አእምሮ፣ባሕርይና ማንነት፣ክፍል 1

9/45

ምዕራፍ 7—በአእምሮ ውስጥ የሚጀምር በሽታ

[‹‹የሚሆነውን ማሰብና ሕመም›› የሚለውን ምዕራፍ 75ን ይመልከቱ።]

በሽታን ለሚያስከትሉ ነገሮች በጣም ትንሽ ግምት ተሰጥቷል።--ዛሬ እጅግ በሰለጠኑትና በታደሉ አገሮች እንኳን ሳይቀር ሞትን ለሚያስከትሉ ነገሮች፣ በሽታና የሞራል ብልሽት፣ እጅግ በጣም አነስተኛ ግምት ተሰጥቶአቸዋል። ሰብአዊ ዘር በማሽቆልቆል (እየከፋ በመሄድ) ላይ ይገኛል።--MH 380 (1905). {1MCP 59.1} 1MCPAmh 50.1

ለበሽታዎች መነሻ 9/10ኛው አእምሮ ነው።--የአእምሮ ሕመም በየቦታው ይታያል። ሰዎች ከሚሰቃዩባቸው በሽታዎች መካከል 9/10ኛው የሚሆኑት መሰረታቸው አእምሮ ውስጥ ነው። ምናልባት ጥቂት የመኖሪያ ቤት ችግር እንደሚመረቅዝ ቁስል ነፍስን እየበላ የሕይወትን ኃይል እያዳካመ ሊሆን ይችላል። ለተፈጸመው ኃጢአት እጅግ ማዘን (መጸጸት) አንዳንድ ጊዜ የአካል አቋምን በማዳከም አእምሮ ሚዛናዊነትን እንዲያጣ ያደርጋል። ለዘላለም እንደሚነድ ገሃነምና መጨረሻ እንደሌለው የኃጢአተኞች ስቃይ ያሉ የስህተት አስተምህሮዎች ደግሞ ለእግዚአብሔር ባሕርይ የተጋነኑና የተዛቡ አመለካከቶችን በመስጠት በቀላሉ ሊነኩ በሚችሉ አእምሮዎች ውስጥ ተመሳሳይ የሆነ ውጤት ያስከትላሉ። --5T 444 (1885). {1MCP 59.2} 1MCPAmh 50.2

አእምሮ በአካል ላይ ተጽእኖ ያሳድራል።---አእምሮና አካል ያላቸው ግንኙነት በጣም የቀረበ ነው። አንዱ ችግር ሲገጥመው ሌላኛውም ችግሩ ይሰማዋል። የአእምሮ ሁኔታ በአካል ክፍሎች ጤና ላይ ተጽእኖ ያሳድራል። ትክክል የሆነ ነገርን ማድረጉን ከመረዳቱና ሌሎች ደስተኛ እንዲሆኑ ከማድረጉ የተነሣ አእምሮ ነጻና ደስተኛ ከሆነ ደም በሰውነት ውስጥ በነጻነት እንዲዘዋወር በማድረግና መላውን አካል በመቃኘት በሁሉም የአካል ክፍሎች ላይ የሚታይ ደስተኛነትን ይፈጥራል። የእግዚአብሔር በረከት ፈዋሽ ኃይል ስለሆነ ሌሎችን በመጥቀም የተትረፈረፉ ሰዎች በልባቸውና በነፍሳቸው ያንን አስደናቂ በረከት ይገነዘባሉ።--CTBH 13, 1890. (CH 28; see also 4T 60, 61 [1876].) {1MCP 59.3} 1MCPAmh 50.3

በደንብ የተመገበና ጤናማ አእምሮ።--አእምሮ የጭንቅላት አካልና መሳሪያ ሲሆን መላውን አካል ይቆጣጠራል። ሌሎቹ የአካል ክፍሎች ሥርዓት ጤናማ እንዲሆን አእምሮ ጤናማ መሆን አለበት። አእምሮ ጤናማ እንዲሆን ደም ንጹህ መሆን አለበት። ትክክለኛ በሆነ የመብላትና የመጠጣት ልምድ ደም ንጹህ ሆኖ መቆየት ይችላል፣ አእምሮ በትክክል ይመገባል።--MS 24, 1900. (MM 291.) {1MCP 60.1} 1MCPAmh 50.4

ግምት የሚያስከትለው ዘላቂ ተጽእኖ።--በሽታ መንስኤ ያለውና ብዙ ጊዜ በሀሳብ እንዲባባስ የሚደረግ ነገር ነው። አንዳንድ ሰዎች ጤናማ እንደሆኑ ቢያስቡ ኖሮ ደህና መሆን ሲችሉ የእድሜ ልክ በሽተኞች የሆኑ አሉ። አንዳንዶች እያንዳንዱ መጠነኛ የሆነ በሽታ ሊያስከትል ለሚችል ነገር መጋለጥ በሽታ ያስከትላል ብለው ስለሚያስቡ የጠበቁት ነገር ስለሆነ መጥፎ ውጤት ይከተላል። ብዙዎች መንስኤው ሙሉ በሙሉ ግምት ከሆነ በሽታ የተነሣ ይሞታሉ። --MH 241 (1905). {1MCP 60.2} 1MCPAmh 51.1

የአእምሮ ኤሌክትሪካዊ ኃይል የአካል ሥርዓት ሕያው እንዲሆን ያደርጋል።--አእምሮ በአካል ላይ ያለው ተጽእኖ እና አካል በአእምሮ ላይ ያለው ተጽእኖ አጽንዖት ሊሰጠው ይገባል። የአእምሮ የኤሌክትሪክ ኃይል፣ በአእምሮ ሥራ ተበረታትቶ፣ መላውን የአካል ሥርዓት ሕያው ስለሚያደርግ በሽታን ለመከላከል ጠቃሚ ነው። ይህ ግልጽ መደረግ አለበት። ጤናን በመጠበቅና በመመለስ ረገድ የፈቃድ ኃይልና ራስን የመቆጣጠር አስፈላጊነት መታየት አለበት፤ ቁጣ፣ አለመርካት፣ ራስ ወዳድነት፣ ወይም ንጽህና ማጣት የሚያስከትሉት ድብርት የማምጣትና አጥፊ ተጽእኖ፣ እና በሌላ በኩል ደስተኛ በመሆን፣ ራስ ወዳድ ባለመሆን፣ በአመስጋኝነት ውስጥ ያለው አስደናቂ የሆነ ሕይወት ሰጭ ኃይልም መታየት አለበት። --Ed 197 (1903). {1MCP 60.3} 1MCPAmh 51.2

አንዳንዶች የፈቃድ ኃይል ስለሌላቸው ይታመማሉ። ባደረግኳቸው ጉዞዎች በአእምሮአቸው ውስጥ ከተፈጠሩ ሀሳቦች የተነሣ በእርግጠኝነት የሚሰቃዩ ሰዎችን አግኝቻለሁ። የአካልና የአእምሮ በሽታን ለመቋቋምና ወደ ላይ ለመነሳት የፈቃድ ኃይል ስለሌላቸው በስቃይ ግዞት ውስጥ ተይዘዋል። . . . {1MCP 61.1} 1MCPAmh 51.3

ብዙ ጊዜ ከእነዚህ ራሳቸውን በሽተኛ ካደረጉ ሰዎች መኝታ አጠገብ ለራሴ እንዲህ ስል እመልሳለሁ፣ ትንሽ በትንሹ እየሞታችሁ ነው፣ ማንም ሳይሆን ራሳችሁ መፈወስ በምትችሉት በሽታ፣ ከስንፍና የተነሣ እየሞታችሁ ነው --HR, Jan, 1871. (MM 106, 107.) {1MCP 61.2} 1MCPAmh 51.4

በጤናማ አካል ውስጥ የጤናማ አእምሮ ጥቅም።--የአእምሮና የግብረገብ ኃይል በአካል ጤና ላይ ይደገፋል። በጤንነት ላይ ጣልቃ የሚገቡ ደስታና ቅንጦት መሰዋት እንዳለባቸው ልጆች መማር አለባቸው። ልጆች ራስን መካድንና ራስን መቆጣጠርን ቢማሩ ኖሮ ደስታንና ከመጠን ያለፈ አለባበስን ፍላጎት እንዲያሟሉ ቢተው ከሚያገኙት ደስታ የበለጠ ደስተኞች ይሆኑ ነበር።. . . {1MCP 61.3} 1MCPAmh 51.5

በቤተሰብ ውስጥ ጥሩ ጤና፣ ጤናማ አእምሮዎችና ንጹህ ልቦች በጠቃሚነታቸው ቅድሚያ አልተሰጣቸውም። ብዙ ወላጆች ልጆቻቸውን ጠቃሚዎች እንዲሆኑና ለሥራ ገጣሚዎች እንዲሆኑ አያስምሩአቸውም። ራስን መካድ የማይቻል ነገር እስኪሆንባቸው ድረስ ይንከባከቡአቸዋል ያቀብጡአቸዋልም። የተሳካ የክርስቲያን ሕይወት እንዲኖር ለማድረግ ጤናማ አእምሮዎችንና ጤናማ አካሎችን ማሳደግ እጅግ በጣም ትልቅ ጠቀሜታ እንዳለው አላስተማሩአቸውም። --RH, Oct 31, 1871. {1MCP 61.4} 1MCPAmh 52.1

በጣም ልጅ እያሉ ያለመጠን ጫና የበዛባቸው ልጆች።--በመማሪያ ክፍል ውስጥ በእርግጠኝነት ለተለያዩ ዓይነት በሽታዎች መሰረት ተጥሏል። ነገር ግን፣ በተለየ ሁኔታ፣ ከአካል ክፍሎች ሁሉ እጅግ በቀላሉ ሊጎዳ የሚችለው አእምሮ ከመጠን ባለፈ ሥራ በቋሚነት ጉዳት ደርሶበታል።…ልጆቻቸው የተሳካላቸው እንዲሆኑ ከፍተኛ ፍላጎት ካላቸው እናቶች የተነሣ የብዙዎች ሕይወት መስዋዕት ሆኗል። ከእነዚህ ልጆች መካከል የዚህን ዓይነት አያያዝ ተቋቁመው ለማለፍ የሚያስችል በቂ የሆነ የአካል አቋም ኃይል ካላቸው ልጆች መካከል የዚህን ውጤት በሕይወታቸው ዘመን ሁሉ የሚሸከሙ እጅግ ብዙዎች አሉ። የአእምሮ የነርቭ ጉልበት እጅግ ስለሚደክም ወደ ብስለት እድሜ ከደረሱ በኋላ ብዙ የአእምሮ ሥራን ለመሸከም የማይቻል ይሆንባቸዋል። አንዳንድ ስስ የሆኑ የአእምሮ ክፍሎች ኃይል የተሟጠጠ ይመስላል። ልጆች ገና ትንሽ እያሉ ያለ እድሜያቸው ወደ ትምህርት ቤት በመላካቸው አደጋ ላይ የወደቀው የአካላቸውና የአእምሮአቸው ጤና ብቻ ሳይሆን ከግብረገብ አንጻርም ክስረት ይገጥማቸዋል። --HL 43, 44, 1865. (2SM 436.) {1MCP 61.5} 1MCPAmh 52.2

አንዳንድ ጊዜ በሽታ ራስን ማዕከል ማድረግን ያስከትላል።--ብዙዎች ትኩረታቸውን ሙሉ በሙሉ ወደ ራሳቸው ከመመለሳቸው የተነሣ በአካል፣ በአእምሮና በግብረገብ በሽተኞች ሆነዋል። በልጆች ጤናማ እንቅስቃሴ፣ ልዩነት በሚያሳዩ አእምሮዎችና እረፍት የለሽ በሆነው ጉልበት እድገት ከሌለበት ሁኔታ ሊድኑ ይችሉ ነበር። --2T 647 (1871). {1MCP 62.1} 1MCPAmh 52.3

ለልጆች የሚደረግ ጥንቃቄ፣ ሀላፊነትና ልምምድ ለቤተሰብ የሚያመጣቸውን ጥቅሞች የሚገነዘቡት በጣም ጥቂት ናቸው።…ልጅ የሌለበት ቤት ምድረ በዳ ነው። በዚያ ቤት ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ልቦች ለራሳቸው ምቾት የሚያመጣ ፍቅርን በመንከባከብና የራሳቸውን ፍላጎቶችና ምቾቶች በማየት ራስ ወዳድ የመሆን አደጋ ውስጥ ናቸው። ስለገጠማቸው መጥፎ ነገር ለራሳቸው ያለ የሌለውን ሀዘኔታ ስለሚሰበስቡ ለሌሎች የሚሰጡት ነገር አይኖራቸውም። ጥገኛ ለሆኑ ልጆች የሚደረግ ጥንቃቄና ፍቅር ከተፈጥሮአችን ሸካራነትን በማስወገድ ገርና ለሌሎች አዛኞች እንድንሆን በማድረግ የባሕርያችንን የከበሩ ነገሮች እንድናሳድግ ተጽእኖ አለው። --2T 647 (1871). {1MCP 62.2} 1MCPAmh 52.4

ድብርት የሚያስከትሉ ስሜቶች ለጤና ጎጂ ናቸው።--በሀዘንና በችግሮች ላይ ትኩረት በማድረግ ከመጨነቅ ይልቅ ደስተኛነትን ማሳደግ የእያንዳንዱ ሰው ተግባር መሆን አለበት። ብዙዎች በዚህ ሁኔታ ራሳቸውን ጎስቋላ ማድረግ ብቻ ሳይሆን ጤንነታቸውንና ደስታቸውን ጤናማ ያልሆነ ሀሳብ በማሰብ መስዋዕት ያደርጋሉ። በዙሪያቸው የማይመቹ ነገሮች ስላሉ በውስጣቸው ያለውን አለመርካት ለማሳየት ቃላት ከሚገልጹት የበለጠ ፊቶቻቸው ቀጣይነት ያለው የመኮሳተር ልብስ ይለብሳሉ። እነዚህ የድብርት ስሜቶች የምግብ መፈጨት ሂደትን በመግታት ሰውነትን በመመገብ ሥራ ውስጥ ጣልቃ ስለሚገቡ ጤንነታቸውን በተመለከተ ትልቅ ጉዳት ያስከትላሉ። ሀዘንና ጭንቀት ለአንዲት ክፋት እንኳን መፍትሄ ባያመጡም ከፍተኛ ጉዳት ማስከተል ግን ይችላሉ፤ ነገር ግን ደስተኛነትና ተስፋ የሌሎችን መንገድ ብሩህ እያደረጉ ‹‹ለሚያገኙአት ሕይወት፣ ለሥጋቸውም ሁሉ ፈውስ ነው›› (ምሳሌ 4፡22)። --ST, Feb 12, 1885. {1MCP 62.3} 1MCPAmh 53.1

በሽተኞችን ስታክሙ አእምሮዎችን አጥኑ።--(ምዕራፍ 42 ‹‹አእምሮና ጤና›› የሚለውን ይመልከቱ)። በሽተኞች ሲታከሙ የአእምሮ ተጽእኖ ውጤት ችላ መባል የለበትም። በትክክል ጥቅም ላይ ከዋለ ይህ ተጽእኖ በሽታን ለመዋጋት እጅግ ውጤታማ ከሆኑ ወኪሎች መካከል አንዱ ይሆናል። --MH 241 (1905). {1MCP 63.1} 1MCPAmh 53.2

የበሽታ መነሻው አእምሮ ነው።--ሰብአዊ ዘርን እያሰቃዩ ካሉ በሽታዎች መካከል አብዛኞቹ መነሻቸው አእምሮ ስለሆነ ሊድኑ የሚችሉት አእምሮን ወደ ጤንነት በመመለስ ብቻ ነው። እኛ ከምናስበው በላይ የአእምሮ ሕመምተኞች የሆኑ እጅግ ብዙ ናቸው። የአእምሮ ችግር የምግብ መፍጫ አካላትን ሽባ የማድረግ ተጽእኖ ስላለው የልብ ሕመም ብዙዎችን ከምግብ አለመፈጨት የተነሣ እንዲሰቃዩ ያደርጋል። --3T 184 (1872). {1MCP 63.2} 1MCPAmh 53.3

ክርስቶስ ይፈውሳል።--ምንም ቅባት ሊደርስበት የማይችል፣ ምንም መድኃኒት ሊፈውሰው የማይችል የነፍስ በሽታ አለ። ለእነዚህ እየጸለያችሁ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ አምጡአቸው። --MS 105, 1898. (WM 71.) {1MCP 63.3} 1MCPAmh 53.4

ከባቢ አየር ጤናንና ብርታትን ይሰጣል።--ከሁሉም ነገር በላይ ወላጆች ልጆቻቸውን በደስተኝነት፣ በደግነትና በፍቅር ከባቢ አየር ይክበቡአቸው። ፍቅር ያለበት እና ይህ ፍቅር በእይታ፣ በቃላትና በተግባር የሚገለጽበት ቤት መላእክት ለመኖር የሚደሰቱበት ቦታ ነው። ወላጆች ሆይ፣ የፍቅር፣ የፈገግታና ደስታ የሚታይበት እርካታ ወደ ልቦቻችሁ ይግባ፣ የዚህ ጣፋጭ ተጽእኖም ቤቱን ይሙላው። የደግነትና የትዕግስተኝነት መንፈስ በማሳየት፣ የቤት ሕይወትን ብሩህ የሚያደርጉ እነዚያን ጸጋዎች በማሳደግ፣ ልጆቻችሁም ተመሳሳይ ባሕርይ እንዲኖራቸው አበረታቱአቸው። በዚህ ሁኔታ የተፈጠረ ከባቢ አየር የልጆችን የአካልና የአእምሮ ጤናና ብርታት ስለሚጨምር አየርና የፀሐይ ብርሐን ለተክሎች ዓለም የሚያስፈልጉትን ያህል ለልጆች አስፈላጊ ነው። --CT 115 (1913). {1MCP 63.4} 1MCPAmh 54.1