አእምሮ፣ባሕርይና ማንነት፣ክፍል 1

6/45

ምዕራፍ 4—መንፈሳዊ ተጽእኖዎችና አእምሮ

ኃይማኖትና ጤና። የግል ኃይማኖት ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው። ዮሐንስ ለጋይዮስ እንዲህ በማለት ጽፏል፡- ‹‹ወዳጄ ሆይ፣ ነፍስህ እንደሚከናወን በነገር ሁሉ እንዲከናወንልህና ጤና እንዲኖርህ እጸልያለሁ›› (3ኛ ዮሐ. 2)። የአካል ጤና በአብዛኛው በነፍስ ጤና ላይ ይደገፋል፤ ስለዚህ ብትበሉ ወይም ብትጠጡ ወይም ምንም ነገር ብታደርጉ ሁሉን ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት። የግል ኃይማኖት በባህርይ፣ በቃላትና በተግባር ይገለጣል። በመጨረሻ ፍጽምና ‹‹እናንተ በእርሱ ሆናችሁ ሙሉ ሆናችኋል›› (ቆላ. 2፡ 10) የሚለውን የእግዚአብሔርን ሙገሳ እስከሚያገኝ ድረስ እድገት እንዲኖር ያደርጋል። --Lt 117, 1901. {1MCP 27.1} 1MCPAmh 25.1

ንፁህ ኃይማኖት የመንፈስ እርካታን፣ እርጋታንና ብርታትን ያመጣል።--ንጹህና ያልተበከለ ኃይማኖት ስሜት ሳይሆን የምህረትና የፍቅር ሥራን መስራት ነው። ይህ ኃይማኖት ለጤንነትና ለደስታ አስፈላጊ ነው። ወደተበከለው የነፍስ ቤተ መቅደስ ይገባና ኃጢአተኛ የሆኑ ሰርጎ ገቦችን በጅራፍ ያባርራቸዋል። ዙፋኑን በመቆናጠጥ ልብን በጽድቅ ፀሐይ ብሩህ ጮራዎች ያበራና በመገኘቱ ሁሉንም ይቀድሳል። የነፍስን መስኮቶች ወደ ሰማይ በመክፈት የእግዚአብሔርን ፍቅር ብርሃን እንዲገባ ያደርጋል። ከዚህ ጋር የመንፈስ እርካታና መረጋጋት ይመጣል። የሰማይ ከባቢ አየር እንደ ሕያውና እንደሚሰራ ወኪል ነፍስን ስለሚሞላ የአካል፣ የአእምሮና የሞራል ብርታት ይጨምራል። ክርስቶስ፣ የክብር ተስፋ፣ በውስጥ ይመሰረታል። --RH, Oct 15, 1901. (WM 38.) {1MCP 27.2} 1MCPAmh 25.2

እግዚአብሔር የሕይወትና የደስታ ምንጭ ነው። እግዚአብሔር ለዩኒቨርስ የሕይወት፣ የብርሃንና የደስታ ምንጭ ነው። ከፀሐይ እንደሚመጡ የብርሐን ጨረሮች፣ ከሕያው ምንጭ እንደሚፈልቁ የውኃ ወንዞች፣ በረከቶች ከእርሱ ለፍጥረታት ሁሉ ይፈልቃሉ። የእግዚአብሔር ሕይወት በሰዎች ልቦች በተገኘበት ሁሉ በፍቅርና በበረከት ወደ ሌሎች ይፈሳል። --SC 77 (1892). {1MCP 28.1} 1MCPAmh 25.3

ሁሉም ከእግዚአብሔር ሕይወትን ይቀበላሉ። የተፈጠሩ ነገሮች በሙሉ በእግዚአብሔር ፈቃድና ኃይል ይኖራሉ። የእግዚአብሔርን ልጅ ሕይወት ተቀባዮች ናቸው። ምንም ያህል ችሎታና መክሊት ያላቸው ቢሆኑም፣ ችሎታዎቻቸው ምንም ያህል ትልቅ ቢሆኑም፣ ሕይወታቸው የሚታደሰው የሕይወት ሁሉ ምንጭ ከሆነው በሚመጣው ሕይወት ነው። እርሱ ምንጭ፣ የሕይወት ውኃ ነው። የማይሞትና በብርሃንና በሕይወት የሚኖር እርሱ ብቻ ‹‹ሕይወቴን አሳልፌ ለመስጠትና መልሼ ለመቀበል ኃይል አለኝ›› ማለት ይችላል። -- MS 131, 1897. (5BC 1113.) {1MCP 28.2} 1MCPAmh 25.4

ሰይጣን አእምሮ በሌሎች አእምሮ ላይ ያለውን ተጽእኖ ይጠቀማል። ሰይጣን ከሰማይ ከተጣለ በኋላ መንግስቱን በዚህች ዓለም ላይ መሰረተ፤ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ሰብአዊ ፍጡራንን ለእግዚአብሔር ካላቸው ታማኝነት ሊያስታቸው ያለማቋረጥ ጥረት እያደረገ ነው። በሰማይ የተጠቀመበትን ያንኑ ኃይል፣ አእምሮ በአእምሮ ላይ ያለውን ተጽእኖ፣ ይጠቀማል። ሰዎች የባልንጀሮቻቸው ፈታኞች ይሆናሉ። ጠንካራ የሆኑና ብልሽት የሚያስከትሉ የሰይጣን ሀሳቦች ተቀባይነት ካገኙ የመቆጣጠርና የማስገደድ ኃይልን ይጠቀማሉ። በእነዚህ ሀሳቦች ተጽእኖ ሥር ሰዎች እርስ በርሳቸው በሕብረቶች፣ በንግድ ዩኒየኖች እና በምስጢር ማህበራት አንድ ይሆናሉ። በዚህ ዓለም ላይ እግዚአብሔር ከዚህ በላይ ለብዙ ጊዜ ሊታገሳቸው የማይችላቸው ወኪሎች በሥራ ላይ ናቸው። --Lt 114, 1903. {1MCP 28.3} 1MCPAmh 26.1

የራስ ወዳድነት ፍላጎቶችን ለማሟላት የሚረዱ ኃይሎችን ሥራ ላይ ለማሰማራት የሰይጣን የተጠና ዓላማ።-- አእዋፍን የሚያጠምድ ሰው ወጥመድ እንደሚያዘጋጅ ሁሉ ሰይጣንም ነፍሳትን ለማጥመድ ያዘጋጃቸው መረቦችና ወጥመዶች አሉት። ሰዎች እግዚአብሔር የሰጣቸውን ኃይሎች እርሱን ለማስከበር አሳልፈው ከመስጠት ይልቅ የራስ ፍላጎትን ለማሟላት አሳልፈው እንዲሰጡ ማድረግ የሰይጣን የተጠና ዓላማ ነው። እግዚአብሔር የሚፈልገው ሰዎች ሰላምና ደስታ በሚያመጣላቸውና ዘላለማዊ ትርፍ በሚያስገኝላቸው ሥራ ላይ እንዲሰማሩ ነው፤ ነገር ግን ሰይጣን ለማይጠቅሙንና ስንጠቀምባቸው ለሚበላሹ ነገሮች ጥረት እንድናደርግ ይፈልጋል። --RH, Sept 1, 1910. (HC 200.) {1MCP 28.4} 1MCPAmh 26.2

መተላለፍ ምንም ዓይነት አዲስ የጉልበትና የፍላጎት ሥርዓት አላመጣም። ከአዳም መተላለፍ ጀምሮ እግዚአብሔር ለሰብአዊ ፍጡራን አዲስ የኃይልና የፍላጎት ስርዓት ሰጥቷል ብለን መገመት የለብንም፤ እንዲህ ከሆነ እግዚአብሔር በሰብአዊ ዘር ውስጥ ኃጢአተኛ የሆኑ ዝንባሌዎችን ለማስቀመጥ ጣልቃ የገባ ይመስላል። ለእግዚአብሔር ሕግ በመታዘዝና በክርስቶስ በማመን ሰዎች በመተላለፍ ምክንያት ያጡትን የእግዚአብሔርን ምስል መልሰው እንዲያገኙ ለማድረግ ሰው እንደተላለፈ ወዲያውኑ ክርስቶስ የመለወጥ ሥራውን ጀመረ። --MS 60, 1905. {1MCP 29.1} 1MCPAmh 26.3

እያንዳንዱ ሰው ከሁለቱ አርማዎች አንዱን መምረጥ አለበት። ትልቅ ጉዳይ እዚህ አለ። እርስ በርሳቸው እየተፋጠጡ ያሉ ሁለቱ ታላላቅ ኃይላት፣ የእግዚአብሔር ልዑል፣ ኢየሱስ ክርስቶስ እና የጨለማው ልዑል ሰይጣን ናቸው። ግልጽ የሆነ ጦርነት ያለው እዚህ ላይ ነው። በዓለም ላይ ሁለት ክፍሎች ብቻ ያሉ ሲሆን እያንዳንዱ ሰብአዊ ፍጡር ከሁለቱ አርማዎች ሥር፣ ማለትም ከጨለማው መስፍን አርማ ሥር ወይም ከኢየሱስ ክርስቶስ አርማ ሥር ራሱን ያሰልፋል። --Lt 38, 1894. {1MCP 29.2} 1MCPAmh 26.4

ኃጢአት አጠቃላይ ማንነትን ይነካል። ኃጢአት መላውን ፍጡር እንደሚነካ ሁሉ ጸጋም መላውን ማንነት ይነካል። --Lt 8, 1891. {1MCP 29.3} 1MCPAmh 27.1

የነፍስን ኃይላት ወደ ታች የጎተተው ኮብላይ ልብ ነው። የነፍስ ቤተ መቅደስ የኃያሉ አምላክ ማደሪያ ቤተ መቅደስ እንዲሆን የድነትን ሳይንስ የሚማሩ ሁሉ በክርስቶስ ትምህርት ቤት ውስጥ ራሳቸውን ያስገዙ መሆን አለባቸው። ከክርስቶስ መማር ካለብን እርሱ የራሱን ምስል በነፍስ ላይ እንዲቀርጽ ነፍስ መኩራሪያ አድርጋ ከያዘቻቸው ሀብቶቿ ሁሉ መላቀቅ አለባት።--Lt 5, 1898. (HC 105.) {1MCP 29.4} 1MCPAmh 27.2

መስቀል ለሰብአዊ አእምሮ ተገቢ የሆነ ደረጃ ይሰጣል። ለሰብአዊ አእምሮ ትክክለኛውን ደረጃ የሚሰጥ ምንድር ነው? የቀራኒዮ መስቀል ነው። የእምነታችን ጀማሪና ፈጻሚ የሆነውን ኢየሱስን በመመልከት ራስን ከፍ ለማድረግ ያለው ፍላጎት ሁሉ በአፈር ውስጥ ይጣላል። በትክክል መመልከት ስንችል ራስን ዝቅ ማድረግንና የአእምሮ የዋህነትን የሚያበረታታው የትህትና መንፈስ ይመጣል። መስቀልን ስናሰላስል ለእያንዳንዱ አማኝ ያመጣውን አስደናቂ መሰናዶ ማየት እንድንችል እንደረጋለን። በትክክል ከታየ እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ… የሰብአዊ ዘርን ራስን ከፍ ከፍ ማድረግንና ጉራን ያጠፋል። ራስን ከፍ ማድረግ አይኖርም፣ ነገር ግን እውነተኛ የሆነ ራስን ማዋረድ ይኖራል። --Lt 20, 1897. (HC 114.) {1MCP 29.5} 1MCPAmh 27.3

ክርስቶስ ሰውን ፍጹም (ምሉእ) አድርጎ ፈጥሮታል።- ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱ ከእርሱ ጋርና ከአባቱ ጋር ሕያው ግንኙነት እንዲኖራቸው ያደርጋል። መንፈስ ቅዱስ በሰብአዊ አእምሮ በሚሰራው ሥራ አማካይነት ሰው በክርስቶስ ኢየሱስ ፍጹም ይሆናል። ከክርስቶስ ጋር የተፈጠረው አንድነት ከእርስ በርስ ጋር አንድነትን ይፈጥራል። ይህ አንድነት ስለ ክርስቶስ ንጉሥነትና መልካምነት እንዲሁም ኃጢአትን ስለሚያስወግደው ኃይሉ ለዓለም አሳማኝ ማረጋገጫ ነው። --MS 111, 1903. (5BC 1148.) {1MCP 30.1} 1MCPAmh 27.4

ሰውን ወደ ግብረገብ ብቃት ደረጃ የሚያደርስ እግዚአብሔር ብቻ ነው።--በክርስቶስ ጽድቅ አማካይነት ሰውን ወደ ግብረገብ ብቃት ማድረስ የሚችል እግዚአብሔር ብቻ ስለሆነ እግዚአብሔር ለሰው የሚሰጠው ዋጋ የሚለካው ግለሰቡ ከክርስቶስ ጋር ባለው ግንኙነት ነው። ዓለማዊ ክብርና ታላቅነት ፈጣሪ ለሰው ከሚሰጠው ዋጋ እጅግ የራቁ ናቸው። ጥበባቸው ሞኝነት ነው፣ ብርታታቸው ድካም ነው። --Lt 9, 1873. (HC 149.) {1MCP 30.2} 1MCPAmh 27.5

ራስ ወዳድነትና ፍሬው።--ራስ ወዳድነት የግብረገብ ብልሽት ስለሆነ እና ሰብአዊ ፍጡራን በራስ ወዳድነት ኃይል ስለተሸነፉ ዛሬ በዓለም ላይ ለእግዚአብሔር ከመገዛት ይልቅ ታቃራኒ የሆነ ባሕርይ ይንጸባረቃል። ሕዝቦች፣ ቤተሰቦች እና ግለሰቦች ራስን ማዕከል በማድረግ ፍላጎት ተሞልተዋል። ሰው እንደ እርሱ ባሉ ሰዎች ላይ ገዥ የመሆን ፍላጎት አለው። ከራስ ወዳድነቱ የተነሣ ራሱን ከእግዚአብሔርና እርሱን ከመሰሉ ፍጡራን በመለየት ልጓም ያልተደረገባቸውን ዝንባሌዎቹን ይከተላል። የሌሎች ደህንነት የሚደገፈው የእርሱን የበላይነት በመቀበላቸው እንደሆነ ያስባል። --RH, June 25, 1908. (CS 24.) {1MCP 30.3} 1MCPAmh 28.1

ድል ሊገኝ ይችላል።--የጽድቅ መርሆዎችን በማጎልበት ሰው በተሳሳተ ግምትና በክፋት ላይ ድል ሊቀዳጅ ይችላል። ለእግዚአብሔር ሕግ ታዛዥ ከሆነ ስሜቶች የጎበጡና የተጣመሙ አይሆኑም፤ የተለያዩ የአካል ክፍሎች ከእግዚአብሔር የሚያርቁ ነገሮችን ለማድረግ ጥቅም ላይ ስለማይውሉ የተዛቡና የባከኑ አይሆኑም። ሰማይ በሰጠው ጸጋ አማካይነት ቃላት፣ ሀሳብ እና ጉልበት ይነጻሉ፤ አዲስ ባሕርይ ተመስርቶ የኃጢአት ዝቅጠት ይሸነፋል። --MS 60, 1905. {1MCP 30.4} 1MCPAmh 28.2

የአእምሮ መዋዠቅ የፈተና ጅምር ነው።--በፈተና የመሸነፍ ጅምሩ አእምሮ እንዲዋዥቅ፣ በእግዚአብሔር ላይ ያለህ መታመን ጽናት እንዲያጣ በማድረግ ኃጢአት ውስጥ ነው። ክፉው (ሰይጣን) በእግዚአብሔር ላይ ጥላሸት ለመቀባትና አእምሮን ወደ ተከለከለው ነገር ለመሳብ ሁል ጊዜ ነቅቶ ይጠብቃል። {1MCP 31.1} 1MCPAmh 28.3

ከተቻለው አእምሮ በአለማዊ ነገሮች ላይ እንዲያተኩር ያደርጋል። ስሜትን ለማነሳሳት፣ ፍትወትን ለመቀስቀስና ፍላጎትህን በማይጠቅሙህ ነገሮች ላይ ለማጣበቅ ጥረት ያደርጋል፤ ነገር ግን እያንዳንዱን ስሜትህን ለትክክለኛ ግንዛቤና ለህሊናህ ማስገዛት የአንተ ጉዳይ ነው። ያኔ ሰይጣን አእምሮህን የመቆጣጠር ኃይል ያጣል። {1MCP 31.2} 1MCPAmh 28.4

ክርስቶስ እንድንሰራ እየጠራን ያለው ሥራ በባሕርያችን ውስጥ ያለውን መንፈሳዊ ክፋት በቀጣይነት የማሸነፍ ሥራ ነው። የተፈጥሮ ዝንባሌዎች መሸነፍ አለባቸው።---የምግብ ፍላጎትና ፍትወት መሸነፍ አለባቸው፣ ፈቃዳችንም ሙሉ በሙሉ በክርስቶስ ወገን መሆን አለበት። --RH, June 14, 1892. (HC 87.) {1MCP 31.3} 1MCPAmh 28.5

በውርስ ከመጡ ዝንባሌዎች የተነሣ ማንም ተስፋ መቁረጥ የለበትም። ሰይጣን ለማታለልና ወደ ስህተት ለመምራት ሁል ጊዜ ነቅቶ ይሰራል። ታዛዥ ያልሆኑ ሰዎች በሚሄዱበት ሰፊ መንገድ ላይ እንዲሄዱ ሰዎችን ለማታለል እያንዳንዱን የመማረክ ዘዴ በመጠቀም ላይ ይገኛል። ስሜቶችን በስህተት አስተሳሰቦች ግራ ለማጋባትና እግዚአብሔር ትክክለኛውን መንገድ ለማመልከት ባቆማቸው የመንገድ ዳር ምልክቶች ላይ የራሱን የውሸት ጽሁፍ በማስቀመጥ ትክክለኛውን ምልክት ለማጥፋት በመሥራት ላይ ይገኛል። ድነትን ወራሽ የሆኑትን ሰዎች በመምራት፣ በመጠበቅ እና በመቆጣጠር አገልግሎት እንዲሰጡ ለሰማያዊ ፍጡራን ሀላፊነት የተሰጠበት ምክንያት እነዚህ ክፉ ወኪሎች ከነፍስ ውስጥ እያንዳንዱን የብርሐን ጮራ ለመጋረድ ጥረት በማድረግ ላይ ስላሉ ነው። በውርስ ከመጣው የክፉ ዝንባሌ የተነሣ ማንም ሰው ተስፋ መቁረጥ የለበትም፣ ነገር ግን የእግዚአብሔር መንፈስ ስለ ኃጢአት ሲዘልፍ ስህተት የፈጸመው ግለሰብ ኃጢአቱን መናዘዝ፣ ንስሃ መግባትና ክፋትን መተው አለበት። ታማኝ የሆኑ ወታደሮች ነፍሳትን በትክክለኛው መንገድ ለመምራት በመጠባበቅ ላይ ናቸው። -- MS 8, 1900. (6BC 1120.) {1MCP 31.4} 1MCPAmh 29.1

ከሌሎች ጋር ሕብረት በመፍጠር የኃጢአት ተካፋይ መሆን።---ከእግዚአብሔር ሀሳብና ባሕርይ ተቃራኒ የሆነ ነገርን ለማድረግ ከስህተት ተጽእኖዎች የተነሣ ወደ ስህተት የተመራች እና ከሌሎች ጋር ሕብረት ከመፍጠሯ የተነሣ የኃጢአት ተካፋይ የሆነች ነፍስ ተስፋ መቁረጥ የለባትም። ‹‹ቅዱስና ያለ ተንኮል ነውርም የሌለበት ከኃጢአተኞችም የተለየ ከሰማያትም ከፍ ከፍ ያለ ሊቀ ካህናት ይገባናልና›› (ዕብ. 7፡ 26)። ክርስቶስ ካህንና አማላጅ ብቻ ሳይሆን መስዋዕትም ነው። አንዴ ራሱን ለሁሉ መስዋዕት አድርጓል። --Lt 11, 1897. {1MCP 32.1} 1MCPAmh 29.2

ሰይጣን ተስፋ ለማስቆረጥ ይሰራል፤ ክርስቶስ ተስፋ እንዲኖረን ይሰራል።---ለአንድ አፍታ እንኳን ቢሆን የሰይጣን ፈተናዎች ከእናንተ ሀሳብ ጋር እንደሚጣጣሙ አድርጋችሁ አትቀበሉ። ከጠላት ከራሱ እንደምትሸሹ አድርጋችሁ ከእነዚህ ፈተናዎች ሽሹ። የሰይጣን ሥራ ነፍስን ተስፋ ማስቆረጥ ነው። የክርስቶስ ሥራ ደግሞ ልብን በእምነትና በተስፋ መሙላት ነው። ሰይጣን መታመናችንን ለመናድ ይፈልጋል።ተስፋዎቻችን እርግጠኛ በሆነውና መዋሸት በማይችለው በእርሱ የማይጠፋ ቃል ላይ ከመመስረት ይልቅ በተሳሳተ ቦታ ላይ እንደተመሰረቱ ይነግረናል።. --MS 31, 1911. (HC 85.) {1MCP 32.2} 1MCPAmh 29.3

ለሁሉም ዓይነት ፈተናዎች መፍትሄ።---ለሁሉም ዓይነት ፈተናዎች መፍትሄ አለ። ከራሳችንና ኃጢአተኛ ከሆነው ባህሪያችን ጋር ያለውን ጦርነት ውስን በሆነው ብርታታችን መዋጋት አንችልም። ኢየሱስ ኃያል ረዳታችን፣ ፍጹም የማይጥለን ደጋፊያችን ነው።…ይህን የመሰለ በቂ እርዳታ እያለን ማንም ቢሆን መውደቅ ወይም ተስፋ መቁረጥ የለበትም።--RH, Apr 8, 1884. (HC 88.) {1MCP 32.3} 1MCPAmh 29.4

የክርስቶስ ደም ብቸኛው ፈውስ።---የያህዌ ሕግ እጅግ ሰፊ ነው። ይህ ቅዱስ የሆነው የእግዚአብሔር ሕግ በቃልና በተግባር እንደሚጣስ ሁሉ በሀሳብና በስሜትም ሊጣስ እንደሚችል ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ በግልጽ ነገራቸው። ከሁሉም አብልጦ እግዚአብሔርን የሚወድ ልብ በማንኛውም መንገድ ቢሆን ጥቃቅን ምክንያቶችን በመፈለግ ሕግጋቱን ወደ ማጥበብ አያዘነብልም፣ ነገር ግን ሕግን በመንፈሳዊ ኃይሉ ስንመለከት፣ ታዛዥና ታማኝ የሆነ ልብ በደስታ ሙሉ የሆነ መንፈሳዊ መታዘዝን ያሳያል። ያኔ ትዕዛዛቱ በትክክለኛ ኃይላቸው ወደ ነፍስ ይመጣሉ። ኃጢአት ኃጢአትነቱ እጅግ ጎልቶ ይታያል። የራስ ጽድቅ፣ ስለ ራስ እልቅና ማሰብ፣ የራስ ክብር አይኖርም። ስለ ራስ ደህንነት መጨነቅ ይጠፋል። የዚህ ውጤት ጥልቅ የሆነ የኃጢአተኛነት ስሜት እና ራስን መጥላት ይሆንና ነፍስ አደጋ ውስጥ መሆኑ እጅግ ስለሚሰማው የእግዚአብሔርን በግ ደም እንደ ብቸኛ ፈውስ አድርጎ ይወስዳል። --Lt 51, 1888. (HC 140.) {1MCP 32.4} 1MCPAmh 30.1

የፈታኝን ግድድሮሽ መጋፈጥ።---ሰይጣን ኃጢአተኛ እንደሆንክ እየነገረህ ይመጣል። ነገር ግን ኃጢአተኛ ስለሆንክ እግዚአብሔር ትቶሃል በሚል ሀሳብ አእምሮህን እንዲሞላ አትፍቀድለት። ለሰይጣን፡- አዎን ኃጢአተኛ ነኝ፣ አዳኝ የምፈልግበት ምክንያቱ ይህ ነው ብለህ ንገረው። ይቅርታና ምህረትን እፈልጋለሁ፣ ክርስቶስ ወደ እርሱ ከመጣሁ እንደማልጠፋ ነግሮኛል። ለእኔ በላከልኝ ደብዳቤ እንዲህ የሚለውን አነባለሁ፡- ‹‹በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለንና ከዓመጻም ሁሉ ሊያነጻን እርሱ የታመነና ጻድቅ ነው›› (1ዮሐ. 1፡ 9)።ለእኔ ያስቀመጠልኝን ቃል አምናለሁ። ትዕዛዛቱን እታዘዛለሁ። ሰይጣን ጠፍተሃል ብሎ ሲነግርህ አዎን ጠፍቻለሁ፣ ግን ኢየሱስ የመጣው የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን ነው። ኃጢአቴ የተለቀውን ያህል አዳኝ የሚያስፈልገኝም በዚያው ልክ ነው ብለህ መልስለት።--Lt 98b, 1896. {1MCP 33.1} 1MCPAmh 30.2

ትኩረት ከግራ መጋባት ወደ እግዚአብሔር የእጅ ሥራ ሲመለስ።…እግዚአብሔር ፍጥረቶቹ በዙሪያቸው ካለው ውዝግብና ግራ መጋባት ትኩረታቸውን እንዲያነሱና የእርሱን እጅ ሥራ እንዲያደንቁ ይጠራቸዋል። ሰማያዊ አካላት እንድናሰላስልባቸው የተገቡ ናቸው። እግዚአብሔር ለሰው ጥቅም ስለፈጠራቸው የእርሱን ሥራዎች ስናጠና ሳለ አእምሮአችንን ሊያበሩና ከሰይጣን ማታለያ ሊጠብቁን የእግዚአብሔር መላእክት ከአጠገባችን ይሆናሉ። --MS 96, 1899. (4BC 1145.) {1MCP 33.2} 1MCPAmh 30.3

ኃይማኖት የሚያደርገው ነገር።---እውነተኛ ኃይማኖት አእምሮን የከበረ ያደርጋል፣ ለነገሮች ያለንን ፍላጎት ያስተካክላል፣ ፍርድ አሰጣጣችንን ይቀድሳል፣ ባለቤቱን ደግሞ የሰማይ ንጽህናና ቅድስና ተካፋይ ያደርጋል። መላእክትን ወደ አጠገባችን በማምጣት ከዓለም መንፈስና ተጽእኖ አብልጦ ይለየናል። ወደ ሁሉም የሕይወት ተግባራትና ግንኙነቶች በመግባት ‹‹የተስተካከለ አእምሮና መንፈስ›› ይሰጠናል፣ ውጤቱም ደግሞ ደስታና ሰላም ነው። --ST, Oct 23, 1884. (CH 629, 630.) {1MCP 34.1} 1MCPAmh 31.1

የአእምሮ እውቀትን ችሎታ ይጨምራል።---በዳንኤል እንደታየው መንፈሳዊ ባሕርይ ባደገ መጠን የአእምሮ እውቀት ችሎታም ይጨምራል። -- RH, Mar 22, 1898. (4BC 1168.) {1MCP 34.2} 1MCPAmh 31.2

የአካል ጤናን ያሻሽላል።---አእምሮ ጨዋ ሲሆንና ፈቃድ ከእግዚአብሔር ወገን ሲሆን አስደናቂ የሆነ የአካል ጤና መሻሸል ይኖራል።--Medical Missionary, Nov-Dec, 1892. (CH 505.) {1MCP 34.3} 1MCPAmh 31.3

ትክክል የሆነውን ነገር ማድረግ ፍቱን መድሃኒት ነው።---ትክክል የሆነውን ነገር ማድረግን ማወቅ ለታመመ አካልና አእምሮ ፍቱን መድሃኒት ነው። በተቀባዩ ላይ የሚያርፈው ልዩ የእግዚአብሔር በረከት ጤናና ብርታት ነው። አእምሮው የተረጋጋና በእግዚአብሔር የረካ ሰው በጤና አውራ ጎዳና ላይ ነው። የእግዚአብሔር ዓይን በላያችን እንደሆነና ጆሮቹም ለጸሎታችን ክፍት እንደሆኑ ማወቅ እርካታ ነው። የነፍሳችንን ምስጢሮች ሁሉ ልንነግረው የምንችል ፈጽሞ የማይተወን ወዳጅ እንዳለን ማወቅ ቃላት በፍጹም ሊገልጹት የማይችሉት ደስታ ነው። --ST, Oct 23, 1884. (CH 628.) {1MCP 34.4} 1MCPAmh 31.4

የኢየሱስ ፍቅር ነፍሳትን መልካም መዓዛ ባለው ከባቢ አየር ይከባል።---ኢየሱስን የሚወዱ ሰዎች ነፍስ ንጹህና በመዓዛ በተሞላ ከባቢ አየር ትከበባለች። የነፍሳቸውን ረሃብ የሚደብቁ ሰዎች አሉ። እንደዚህ ያሉ ሰዎች በእጅጉ የሚረዱት ገር በሆነ ቃል ወይም ቸርነት ባለበት ትውስታ ነው። ከእግዚአብሔር በነጻ ተትረፍርፈው የተሰጡት ሰማያዊ ስጦታዎች የእኛ ተጽእኖ በሚደርስበት አካባቢ ላሉ ሰዎች ሁሉ በነጻ መሰጠት አለባቸው። በዚህ መልኩ ከሰማይ የተገኘውንና ሌሎችን በመባረክ ሂደት በነጻ ጥቅም ላይ በዋለ ቁጥር እየጨመረ የሚሄደውን ፍቅር እናሳያለን። በመሆኑም እግዚአብሔርን እናከብራለን። --MS 17, 1899. (HC 231.) {1MCP 34.5} 1MCPAmh 31.5

የአንዲት ቅጽበት ሀሳብ የለሽነት ውጤቶች።---አንዲት የህሊናን ልጓም መልቀቅ፣ አንዲት ክፉ ልምድን መፈጸም፣ አንዲት እንድትፈጽመው የተሰጠህን ከፍተኛ ተግባር ችላ ማለት፣ ሁል ጊዜ እግዚአብሔርንና የእርሱን ሥራ እንደምትወድ እየተናገርክ ሳለህ ሰይጣንን ከሚያገለግሉ ሰዎች ጎራ እንድትመደብ የሚያደርግህ የመታለል መንገድ ጅምር ሊሆን ይችላል። ሀሳብ የለሽ የሆናችሁበት አንዲት ቅጽበት፣ አንዲት የስህተት እርምጃ፣ መላውን የሕይወታችሁን እንቅስቃሴ በተሳሳተ አቅጣጫ እንዲሄድ ታደርጋለች። -- 5T 398 (1885). {1MCP 35.1} 1MCPAmh 31.6

የዘራነውን ዘር መከር እንዳንሰበስብ ለማድረግ እግዚአብሔር ምንም ተአምር አይሰራም።---ስህተቶቻችን ሁለተኛው ባሕርያችን ከመሆናቸው በፊት እግዚአብሔር ስህተቶቻችንን ማስተካከል እንድንችል እድል ሊሰጠን ማስጠንቀቂያን፣ ምክርን እና ተግሳጽን ይልክልናል። ነገር ግን ለመታረም ፈቃደኛ ካልሆንን፣ የራሳችንን የተግባር መንገድ ለመከተል ያለንን ዝንባሌ ለመቃረን እግዚአብሔር ጣልቃ አይገባም። የተዘራው ዘር እንዳይበቅልና ፍሬ እንዳያፈራ ለማድረግ ምንም ዓይነት ተአምራት አይሰራም።{1MCP 35.2} 1MCPAmh 32.1

በመለኮታዊ እውነት ላይ የክህደት ድፍረትን የሚያሳይ ወይም መለኮታዊ እውነት ስሜት የማይሰጠውን ግድየለሽነት የሚያሳይ ሰው ራሱ የዘራውን መከር ይሰበስባል። ይህ የብዙዎች ልምምድ ነው። በአንድ ወቅት ነፍሶቻቸውን ቀስቅሰው የነበሩ እውነቶችን ቅዝቃዜ በተሞላበት ቸልተኝነት ይሰሙአቸዋል። ቸልተኝነትን፣ ግድ የለሽነትን እና እውነትን መቋቋምን ዘሩ፤ ከዚህ የተነሣ የሚሰበስቡት መከር የዚሁ ዓይነት ይሆናል። የበረዶ ቅዝቃዜ፣ የብረት ጥንካሬ፣ ምንም በውስጡ የማያሳልፍና ምንም ነገር ሊገባው የማይችል የዓለት ባሕርይ፡- እነዚህ ሁሉ ባሕርያት ክርስቲያን ነን በሚሉ በብዙዎች ባሕርይ ውስጥ ጓደኛ አላቸው።{1MCP 35.3} 1MCPAmh 32.2

እግዚአብሔር የፈርዖንን ልብ ያጠነከረው እንዲህ ነበር። እግዚአብሔር ለግብፅ ንጉስ በሙሴ አፍ እጅግ አስደናቂ የሆነውን መለኮታዊ ኃይል ማረጋገጫ በመስጠት ተናገረው፤ ነገር ግን ንጉሡ ወደ ንስሃ ሊያመጣው ይችል የነበረውን ብርሃን በትዕቢት አልቀበል አለ። እግዚአብሔር የአመጸኛውን ንጉስ ልብ ለማጠንከር ከተፈጥሮ ውጭ የሆነ ኃይል አልላከም፣ ነገር ግን ፈርዖን እውነትን አልቀበል ሲል መንፈስ ቅዱስ ከእርሱ ተለየና በመረጠው ጨለማና አለማመን ውስጥ ተተወ። ሰዎች ያለማቋረጥ የመንፈስ ቅዱስን ተጽእኖ ሲቋቋሙ ራሳቸውን ከእግዚአብሔር ይለያሉ። አእምሮአቸውን ለማብራት የተጠበቀ ችሎታ ያለው ወኪል የለም። ካለማመናቸው የተነሣ የእርሱ ፈቃድ መገለጥ ሊደርሳቸው አይችልም። --RH, June 20, 1882. (3BC 1151.) {1MCP 35.4} 1MCPAmh 32.3

በዙሪያችን ባሉ ነገሮች ከመቀረጽ ይልቅ ዙሪያችንን መቅረጽ።---ሰው ሊቀንሳቸው የሚችላቸው ግን ሊያጠፋቸው የማይችላቸው ክፉ ነገሮች አሉ። እንቅፋቶችን በማሸነፍ በአካባቢው ባሉ ነገሮች ከመቀረጽ ይልቅ አካባቢውን መቅረጽ አለበት። ከውዝግብ ውስጥ ሥርዓትንና መጣጣምን በማምጣት ሂደት ችሎታዎቹን ሥራ ላይ ለማዋል ቦታ አለው። በዚህ ሥራ ውስጥ እርዳታ ከጠየቀ መለኮታዊ ድጋፍ ሊሰጠው ይችላል። በራሱ ብርታት ፈተናዎችንና ችግሮችን እንዲዋጋ አይተውም። እርዳታ ያለው ኃያል በሆነው ላይ ነው። ሰው በሕይወት ፈተናዎች ውስጥ እንዲያልፍና ፈተናዎችን እንዲቋቋም ሰውን ለማስተማር ኢየሱስ ንጉሣዊውን የሰማይ አደባባዮች ተወ። እዚህ ላይ እንድንከተለው ምሳሌ ተቀምጦልናል።--5T 312 (1885). {1MCP 36.1} 1MCPAmh 33.1

እግዚአብሔር አእምሮ እንዲታደስ ይፈልጋል።---ጥያቄ የሚያሳድሩ (አጠራጣሪ) መርሆዎችና ልምምዶች ቆሻሻ ተጠራርጎ መውጣት አለበት። እግዚአብሔር የሚፈልገው አእምሮ እንዲታደስና ልብ በእውነት ሀብቶች እንዲሞላ ነው። --MS 24, 1901. (HC 106.) {1MCP 36.2} 1MCPAmh 33.2

ከተለያዩ አእምሮዎች ጋር በጥበብ መሥራት።---ሰዎች ለእግዚአብሔር ቃልና እውነተኛ ለሆነው የክርስቲያን ሕይወት ትክክለኛ የሆነ መረዳት እንዲኖራቸው መርዳት እንድንችል ሁላችንም ከተለያዩ አእምሮዎች ጋር እንዴት በጥበብ መሥራት እንደምንችል ለማወቅ ባሕርይንና ሁኔታዎችን ማጥናት ያስፈልገናል። ከእነርሱ ጋር መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናትና አእምሮአቸውን ከጊዜያዊ ነገሮች ወደ ዘላለማዊ ነገሮች መሳብ አለብን። የእግዚአብሔር ልጆች ሥራ ለእርሱ ሚስዮናውያን መሆን፣ እርዳታ ከሚያስፈልጋቸው ጋር መተዋወቅ ነው። አንድ ሰው ከፈተና ሥር ሆኖ እየተንገዳገደ ከሆነ የእርሱ ጉዳይ በጥንቃቄ መወሰድና በጥበብ መያዝ አለበት፤ የዚህ ግለሰብ ዘላለማዊ ፍላጎት አደጋ ላይ ስለሆነ ለእርሱ ድነት እየሰሩ ያሉ ሰዎች ቃላትና ተግባር የሕይወት ሽታ ለሕይወት ወይም የሞት ሽታ ለሞት ሊሆን ይችላል።--4T 69 (1876). {1MCP 36.3} 1MCPAmh 33.3

የማይታጠፍ (የማይጎብጥ) መርህ የኢየሱስ ተማሪዎች መለያ ነው። የማይታጠፍ መርህ በኢየሱስ እግር ሥር ቁጭ ብለው ከእርሱ የሚማሩ ሰዎች የሚሄዱበትን መንገድ ያሳያል። --RH, June 20, 1882. (HC 160.) {1MCP 37.1} 1MCPAmh 33.4