አእምሮ፣ባሕርይና ማንነት፣ክፍል 1

8/45

ምዕራፍ 6—ጤናማ የሆነ ትክክለኛነት

የእውነተኛ ደስታ ምንጭ።--ኃይማኖት በብረት በትር እንደሚገዛ እንደ ጨካኝ ገዥ የሆነባቸው የታመመ አስተሳሰብ ያላቸው ግለሰቦች አሉ። እንደ እነዚህ ያሉ ሰዎች ያለማቋረጥ በሕገወጥነታቸው እያዘኑና በሚገምቱት ክፋት እየቃተቱ ናቸው። በልባቸው ፍቅር የለም፤ በፊታቸው ሁል ጊዜ ቁጣ አለ። የዋህነት ያለበት የወጣቶች ወይም የማንኛውም ሰው ሳቅ ያንቀጠቅጣቸዋል። መዝናኛን ወይም መደሰቻን ሁሉ ኃጢአት እንደሆነ ስለሚቆጥሩ ሁል ጊዜ አእምሮ እንደዚህ ላለ ጥብቅና ኃይለኛ ለሆነ ድምጽ መንቀጥቀጥ አለበት ብለው ያስባሉ። ይህ ወደ አንድ ጫፍ የወጣ አስተሳሰብ ነው። {1MCP 48.1} 1MCPAmh 43.1

ሌሎች ደግሞ ጤንነትን ለማግኘት አእምሮ አዳዲስ መደሰቻዎችንና ጊዜ ማሳለፊያ ጨዋታዎችን ለመፈልሰፍ ሁል ጊዜ በሥራ መያዝ አለበት ብለው ያስባሉ። በሚያስደስቱ ነገሮች ላይ መደገፍን ስለሚማሩ ያለ እርሱ ምቾት አይሰማቸውም። እንደ እነዚህ ያሉት እውነተኛ ክርስቲያኖች አይደሉም። ወደ ሌላኛው ጫፍ የሚሄዱ ናቸው። {1MCP 48.2} 1MCPAmh 43.2

እውነተኛዎቹ የክርስትና መርሆዎች በሁሉም ፊት ከፍታውና ጥልቀቱ፣ ርዝመቱና ስፋቱ ሊለካ የማይችለውን የደስታ ምንጭ ይከፍታሉ። ክርስቶስ በእኛ ውስጥ ለዘላለም ሕይወት የሚፈሰው የውኃ ምንጭ ነው። ክርስቲያን በምርጫው የሚጠጣውና በፍጹም የማያልቅ ዘላቂ የሆነ የውኃ ምንጭ ነው። --1T 565, 566 (1867). {1MCP 48.3} 1MCPAmh 43.3

ፈጥኖ የሚጠፋ ቅንዓት።--ተስፋ መቁረጥንና ጭንቀትን ጥሎ የሚያልፈውን ቶሎ የሚጠፋ የአፍታ ቅንዓት የሚያመጣና ታላቅ ፍላጎትን የሚቀሰቅስ መንፈስ ማደፋፈር የለብንም። ለነፍስ ሕይወትን ለመስጠት ከሰማይ የወረደውን የሕይወት እንጀራ እንፈልጋለን። የእግዚአብሔርን ቃል አጥኑ። በስሜታችሁ ቁጥጥር ሥር አትሁኑ። በእግዚአብሔር የወይን ቦታ የሚሰሩ ሁሉ ስሜት እምነት እንዳልሆነ መማር አለባቸው። ሁል ጊዜ በከፍታ ሁኔታ ውስጥ መሆን አያስፈልግም። የእግዚአብሔርን ቃል እንደ ክርስቶስ ሥጋና ደም አድርጎ የሚመለከት ጽኑ እምነት ሊኖረን ይገባል። --Lt 17, 1902. (Ev 138.) {1MCP 49.1} 1MCPAmh 43.4

ቀዝቃዛ የሆነ ትክክለኛ እምነት መያዝም ሆነ ግድየለሽ የሆነ ኃይማኖታዊ ልልነት አስፈላጊ አይደለም።--ተሃድሶ የሚያሳየው እድገት የሚደገፈው መሰረታዊ የሆኑ እውነቶችን በጠራ ሁኔታ በመገንዘብ ላይ ነው። በአንድ ወገን በጠባብ ፍልስፍና እና ጠንካራ በሆነ ቀዝቃዛ ትክክለኛ እምነት በኩል አደጋ ሲያደባ በሌላ በኩል ደግም ግድየለሽነት ያለበት ኃይማኖታዊ ልልነት ትልቅ አደጋ አለው። የሁሉም ዘለቄታ ያለው ተሃድሶ መሰረቱ የእግዚአብሔር ሕግ ነው። ይህን ሕግ የመታዘዝ አስፈላጊነትን ግልጽ በሆኑና በሚታዩ መስመሮች አስምረን ማቅረብ አለብን። መርሆዎቹ በሰዎች ፊት መቅረብ አለባቸው። እንደ እግዚአብሔር ዘላለማዊና የማይቀየሩ ናቸው። -- MH 129 (1905). {1MCP 49.2} 1MCPAmh 43.5

በደንብ ሚዛናዊ የሆኑ አእምሮዎች ይፈለጋሉ።--ትክክለኛ እምነት ሊኖረን እንደሚገባ በመልእክቶች ውስጥ ብዙ ተብሏል። ይህ ጥንቃቄ እንደሚያስፈልግ ሊያስተምረን ይገባል። በልምምዳችን ውስጥ የራሳችንን ዝንባሌዎችና ጠንካራ የሆኑ ባሕርያትን መሸመን የለብንም። ይህ ለከበሩት፣ ከፍ ለሚያደርጉት፣ ለሚያስከብሩት የእውነት መርሆዎች የተሳሳተ መልክ በመስጠት ሌሎችን ወደ ስህተት ይመራል። በእምነት ትክክለኛ ሆኖ መገኘት ብዙዎች ከሚገነዘቡት በላይ ነው። የእግዚአብሔርን ቃል እንዳናጎድፍ በሀሳባችንና በተግባሮቻችን ውስጥ ያለውን እያንዳንዱን ስህተት ማረም ማለት ነው። {1MCP 49.3} 1MCPAmh 44.1

በዚህ ወቅት ሚዛናዊ የሆኑ አእምሮዎች፣ ጤናማ የሆኑና የተሟላ ስብዕና ያላቸው ክርስቲያኖች ይፈለጋሉ። በክርስቶስ እናምናለን ከሚሉ ክርስቲያኖች መካከል ብዙዎቹ ጤናማ ያልሆነ ልምምድ ያላቸው ናቸው። ምቹ ያልሆነውን ማንኛውንም ነገር መሸከም አይችሉም። በማንኛውም መንገድ ቢሆን ሰዎች እንዳቀለሉአቸው ወይም እንደጎዱአቸው ሲያስቡ፣ ወንድሞቻቸው እነርሱ መሆን አለባቸው ብለው እንደሚያስቡት ገር ካልሆኑላቸው ተስፋ ይቆርጣሉ። ታላቁ ሐኪም፣ ገደብ በሌለው ችሎታው፣ ትክክለኛ ወደ ሆነ የግብረገብ ጤና ይመልሳቸዋል፤ ነገር ግን ሕመምተኛው እርሱ የሚያዘውን መድሃኒት መቀበል እምቢ ይላል። እነዚህ ግለሰቦች በጉዳያቸው ውስጥ የእግዚአብሔርን ቃል ለአጭር ጊዜ ይጠቀማሉ፣ ነገር ግን ቃሉን አድራጊዎች አይሆኑም። ብዙም ሳይቆዩ ከተፈጥሮ ፍላጎታቸው ጋር ከሚስማሙ ተጽእኖዎች ሥር ይሆኑና ያገኙትን ሁሉ መልሰው ይቃወሙታል። --RH, July 28, 1896. {1MCP 49.4} 1MCPAmh 44.2

ሁሉም ተፈጥሮአዊ ኃይሎች መልማት አለባቸው።-- ሌሎቹ ችላ ተብለው የተወሰኑ ተፈጥሮአዊ ኃይሎች ጥቅም ላይ ከዋሉ የእግዚአብሔር እቅድ በእኛ በትክክል ሥራ ላይ አልዋለም፤ ይህ የሚሆንበት ምክንያት ሁሉም በአካላችን ውስጥ ያሉ የተፈጥሮ ኃይሎች በከፍተኛ ደረጃ ተጽእኖ የሚፈጥሩና በእርስ በርስ ላይ የሚደገፉ ናቸው። በጥንቃቄ ሚዛንን መጠበቅ እንዲቻል ሁሉም ሥራ ላይ ካልዋሉ በስተቀር አንዱ ብቻ ውጤታማ በሆነ ሁኔታ ሥራ ላይ መዋል አይችልም። ሌሎች ሥራ ላይ ሳይውሉ ለአንዱ ብቻ ትኩትረና ብርታት ከተሰጠ ሁሉም ኃይሎች ስላልለሙ የዚያ እድገት ብቻ ጠንካራ ይሆንና ወደ ጫፍ መውጣትን ያስከትላል። አንዳንድ አእምሮዎች የኮሰሱና በደንብ ሚዛናዊ ያልሆኑ ናቸው። ሁሉም አእምሮዎች በተፈጥሮ በተመሳሳይ ሁኔታ የተቀናጁ አይደሉም። የተለያዩ ዓይነት አእምሮዎች አሉን፤ አንዳንዶች በአንዳንድ ነጥቦች ላይ ጠንካራ ሆነው በሌሎቹ ነጥቦች ላይ በጣም ደካማ ናቸው። በግልጽ የሚታዩ እነዚህ ጉድለቶች መኖር የማያስፈልጋቸውና የሌለባቸው ናቸው። {1MCP 50.1} 1MCPAmh 44.3

እነዚህ ነገሮች ያሏቸው ሰዎች በባሕርያቸው ውስጥ ያሉትን ደካማ ነጥቦች በማረም በሥራ ካጠነከሩ ጠንካራ ይሆናሉ።--3T 33 (1872). {1MCP 50.2} 1MCPAmh 45.1

የአእምሮ ኃይሎችን በሙሉ ጥቅም ላይ አውሏቸው።--ወንዶችና ሴቶች ሚዛናዊ የሆነ አእምሮ እንዲኖራቸው የአእምሮ ኃይሎች በሙሉ ጥቅም ላይ እንዲውሉ መደረግ አለባቸው። ዓለም በአንድ ጎን ብቻ ባደጉ ወንዶችና ሴቶች የተሞላች ነች፤ ለዚህ ምክንያቱ ከአካል ኃይሎቻቸው አንዱ ክፍል ብቻ አድጎ ሌሎቹ ደግሞ ሥራ ካለመስራታቸው የተነሣ ድንኪዬዎች ሆነው ስለቀሩ ነው። {1MCP 50.3} 1MCPAmh 45.2

የብዙ ወጣቶች ትምህርት ያልተሳካ ትምህርት ነው። ለተግባራዊው የስራ ሕይወት የሚያስፈልገውን ነገር ችላ ብለው ያለመጠን ያጠናሉ። ወንዶችና ሴቶች ለኃላፊነታቸው ትክክለኛ የሆነ ትኩረት ሳይሰጡ ወላጆች ይሆኑና በሰብአዊ ዘር የእጦት መለኪያ ሲለኩ ልጆቻቸው ከእነርሱ ይልቅ ወደ ታች ዘቅጠው ይታያሉ። ከዚህ የተነሣ ትውልዱ በፍጥነት እየዘቀጠ ነው። {1MCP 50.4} 1MCPAmh 45.3

አሁን ትምህርት ቤቶች እየተካሄዱ ባሉበት ሁኔታ እየተሰጠ ያለው ትምህርት ወጣቶችን ለተግባራዊ ሕይወት ገጣሚ እያደረጋቸው አይደለም። ሰብአዊ አእምሮ ተግባር ይኖረዋል። በትክክለኛው አቅጣጫ ንቁ ካልሆነ በስህተት ላይ ንቁ ይሆናል። የአእምሮ ሚዛንን ጠብቆ ለማቆየት ሥራና ጥናት በትምህርት ቤቶች ውስጥ አንድነት መፍጠር አለባቸው። --3T 152, 153 (1872). {1MCP 50.5} 1MCPAmh 45.4

የመሻሻያ መንገድ ሁሉም ሊደርሱበት የሚችሉት ነገር ነው።--እግዚአብሔር የሰጣቸውን የአእምሮ ኃይሎች የሚያደንቁና ከፍተኛ ጥንቃቄ በማድረግ የሚያሳድጉ አስተዋይ ወጣቶች ይፈለጋሉ። ሥራ መስራት እነዚህን የአካል ክፍሎች ያሳድጋል፣ ልብን መግራት ችላ ካልተባለ በስተቀር ባሕርይ ሚዛኑን የጠበቀ ይሆናል። የመሻሸያ መንገዶች ሁሉም ሊደርሱባቸው በሚችሉበት ቦታ ናቸው። ስለዚህ ጌታ ፍሬ ፈልጎ ሲመጣ ቅጠልን ብቻ በማቅረብ ማንም እርሱን አያሳዝን። ቁርጠኝነት ያለው ዓላማ በክርስቶስ ጸጋ ሲቀደስ ድንቅ ነገሮችን ያደርጋል። --MS 122, 1899. {1MCP 51.1} 1MCPAmh 45.5

አካል፣ አእምሮ፣ ልብ፣ በእግዚአብሔር ቁጥጥር ሥር።--በእውነት እግዚአብሔርን የሚወድና የሚፈራ ሰው፣ በማያወላውል አእምሮ የእርሱን ፈቃድ ለማድረግ ጥረት በሚያደርግበት ጊዜ አካሉን፣ አእምሮውን፣ ልቡን፣ ነፍሱን፣ እና ብርታቱን በእግዚአብሔር ቁጥጥር ሥር ያደርጋል። ሄኖክ ያደረገው ይህንን ነበር። ከእግዚአብሔር ጋር አካሄዱን አደረገ።…የእግዚአብሔር ፈቃድ የእነርሱ ፈቃድ እንዲሆን ቁርጥ ውሳኔ ያደረጉ ሰዎች በሁሉም ነገር እግዚአብሔርን ማገልገልና ማስደሰት አለባቸው። እንዲህ ሲሆን ባሕርይ የተጣጣመና ሚዛናዊ የሆነ፣ የማይለዋወጥ፣ ደስታ የሚታይበትና እውነተኛ ይሆናል።--Lt 128, 1897. (HP 190.) {1MCP 51.2} 1MCPAmh 46.1

የአእምሮ ኃይላት አካልን መቆጣጠር አለባቸው።--እውነተኛ ትምህርት ሁሉን ያካትታል። ራስን በትክክል መጠቀም እንዳለብን ያስተምራል። የአካል፣ የራስና የልብ ክፍል የሆኑትን አእምሮን፣ አጥንትን፣ ጡንቻን በደንብ መጠቀም እንድንችል ያደርጋል። የአእምሮ ኃይላት ከፍ ያሉ ኃይላት እንደመሆናቸው የአካልን ግዛት ማስተዳደር አለባቸው። ተፈጥሮአዊ የምግብ ፍላጎቶችና ጠንካራ ስሜቶች በሕሊና እና በመንፈሳዊ ፍቅር ቁጥጥር ሥር መሆን አለባቸው። ክርስቶስ የሰብአዊ ዘር ራስ እንደመሆኑ በአገልግሎቱ ውስጥ ከፍ ወዳለውና ወደ ንጹህና ቅዱስ መንገዶች መምራት ዓላማው ነው። የእርሱ ጸጋ በሚፈጽመው አስደናቂ ሥራ በእርሱ ፍጹማን መሆን እንችላለን።--MH 398, 399 (1905). {1MCP 51.3} 1MCPAmh 46.2

በደንብ ያደጉ አእምሮዎችና ሰፊ ባሕርያት።--የእግዚአብሔር ሰራተኞች በሁሉም አቅጣጫ የተሟሉ ለመሆን መሥራት አለባቸው፤ ይህ ማለት የባሕርይ ስፋት ያላቸው፣ ባለ አንድ አሳብ ብቻ ያልሆኑ፣ በአንድ የስራ ዓይነት ብቻ ያልተቃኙ መሆን አለባቸው፤ በአጣብቂኝ መስመር ውስጥ በመግባታቸው ቃላቶቻቸውና ለእውነት ያላቸው ጥብቅና አብረዋቸው ከሚኖሩ ሰዎች መደብና ከሚገጥሙአቸው ሁኔታዎች ጋር የተለያየ ዓይነት መሆን እንዳለበት ማየትና መገንዘብ የማይችሉ መሆን የለባቸውም። ሁሉም በደንብ ያደገ አእምሮ እንዲኖራቸውና ሚዛናዊ ያልሆኑ ባሕርያትን ለማሸነፍ ያለማቋረጥ የሚሹ መሆን አለባቸው። ጠቃሚና የተከናወነልህ ሰራተኛ መሆን ከፈለግክ ይህ የሁል ጊዜ ጥናትህ መሆን አለበት። --Lt 12, 1887. (Ev 106.) {1MCP 52.1} 1MCPAmh 46.3

ተራ የሆኑ፣ የማይረቡ ነገሮች አእምሮን ያቀጭጫሉ (ድንክዬ ያደርጋሉ)፡--አእምሮ የመለኮታዊ መገለጥን እውነቶች ለመረዳት ካልተማረና ልብ የክርስቶስን ወንጌል ካልተቀበለ በስተቀር ትምህርት ውጤታማ አይደለም የሚለው አሳብ በእያንዳንዱ ተማሪ አእምሮ ውስጥ መቀረጽ አለበት። ሰፊ በሆኑ የእግዚአብሔር ቃል መርሆዎች ቦታ ተራ ሀሳቦችን የሚቀበልና ጊዜና ትኩረት ተራ በሆኑና በማይረቡ ነገሮች እንዲያዙ የሚያደርግ ተማሪ አእምሮው ቀጭጮና ደካማ ሆኖ ያገኘዋል። የእድገትን ኃይል አጥቷል። አእምሮ ስለ ዘላለማዊ ሕይወት የሚመለከቱ ነገሮችን ለማስተዋል መሰልጠን አለበት። --RH, Nov 11, 1909.(FE 536.) {1MCP 52.2} 1MCPAmh 46.4

አእምሮዎች በማይጠቅሙ ነገሮች መጨናነቅ የለባቸውም።--በዛሬዎቹ ትምህርት ቤቶች ውስጥ [1897] እየተካሄደ ያለው ትምህርት ወደ አንድ ወገን ያጋደለ መሆኑ ስህተት ነው። በእግዚአብሔር ልጅ የተገዛን እንደመሆናችን የእርሱ ንብረት ስለሆንን እያንዳንዱ ሰው በክርስቶስ ትምህርት ቤት ውስጥ መማር አለበት። ለትምህርት ቤቶቻችን ጠቢባን መምህራን መመረጥ አለባቸው። መምህራን የሚሰሩት ከሰብአዊ አእምሮዎች ጋር ስለሆነ በእነዚህ አእምሮች ውስጥ ክርስቶስ የግል አዳኛቸው መሆኑን የማወቅን አስፈላጊነት እንዲያሰርጹ እግዚአብሔር ሀላፊነት ሰጥቶአቸዋል። ነገር ግን ማንም ሰው ቢሆን ራሱ በክርስቶስ ትምህርት ቤት ውስጥ እንዴት ማስተማር እንዳለበት ካልተማረ በስተቀር እግዚአብሔር ለራሱ የገዛውን ርስት በእውነት ማስተማር አይችልም።{1MCP 52.3} 1MCPAmh 47.1

እግዚአብሔር ከሰጠኝ ብርሃን ልነግራችሁ ግድ ይለኛል፣ ተማሪዎች እንደ ገለባ የሆነ እውቀትን ለማግኘት ብዙ ጊዜንና ገንዘብን እንደሚያባክኑ አውቃለሁ፤ እነዚህ ተማሪዎች ያገኙት ትምህርት እንደ እነርሱ ያሉ ሰዎች በላይኛው ትምህርት ቤት ከቅዱሳንና ከመላእክት ጋር አንድነት ለመፍጠር ገጣሚ የሚያደርጋቸውን ባሕርይ እንዲመሰርቱ ለመርዳት አያስችላቸውም። አብዛኛውን ጊዜ የወጣቶችን አእምሮ በማይጠቅሟቸውና ጣዕም በሌላቸው ነገሮች ክምችት ከማጨናነቅ ይልቅ ተግባራዊ እውቀት ሊሰጣቸው ይገባል። የማይጠቅም እውቀትን በማግኘት ጊዜና ገንዘብ ይባክናል። አእምሮ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶችን እንዲያውቅ በጥንቃቄና በጥበብ መማር አለበት። የትምህርት ዋናው ዓላማ መሆን ያለበት በፍጥረትም ሆነ በድነት የእርሱ የሆንነውን እግዚአብሔርን እንዴት እንደምናከብር እውቀት ማግኘት መሆን አለበት። የትምህርት ውጤት መሆን ያለበት የእግዚአብሔርን ድምጽ እንድንረዳ ማስቻል ነው። . . . {1MCP 52.4} 1MCPAmh 47.2

የእግዚአብሔር ቃል፣ በእውነተኛው የወይን ግንድ ላይ እንዳሉት ቅርንጫፎች፣ በልዩነት ውስጥ አንድነትን ያቀርባል። በእርሱ ውስጥ ፍጹም፣ ከሰብአዊ አቅም በላይ የሆነ፣ ምስጢራዊ አንድነት አለ። የእውነተኛ ትምህርት መሰረት የሆነውን መለኮታዊ ጥበብ ይዟል፤ ነገር ግን ይህ መጽሐፍ በግድ የለሽነት ተወስዷል።{1MCP 53.1} 1MCPAmh 47.3

አሁን፣ ከመቼውም ጊዜ ይልቅ፣ እውነተኛውን የትምህርት ሳይንስ ማወቅ አለብን። ይህን ማስተዋል ካልቻልን በእግዚአብሔር መንግስት በፍጹም ቦታ አይኖረንም። ‹‹እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት›› (ዮሐ. 17፡3)። ይህ ሰማይ የሚሰጠው ዋጋ ከሆነ ትምህርታችን በእነዚህ መስመሮች መካሄድ አይችልምን? --Christian Educator, Aug, 1897. {1MCP 53.2} 1MCPAmh 47.4

ለሌሎች የሚከብዱ ሕጎችን ማውጣት እግዚአብሔር እንዳይከበር ያደርጋል። ሰው በትንሹም ቢሆን መሰሎቹን እንዲገዛ ወይም እንዲጨቁን የሚያደርገውን ማንኛውንም መሳሪያ ትክክለኛነት እግዚአብሔር አያረጋግጥም። ሰው ሌሎችን ለመግዛት የጭካኔ ሕግ ማዘጋጀት ሲጀምር በዚያኑ ጊዜ እግዚአብሔርን በማዋረድ የራሱንና የወንድሞቹን ነፍስ አደጋ ውስጥ ይጥላል። --7T 181 (1902). {1MCP 53.3} 1MCPAmh 48.1

የማይመሳሰሉ አእምሮዎች ሚዛን አስፈላጊ ነው።--አሁን አብረን ያለነው የተለያዩ አአምሮዎች፣ የተለያየ ትምህርት እና የተለያየ ስልጠና ያለን ሰዎች እንደመሆናችን ሁሉም አእምሮ በአንድ መስመር በትክክል ይሄዳል ብለን አንጠብቅም፤ ነገር ግን መጠየቅ ያለብን በእውነት የወይን ግንድ ላይ የተጣበቅን(የተከተብን) ብዙ ቅርንጫፎች ነን ወይ የሚለውን ጥያቄ ነው። መጠየቅ የምንፈልገው ይህን ጥያቄ ነው፣ ተማሪዎችንም መምህራንንም መጠየቅ እንፈልጋለን። በርግጥ በዋናው የወይን ግንድ ላይ መጣበቅ አለመጣበቃችንን ማወቅ እንፈልጋለን። ተጣብቀን ከሆነ የተለያዩ ባሕርያት፣ የተለያዩ ቅኝቶችና የተለያዩ ድምጾች ሊኖሩን ይችላሉ። ነገሮችን በአንድ አቅጣጫ ላናይ እንችላለን፣ ከቅዱሳት መጽሐፍት የተወሰዱ ጥቅሶችን በተመለከተ እርስ በርሳችን የተለያዩ ሀሳቦች አሉን፤ ይህ የሚሆነው ጥቅሶቹን በመቃረን ሳይሆን ሀሳቦቻችን ሊለያዩ ስለሚችሉ ነው። የእኔ አእምሮ በአብዛኛው በሚያውቀው መስመር ሊሄድ ሲችል ሌላኛው ሰው ደግሞ በራሱ ባሕርያት ተመስርቶ እያሰበና የራሱን አመለካከት ሊይዝ ስለሚችል በአንድ ወገን ሌሎች ያላዩትን እጅግ ጥልቅ የሆነ ነገር ሊያይ ይችላል። --MS 14, 1894. {1MCP 53.4} 1MCPAmh 48.2

ሒሶጵ፣ ጥድና ዘንባባ።--እግዚአብሔር ነገሮችን አስተካክሎ ካስቀመጠባቸው አቀማመጦች ሁሉ ለወንዶችና ለሴቶች የተለያዩ ዓይነት ስጦታዎችን ለመስጠት ካለው እቅድ የበለጠ ውብ የሆነ ነገር የለም። ቤተ ክርስቲያን በተለያዩ ዓይነት ዛፎች፣ እጽዋትና አበቦች ያጌጠች የእርሱ የአትክልት ቦታ ነች። ሒሶጵ የጥድን ያህል እንዲሆን አይጠብቅም፣ የወይራ ዛፍም ግዙፍ የሆነውን የዘንባባ ዛፍ ከፍታ እንዲደርስ አይጠበቅበትም። ብዙዎች ውስን የሆነ ኃይማኖታዊና አእምሮአዊ ስልጠና ወስደዋል፣ ነገር ግን እነዚህ ሰዎች ራሳቸውን በማዋረድና በእግዚአብሔር በመታመን የሚሰሩ ከሆነ እግዚአብሔር ለእነርሱ ያዘጋጀላቸው ሥራ አለ። --Lt 122, 1902. (Ev 98, 99). {1MCP 54.1} 1MCPAmh 48.3

የሰዎች ባሕርያት እንደ አበቦች መልክ የተለያዩ ናቸው።--ቆጥረን ልንዘልቃቸው ከማንችላቸው የተለያዩ ዓይነት እጽዋትና አበቦች ጠቃሚ የሆነ ትምህርት መማር እንችላለን። ሁሉም አበቦች በቅርጽም ሆነ በቀለም አንድ ዓይነት አይደሉም። አንዳንዶች የመፈወስ ባሕርይ አላቸው። አንዳንዶች ሁል ጊዜ መልካም መዓዛ አላቸው። አንዳንድ ክርስቲያን ነን ባዮች እያንዳንዱን ክርስቲያን እንደ እነርሱ እንዲሆን ማድረግ ሥራቸው እንደሆነ ያስባሉ። ይህ የሰው እቅድ እንጂ የእግዚአብሔር እቅድ አይደለም። ልክ በአትክልት ቦታ ውስጥ እንዳሉ አበቦች በእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለተለያዩ ዓይነት ባሕርያት ቦታ አለ። በእርሱ መንፈሳዊ የአትክልት ቦታ ውስጥ ብዙ የተለያዩ ዓይነት አበቦች አሉ።--Lt 95, 1902. (Ev 99.) {1MCP 54.2} 1MCPAmh 49.1

የአእምሮና የአካል ኃይላት--የእግዚአብሔር ሥጦታ።--እግዚአብሔር እንድናደርግ የሚጠይቃቸው ነገሮች ወደ ሕሊና መምጣት አለባቸው። ወንዶችና ሴቶች ራስን ለማሸነፍ፣ ንጽህናን ለመፈለግ፣ ከእያንዳንዱ አዋራጅ የምግብ ፍላጎትና ከሚያረክስ ልምድ ነጻ የመውጣት ሥራ ለመሥራት መንቃት አለባቸው። ሁሉም የአካልና የአእምሮ ኃይላት የእግዚአብሔር ሥጦታ ስለሆኑ ለእርሱ አገልግሎት በተቻለ መጠን በጥሩ ሁኔታ መጠበቅ እንዳለባቸው የሚገልጸው እውነታ ልባቸውን መንካት አለበት። --MH 130 (1905). {1MCP 54.3} 1MCPAmh 49.2

እግዚአብሔር የተስተካከሉ ባሕርያትን ይፈልጋል።--እግዚአብሔር ሰዎችን የሚዘልፋቸው ስለሚወዳቸው ነው። በእርሱ ብርታት ብርቱ እንዲሆኑ፣ ሚዛናዊ የሆኑ አእምሮዎችና የተስተካከሉ ባሕርያት እንዲኖሩአቸው ይፈልጋል፤ እንዲህ ሲሆን በቃልና በሕይወት ምሳሌነት ወደ ሰማይ እንዲጠጉ በመምራት ለእግዚአብሔር መንጋ ምሳሌ ይሆናሉ። --MS 1, 1883. (1SM 48.) {1MCP 55.1} 1MCPAmh 49.3