አእምሮ፣ባሕርይና ማንነት፣ክፍል 1
ምዕራፍ 27—የእግዚአብሔር ፍቅር
እግዚአብሔር ፍቅር ነው።--‹‹እግዚአብሔር ፍቅር ነው›› (1ኛ ዮሐንስ 4፡ 16)። የእርሱ ተፈጥሮ፣ ሕጉም ፍቅር ነው። ከዚህ በፊት ነበር፤ ወደፊትም ይኖራል። ‹‹ለዘላለም የሚኖር ስሙም ቅዱስ የሆነ፣ ከፍ ያለው ልዑል›› (ኢሳ. 57፡ 15)፣ ‹‹መንገዱ ከዘላለም የሆነ›› (ዕንባቆም 3፡ 6) እርሱ አይለወጥም። በእርሱ ዘንድ ‹‹መለወጥ ወይም በመዞር የተደረገ ጥላ›› የለም (ያዕቆብ 1፡ 17)። {1MCP 247.1} 1MCPAmh 204.1
እያንዳንዱ የመፍጠር ኃይል መገለጥ የዘላለማዊው ፍቅር መግለጫ ነው። የእግዚአብሔር ሉአላዊነት ለተፈጠሩ ፍጡራን ሁሉ የበረከት ሙላትን ያካትታል። . . . {1MCP 247.2} 1MCPAmh 204.2
በክፉና በመልካም መካካል ያለው ተጋድሎ ታሪክ፣ በመጀመሪያ በሰማይ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በመጨረሻ አመጽ እስከሚገረሰስበትና ኃጢአት ሙሉ በሙሉ እስከሚጠፋበት ጊዜ ድረስ፣ የእግዚአብሔር የማይለወጥ ፍቅር ማሳያ ነው። -- PP 33 (1890). {1MCP 247.3} 1MCPAmh 204.3
የእግዚአብሔር ፍቅር በተፈጥሮ ውስጥ ታይቷል።--ተፈጥሮና ራዕይ በተመሳሳይ ሁኔታ የእግዚአብሔርን ፍቅር ይመሰክራል። በሰማይ ያለው አባታችን የሕይወት፣ የጥበብና የደስታ ምንጭ ነው። የተፈጥሮን ድንቅና ውብ ነገሮች ተመልከቱ። ለሰው ፍላጎትና ደስታ ብቻ ሳይሆን ለፍጡራን ሁሉ ፍላጎትና ደስታ ለመስጠት ስላላቸው አስደናቂ ምቹነት አስቡ። ምድርን፣ ኮረብታዎችን፣ ባህርንና ሜዳዎችን የሚያስደስቱና የሚያድሱ የፀሐይ ብርሃንና ዝናብ በሙሉ ስለ ፈጣሪ ፍቅር ይናገራሉ።ፍጥረታቱ ሁሉ በየዕለቱ የሚያስፈልጋቸውን ነገር የሚሰጥ እግዚአብሔር ነው።. . . {1MCP 247.4} 1MCPAmh 204.4
‹‹እግዚአብሔር ፍቅር ነው›› የሚለው አረፍተ ነገር በእያንዳንዱ እንቡጥ፣ በእያንዳንዱ በሚበቅል ሳር ጫፍ ላይ ተጽፎአል። በደስታ ዝማሬያቸው አየሩ እንዲያስተጋባ የሚያደርጉ ደስ የሚሉ ወፎች፣ በፍጽምናቸው አየሩን በመልካም መዓዛ የሚሞሉ የተለያየ ውብ ቀለም ያላቸው አበባዎች፣ ሕያው አረንጓዴነትን የተላበሱ ቅጠሎች ያሉአቸው በደን ውስጥ ያሉ ግዙፋን ዛፎች--ሁሉም ስለ አምላካችን መልካም አባታዊ ጥንቃቄና ልጆቹን ደስተኛ ለማድረግ ስላለው ፍላጎት ይመሰክራሉ። --SC 9, 10 (1892). {1MCP 248.1} 1MCPAmh 204.5
በፍቅር መርህ ላይ የተመሰረቱ ትዕዛዛት።--በአስርቱ ትዕዛዛት ውስጥ ያሉት ቃላት ለሁሉም ሰብአዊ ዘር ተስማሚ ሲሆኑ ሁሉንም ለማስተማርና ለማስተዳደር የተሰጡ ናቸው። ሳይንዛዙ የተገለጹ፣ ሁሉንም ያካተቱና ሥልጣን ያላቸው አስርቱ ትዕዛዛት ሰው ለእግዚአብሔርና ለባልንጀሮቹ ያለበትን ሀላፊነት የሚሸፍኑ ናቸው፤ ሁሉም መሰረታዊ በሆነው በታላቁ የፍቅር መርህ ላይ የተመሰረቱ ናቸው።--PP 305 (1890). {1MCP 248.2} 1MCPAmh 204.6
ኢየሱስና ርኅራኄ ያለበት የፍቅር ሕግ።--የእግዚአብሔር ሕግ በባሕሪዩ የማይለወጥ ስለሆነ ክርስቶስ በወደቀው ሰው ፈንታ ራሱን መስዋዕት አድርጎ ሰጠ፣ አዳምም ኤደንን በማጣት ከዝርያው ሁሉ ጋር በአመክሮ ውስጥ ገባ። {1MCP 248.3} 1MCPAmh 205.1
ሰይጣን ከሰማይ ከተጣለ በኋላ ከእግዚአብሔር ሕግ አንዲቷ እንኳን ተሽራ ቢሆን ኖሮ ከመውደቁ በፊት በሰማይ ማግኘት ያልቻለውን ነገር ከውድቀቱ በኋላ በምድር ላይ ያገኝ ነበር። የጠየቀውን ሁሉ መቀበል ይችል ነበር። ይህን እንዳላደረገ እናውቃለን…። ሕግ እንደ እግዚአብሔር ዙፋን የማይለወጥ ስለሆነ የእያንዳንዱ ነፍስ መዳን የሚወሰነው በመታዘዝ ወይም ባለመታዘዝ ነው። . . . {1MCP 248.4} 1MCPAmh 205.2
ኢየሱስ ርኅራኄ ባለበት የፍቅር ሕግ ኃጢአታችንን ተሸከመ፣ ቅጣታችንን ወሰደ፣ ለሕግ ተላላፊ የተመደበውን የእግዚአብሔርን ቁጣ ጽዋ ጠጣ…። እኛ ሕይወት፣ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረን ስለ እኛ ራስን የመካድንና መስዋዕት የማድረግን መስቀል ተሸከመ። እኛስ ለክርስቶስ መስቀል እንሸከምለታለን? --Lt 110, 1896. (KH 289.) {1MCP 248.5} 1MCPAmh 205.3
ስሜት ያለው፣ የክርስቶስ የፍቅር ተፈጥሮ።--ሕይወቱ፣ ከጅምር እስከ ፍጻሜው፣ ራስን የመካድና መስዋዕት የማድረግ ነበር። መላው ዓለም ከፈለገ ድነትን ያገኝ ዘንድ በቀራኒዮ መስቀል ላይ ራሱን ታላቅ መስዋዕት አድርጎ ሰጠ። ክርስቶስ በእግዚአብሔር ውስጥ ተደብቆ እግዚአብሔር በልጁ ባሕርይ ውስጥ ለዓለም ተገለጠ።. . . {1MCP 249.1} 1MCPAmh 205.4
ለጠፋው ዓለም ያለው ፍቅር በየቀኑ፣ በሕይወቱ በእያንዳንዱ ተግባር ተገለጠ። የእርሱን መንፈስ የተሞሉ ሰዎች ክርስቶስ በውስጣቸው በሰራባቸው ሰዎች መስመር ይሰራሉ። የእግዚአብሔር ብርሃንና ፍቅር በክርስቶስ በሰብአዊ ተፈጥሮ ተገልጠው ነበር። አንድም ሰብአዊ ፍጡር ሰብአዊነት መለኮታዊ ተፈጥሮን በመካፈል ስለሚሆነው ነገር ራስና ተወካይ ሆኖ የቆመው፣ ኃጢአት የሌለበት፣ የእግዚአብሔር ቅዱስ የነበረውን ዓይነት ስሜት ያለው ተፈጥሮ በፍጹም አልነበረውም።--YI, Aug 16, 1894. (KH 288.) {1MCP 249.2} 1MCPAmh 205.5
የእግዚአብሔር ፍቅር ሕያው ምንጭ።--የእግዚአብሔር ፍቅር ዝም ብሎ አሉታዊ ከሆነ ነገር በላይ ነው፤ አዎንታዊ የሆነና የሚሰራ መርህ፣ ሌሎችን ለመባረክ ሁል ጊዜ የሚፈስ ሕያው ምንጭ ነው። የክርስቶስ ፍቅር በእኛ ካደረ እንደ እኛ ላሉ ሰዎች ጥላቻን የማናሳይ ብቻ ሳንሆን በእያንዳንዱ መንገድ ለእነርሱ ፍቅር ለማሳየት የምንፈልግ እንሆናለን።--MB 58 (1896). {1MCP 249.3} 1MCPAmh 205.6
ዩኒቨርስ የእግዚአብሔርን ፍቅር ይገልጻል።--ሰማያዊው አባት ለዓለማችን የሰጠውን ክቡር ስጦታ እያንዳንዱ ሰው ምነው መገመት በቻለ። ደቀ መዛሙርት የክርስቶስን ፍቅር መግለጽ እንዳልቻሉ ተሰምቶአቸው ነበር። ‹‹ፍቅርም እንደዚህ ነው›› ብቻ ማለት ችለዋል። መላው ዩኒቨርስ ይህን ፍቅርና የእግዚአብሔርን ገደብ የለሽ ለጋስነት ይገልጻል። {1MCP 249.4} 1MCPAmh 206.1
እግዚአብሔር ዓለምን ለመኮነን ልጁን መላክ ይችል ነበር። ነገር ግን አስደናቂ ጸጋ! ክርስቶስ ለማጥፋት ሳይሆን ለማዳን መጣ። ሐዋርያት አቻ በሌለው የአዳኝ ፍቅር ልባቸው ሳይሞቅ ይህን ዋና ሀሳብ በፍጹም አልነኩትም። ሐዋርያው ዮሐንስ የሚሰማውን ስሜት ለመግለጽ ቃላት ማግኘት አልቻለም ነበር። እንዲህ በማለት ነበር በቃለ አጋኖ የተናገረው፣ ‹‹የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን እንድንጠራ አብ እንዴት ያለ ፍቅር እንደሰጠን ተመልከቱ፡- ስለዚህ ዓለም እርሱን ስላላወቀ እኛንም አያውቀንም›› (1 ዮሐንስ 3፡ 1)። አብ ምን ያህል እንደወደደን በፍጹም ልናሰላ አንችልም። ልናወዳድር የምንችልበት መስፈርት የለም።--Lt 27, 1901. {1MCP 249.5} 1MCPAmh 206.2
ጨካኝና ጥብቅ የሆነ አምላክን ጽንሰ ሀሳብ ለማምጣት ኃላፊነት የሚወስደው ሰይጣን ነው።--ሰዎች በፍትህ አሰጣጥ ላይ እጅግ ጥብቅ መሆን የእግዚአብሔር ዋና ባሕሪይ እንደሆነ አድርገው እንዲያስቡ ሰይጣን መራቸው--ኃይለኛ ዳኛ፣ ጨካኝና ርኅራኄ የሌለው አበዳሪ እንደሆነ እንዲያስቡ መራቸው። በሰዎች አእምሮ ስለ ፈጣሪ የሳለው ስዕል ፍርድ ለማምጣት ስህተቶችንና ጉድለቶችን ለማግኘት ቅናት በተሞላ ዓይኖች የሚመለከት ፍጡር እንደሆነ የሚያሳይ ነው። ኢየሱስ በሰዎች መካከል ለመኖር የመጣው የእግዚአብሔርን መጨረሻ የሌለው ፍቅር ለዓለም በማሳየት ይህን ጥቁር ጥላ ለመግፈፍ ነበር።--SC 11 (1892). {1MCP 250.1} 1MCPAmh 206.3
በአባትና በልጅ መካከል ያለው ፍቅር ምሳሌ ነው።--እረኛ በጎቹን እጅግ ቢወዳቸውም ወንድና ሴት ልጆቹን ከእነርሱ አብልጦ ይወዳል። ኢየሱስ እረኛችን ብቻ አይደለም፤ ‹‹የዘላለም አባታችንም›› ነው። እንዲህ ይለናል፡- ‹‹አብ እንደሚያውቀኝ እኔም አብን እንደማውቀው የራሴን በጎች አውቃለሁ የራሴም በጎች ያውቁኛል›› (ዮሐ. 10፡ 14)። ይህ እንዴት ያለ መግለጫ ነው!--በአባቱ እቅፍ ያለው አንድያ ልጅ፣ እግዚአብሔር ‹‹ወዳጄ›› (ዘካ. 13፡ 7) ብሎ የተናገረለት--በእርሱና በዘላለማዊ አምላክ መካከል ያለው ግንኙነት በክርስቶስና በምድር ላይ ባሉ ልጆቹ መካከል ያለውን ግንኙነት እንዲወክል ተደርጓል!--DA 483 (1898). {1MCP 250.2} 1MCPAmh 206.4
እግዚአብሔር የክርስቶስን ተከታዮች የሚወደው አንድያ ልጁን እንደሚወድ ነው።--MS 67, 1894. {1MCP 250.3} 1MCPAmh 207.1
የክርስቶስ ፍቅር ብርታት የሚሰጥ፣ ፈዋሽ ኃይል ነው።--ክርስቶስ በመላው አካል ውስጥ ሰርጾ እንዲገባ የሚያደርገው ፍቅር ብርታት የሚሰጥ ኃይል ነው። እያንዳንዱን አስፈላጊ የሆነ ክፍል--አእምሮን፣ ልብን፣ ነርቮችን-- በፈውስ ይነካል። በእርሱ የሰዎች ከፍተኛ የሆኑ ኃይሎች ለሥራ ይነሳሳሉ። ነፍስን የሕይወት ኃይሎችን ከሚጨፈልቁ ከበደለኛነት ስሜትና ከሀዘን፣ ከስጋትና ከጭንቀት፣ ነጻ ያወጣል። ከእርሱ ጋር የመንፈስ እርካታና እርጋታ ይመጣል። ማንኛውም ምድራዊ የሆነ ነገር ሊያጠፋው የማይችለውን ደስታ በነፍስ ውስጥ ይተክላል--በመንፈስ ቅዱስ መደሰት--ጤናና ሕይወት ሰጭ ደስታ ይፈጥራል። --MH 115 (1905). {1MCP 250.4} 1MCPAmh 207.2
የእግዚአብሔርን ፍቅር መገምገም (መቃኘት)።--እግዚአብሔር ስላቀረበልን ብሩህ ምናባዊ ስዕሎች እናመስግነው። ሁል ጊዜ ልንመለከታቸው እንድንችል የእርሱን የተባረኩ የፍቅር ዋስትናዎች አንድ ላይ እንመድባቸው፡- የእግዚአብሔር ልጅ ሰውን ከሰይጣን ኃይል ለማዳን የአባቱን ዙፋን ትቶ መለኮታዊነትን በሰብአዊነት መሸፈኑን፤ በእኛ ፋንታ ድል ማድረጉን፣ ሰማይን ለሰዎች ክፍት ማድረጉን፣ መለኮት ክብሩን የሚገልጥበትን ክፍል ለሰብአዊ ዕይታ መግለጡን፤ የወደቀው ዘር በኃጢአት ከተዘፈቀበት ከጥፋት ጉድጓድ መውጣቱንና ዘላለማዊ ከሆነው አምላክ ጋር እንደገና ግንኙነት መፍጠሩን፣ በአዳኛችን ባለው እምነት አማካይነት መለኮታዊ ፈተናን ማለፉን፣ የክርስቶስን ጽድቅ መልበሱንና ወደ ዙፋኑ ከፍ ማለቱን--እግዚአብሔር እንድናሰላስልባቸው የሚፈልግብን ምናባዊ ስዕሎች እነዚህ ናቸው። --SC 118 (1892). {1MCP 251.1} 1MCPAmh 207.3
ፍቅር የእኛን ሰማይ ይሰራል።--የእኛን ሰማይ የሚሰራው የክርስቶስ ፍቅር ነው። ነገር ግን ስለዚህ ፍቅር ለመናገር ስንፈልግ ቋንቋ ያጥረናል። በምድር ላይ ስለነበረው ሕይወቱ፣ ለእኛ ስለፈጸመው መስዋዕትነት እናስባለን፤ በሰማይ የእኛ ጠበቃ ሆኖ ስለሚሰራው ሥራ፣ እርሱን ለሚወዱት እያዘጋጀ ስላለው ቤቶች እናስባለን፤ ከዚህ የተነሣ ‹‹ኦ፣ የክርስቶስ ፍቅር ከፍታና ጥልቀት!›› በማለት በአድናቆት እንናገራለን። ከመስቀሉ ስር ስንቆይ ስለ እግዚአብሔር ፍቅር ጥቂት ሀሳብ ስለምናገኝ ‹‹ፍቅርም እንደዚህ ነው፣ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን፣ ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም›› እንላለን (1 ዮሐንስ 4፡ 10)። ነገር ግን ስለ ክርስቶስ በምናሰላስልበት ጊዜ ሊለካ በማይቻል ፍቅር ጠርዝ አካባቢ ላይ ብቻ እየቆየን ነን። የእርሱ የፍቅር ጥልቀት መጨረሻ ወይም ዳር እንደሌለው ሰፊ ውቅያኖስ ነው። --RH, May 6, 1902. {1MCP 251.2} 1MCPAmh 207.4
የእግዚአብሔር ፍቅር ሊለካ የማይችልና የማያልቅ ነው።--የሰብአዊ ልብን መስመር ተከትሎ ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተላለፈ የመጣው የወላጅ ፍቅር፣ በሰዎች ነፍስ ውስጥ የተከፈቱ የገርነት ምንጮች ሁሉ፣ ሊለካ ከማይችለውና ከማያልቀው የእግዚአብሔር ፍቅር ጋር ሲነጻጸሩ፣ ትንሽ ምንጭን ገደብ ከሌለው ውቅያኖስ ጋር እንደማነጻጸር ነው። አንደበት ሊናገረው አይችልም፤ ብዕር ሊገልጸው አይችልም። በሕይወትህ ዘመን ሁሉ በየቀኑ ልታሰላስለው ትችላለህ፤ ለመረዳት ቅዱሳት መጻሕፍትን በትጋት ልትመረምር ትችላለህ፤ የሰማያዊ አባትን ፍቅርና ርኅራኄ ለመገንዘብ በምታደርገው ጥረት እግዚአብሔር የሰጠህን እያንዳንዱን ኃይልና ችሎታ ልታሰባስብ ትችላለህ፤ ነገር ግን ከዚህ ባሻገር ማብቂያ የሌለው ነገር አለ። ያንን ፍቅር ለዘመናት ልታጠኑት ትችላላችሁ፤ ሆኖም እግዚአብሔር ለዓለም እንዲሞት ልጁን በመስጠት የገለጸውን ፍቅር ርዝመትና ስፋት፣ ጥልቀትና ከፍታ በፍጹም በሙላት መረዳት አትችሉም። ዘላለም ራሱ በፍጹም በሙላት ሊገልጸው አይችልም። ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስን ስናጠና እና በክርስቶስ ሕይወትና በድነት ዕቅድ ላይ ስናሰላስል እነዚህ ታላላቅ ርዕሰ ጉዳዮች ለግንዛቤያችን የበለጠውን ክፍት ይሆናሉ።--5T 740 (1889). {1MCP 251.3} 1MCPAmh 208.1
የእግዚአብሔር ፍቅር ቀስ በቀስ እየጨመረ የሚሄድ ነው።--የዘላለም አመታት እያለፉ ሲሄዱ፣ ስለ እግዚአብሔርና ስለ ክርስቶስ የበለጸጉና አሁንም የበለጠውን በግርማ የተሞሉ መገለጦችን ያመጣሉ። እውቀት ቀስ በቀስ የሚጨምር እንደሆነ ሁሉ ፍቅር፣ አምልኮና ደስታም እየጨመሩ ይሄዳሉ። ሰዎች ስለ እግዚአብሔር አብልጠው በተማሩ ቁጥር የእርሱን ባሕርይ አብልጠው ያደንቁታል። --GC 678 (1911). {1MCP 252.1} 1MCPAmh 208.2