {1MCP 23.1} 1MCPAmh 21.5
አንዱ አእምሮ ሌላውን ሲቆጣጠር።--አንዱ ሰብአዊ አእምሮ በሌላኛው ሰብአዊ አእምሮ ላይ ጫና ማሳደር በሚችልበት ኃይል ውስጥ ሰይጣን ብዙ ጊዜ ኃይለኛ የሆነ የክፋት ወኪል ያገኛል። ይህ ተጽእኖ እጅግ አታላይ ከመሆኑ የተነሣ በዚህ እየተቀረጸ ያለ ሰው ብዙ ጊዜ የእርሱን ኃይል አይገነዘብም። ይህን ክፋት በተመለከተ ማስጠንቀቂያ እንድሰጥ እግዚአብሔር አዞኛል። --Lt 244, 1907. (2SM 352.) {1MCP 23.2} 1MCPAmh 21.6
ለክፉ ነገር ኃይል፣ ለመጥፎ ነገር ኃይል።-- አንዱ አእምሮ በሌላ አእምሮ ላይ ያለው ተጽእኖ የተቀደሰ ከሆነ ለመልካም ነገር እጅግ ጠንካራ ኃይል የሚሆነውን ያህል እግዚአብሔርን በሚቃወሙት እጅ ሲሆን ለክፋት ጠንካራ ኃይል ይሆናል። ሰይጣን በመላእክት አእምሮ ውስጥ ክፉን ለመትከል ይህን ኃይል የተጠቀመ ሲሆን ይህን እያደረገ የነበረው ለዩኒቨርስ መልካም ነገርን ከመፈለግ የተነሣ እንደሆነ እንዲመስል አደረገ። ሉሲፌር የተቀባ ኪሩብ እንደመሆኑ እጅግ ከፍ ያለ ቦታ ነበረው፤ በሰማያዊ ፍጡራን ዘንድ እጅግ የተወደደ ስለነበር በእነርሱ ላይ የነበረው ተጽእኖ ጠንካራ ነበር። አብዛኞቻቸው የእርሱን አስተያየቶች ይሰሙ ቃላቶቹንም ያምኑ ነበር። ‹‹በሰማይ ሰልፍ ሆነ፡- ሚካኤልና መላእክቱ ዘንዶውን ተዋጉ፤ ዘንዶውም ከመላእክቱ ጋር ተዋጉ፣ አላሸነፉምም፤ በሰማይም ስፍራ አልተገኘላቸውም›› (ራዕይ 12፡ 8)--Lt 114, 1903. (7BC 973.) {1MCP 23.3} 1MCPAmh 22.1
የአንድ ሰው አእምሮ መታመን የለበትም።--የሰው እጅግ ታላላቅ ፍላጎቶች በጥያቄ ውስጥ ስለሆኑ እና አእምሮ ከሰብአዊ ድክመቶችና ስህተቶች ነጻ ስላልሆነ የአንድ ሰው አእምሮና የአንድ ሰው ፍርድ አሰጣጥ (ውሳኔ) መታመን የለበትም።…ማንኛውም ሰው ከተሳሳቱ የማነሳሻ ምክንያቶች የመንቀሳቀስ አደጋ እንዳይኖርበትና ነገሮችን ከተሳሳተ አቅጣጫ ከመመልከት እንዳይታቀብ አእምሮው ፍጹም አይደለም። --Lt 41, 1891. {1MCP 23.4} 1MCPAmh 22.2
ሰይጣን ያልተጠበቁ አእምሮዎችን በንቃት ይመለከታል።--ሰይጣን አእምሮን ባልተጠበቀ ጊዜ ለማግኘትና ለመቆጣጠር ነቅቶ እየጠበቀ ነው። ለእርሱ ዘዴዎች መሃይም መሆን የለብንም፣ በእርሱ ዘዴዎች መሸነፍም የለብንም። ብልህ ስለሆነ እርሱን ቀንዶችና ሰኮናዎች እንዳለው አስመስለው በሚቀርቡ ስዕሎች ደስ ይለዋል፤ በአንድ ወቅት የብርሃን መልአክ ነበር። --MS 11, 1893. {1MCP 24.1} 1MCPAmh 22.3
ክፉ መላእክት የሰውን ፈቃድ ለማጥፋት ይሞክራሉ።--ክፉ መላእክት ከተፈቀደላቸው ሰዎች የራሳቸው አእምሮ ወይም ፈቃድ እንዳይኖራቸው እስከሚያደርጉ ድረስ በአእምሮዎቻቸው ላይ ይሰራሉ [ይይዙና ይቆጣጠራሉ]።--MS 64, 1904. {1MCP 24.2} 1MCPAmh 22.4
ያለን ብቸኛው ደህንነት እርሱን በመቋቋም ነው።--ያለን ብቸኛው ደህንነት ለሰይጣን ቦታ አለመስጠት ነው፤ የእርሱ አስተያየቶችና ዓላማዎች እኛን ማቁሰልና በእግዚአብሔር ላይ እንዳንደገፍ መከልከል ነው። እርሱ እውነት በሚመስሉ ፈተናዎቹ አማካይነት የማታለያ ዘዴዎቹን በማንለይበት ሁኔታ ዕቅዶቹን ለማስተዋወቅ ራሱን ወደ ንጹህ መልአክ ይለውጣል። በተሸነፍንለት ቁጥር ማታለያዎቹ እያየሉ ይሄዳሉ። ከእርሱ ጋር መከራከር ወይም መደራደር አደጋ አለው። ለጠላት ዕድል በሰጠነው ቁጥር እርሱ የበለጠውን ይፈልግብናል። {1MCP 24.3} 1MCPAmh 22.5
ብቻኛው ደህንነታችን ያለ መጠን እንድንደፍር የሚያመጠውን የመጀመሪያውን ጥቆማ በጽናት መቋቋም ነው። እግዚአብሔር በክርስቶስ አማካይነት ሰይጣንን ለመቋቋም የሚያስችልና ከአሸናፊዎች በላይ እንድንሆን የሚያደርግ በቂ ጸጋ ሰጥቶናል። መቋቋም ስኬት ነው። ‹‹ሰይጣንን ተቋቋሙ፣ ከእናንተም ይሸሻል።›› ተቃውሞው ጽኑና ጠንካራ መሆን አለበት። ዛሬ ብቻ ተቃውመን ነገ የምንሸነፍ ከሆንን ያተረፍነውን ሁሉ መልሰን እናጣለን።--RH, Apr 8, 1880. (HC 95.) {1MCP 24.4} 1MCPAmh 23.1
ከድፍረት ተግባራት መራቅ።-- በግድ የለሽነት ራሳቸውን አደጋና ችግር ባለባቸው ቦታዎች የሚያስቀምጡና ራሳቸውን ለፈተናዎች የሚያጋልጡ ሰዎች አሉ፤ ከዚህ ውስጥ ሰይጎዱና ሳይበከሉ ለመውጣት የእግዚአብሔርን ተአምር ይጠይቃል። እነዚህ እግዚአብሔር የማይደሰትባቸው የድፍረት ተግባራት ናቸው። የዓለም አዳኝ ከቤተ መቅደሱ ጫፍ ራሱን ወደ ታች እንዲጥል ሰይጣን ያቀረበለትን ፈተና በጽናት ተቃውሞታል። ክርስቶስ እግዚአብሔር በሰጠው የተስፋ ቃል ብርታት የተጠየቀውን ነገር ያለ ስጋት እንዲያከናውን ለማድረግ ጠላት እግዚአብሔር የሰጠውን የተስፋ ቃል ጠቀሰ። ኢየሱስ ይህን ፈተና በመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ተጋፈጠ፡- ‹‹ጌታን አምላክህን አትፈታተነው ተብሎ ተጽፏልና።›› በተመሳሳይ ሁኔታ ሰይጣን ለሚያቀርባቸው አስተያየቶች ማስረጃ እንዲሆን ከመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን በመጥቀስ እግዚአብሔር እንዲሄዱ ወደማይፈልግባቸው ቦታዎች ሰዎች እንዲሄዱ ይገፋፋቸዋል።--RH, Apr 8, 1880. (HC 95.) {1MCP 24.5} 1MCPAmh 23.2
ትክክለኛ እምነትና ድፍረት።- እግዚአብሔር እንድንጠቀምባቸው የሰጠንን የተፈጥሮ ሕጎችን በመተላለፍ ወይም ጥንቃቄንና ፍርድን ችላ እያልንና በግድ የለሽነት ወደ አደጋ እየሮጥን እርሱ የሰጠንን የተስፋ ቃሎች በችኮላ እንዲሰጡን መጠየቅ ተገቢ አይደለም። ይህ ትክክለኛ እምነት ሳይሆን ድፍረት ይሆናል።…{1MCP 25.1} 1MCPAmh 23.3
ሰይጣን ወደ እኛ የሚመጣው ዓለማዊ ክብርን፣ ሀብትንና የሕይወት ደስታዎችን ይዞ ነው። እነዚህ ፈተናዎች የተለያየ ማዕረግ ያላቸውንና በተለያየ የኑሮ ደረጃ ያሉትን ሰዎች ለመገናኘትና ከፈጣሪያቸው ይልቅ ራሳቸውን እንዲያገለግሉና ከእግዚአብሔር እንዲርቁ ለማድረግ እንደየደረጃቸው የተለያዩ ናቸው። ሰይጣን ለክርስቶስ ‹‹እነዚህን ነገሮች ሁሉ እሰጥሃለሁ›› አለው። ‹‹ይህን ሁሉ ገንዘብ፣ ይህን መሬት፣ ይህን ሁሉ ሥልጣን፣ ክብርና ሀብት እሰጥሃለሁ››፤ በዚህ ሁኔታ ሰው ተማርኮአል፣ ተታሎአል፣ በብልጠት እርሱ ወዳዘጋጀው ጥፋት ተወስዶአል። ራሳችንን ለልብና ለሕይወት ዓለማዊነት አሳልፈን ስንሰጥ ሰይጣን ይረካል። --Lt 1a, 1872. (HC 93.) {1MCP 25.2} 1MCPAmh 23.4
የሰዎችን አእምሮዎች ክፉ መላእክት ወይም የእግዚአብሔር መላእክት ይቆጣጠራሉ።--የሰዎችን አእምሮዎች የእግዚአብሔር መላእክት ወይም ክፉ መላእክት እየተቆጣጠሩ ናቸው። አእምሮዎቻችን እግዚአብሔር ወይም የጨለማው ኃይሎች እንዲቆጣጠሩት አልፈው ተሰጥተዋል፤ ለእኛ መልካም የሚሆነው ዛሬ የት እንደቆምን--በደም በተቀለመው በልዑል አማኑኤል ባንዲራ ሥር ወይም በጨለማ ኃይላት ጥቁር ባንዲራ ሥር መሆናችንን-- መጠየቅ ነው። --MS 1, 1890. (6BC 1120.) {1MCP 25.3} 1MCPAmh 24.1
ከተሸነፍን ብቻ።--ሰይጣን ካልተሸነፍንለት በቀር አእምሮን ወይም የማሰብ ችሎታን ሊነካ አይችልም።--MS 17, 1893. (6BC 1105.) {1MCP 26.1} 1MCPAmh 24.2
የጠራ ማስተዋል ያስፈልጋል።--በስንዴና በገለባ መካከል፣ በሰይጣን ሳይንስና በእውነት ቃል ሳይንስ መካከል ያለውን ልዩነት ለማወቅ ጥርት ያለ መንፈሳዊ እይታ ያስፈልጋል። ታላቁ ሐኪም ክርስቶስ ወደ ዓለማችን የመጣው ለሚቀበሉት ሁሉ ጤናን፣ ሰላምንና የባሕርይ ፍጽምናን ለመስጠት ነበር። የእርሱ ወንጌል የክፉ ሥራ ሳይንስ የኋላ ኋላ ታላቅ መርገም መሆኑ ሲረጋገጥ እንደ ታላቅ በረከት የሚተዋወቅበትን ውጫዊ ዘዴዎችንና አፈጻጸሞችን አያካትትም። --Lt 130, 1901. (HC 109.) {1MCP 26.2} 1MCPAmh 24.3
ጸሎት ሰይጣንን ያሸንፋል።--የእምነት ጸሎት የክርስቲያን ትልቁ ብርታት ስለሆነ በእርግጠኝነት ሰይጣንን ያሸንፋል። ጸሎት እንደማያስፈልገን የሚጠቁምልን ከዚህ የተነሣ ነው። እርሱ የጠበቃችንን የኢየሱስን ስም ይጸየፋል፤ ከልባችን እርዳታ ፈልገን ወደ እርሱ ስንመጣ የሰይጣን ሠራዊት ይሸበራል። ጸሎትን ችላ ስንል የሰይጣን የውሸት ተአምራቶች ያለ አንዳች ችግር ተቀባይነት ስለሚያገኙ የእርሱን ዓላማ ለመፈጸም በደንብ ይጠቅመዋል። ክርስቶስን በመፈተን መፈጸም ያልቻለውን ነገር አታላይ የሆኑ ፈተናዎችን በሰው ፊት በማስቀመጥ ይፈጽመዋል። --1T 296 (1862). {1MCP 26.3} 1MCPAmh 24.4