አእምሮ፣ባሕርይና ማንነት፣ክፍል 1
(ሀ) አዎንታዊው (የልዩ ጥቅምና የምክር ቃላት)
ኢየሱስና የቤተሰብ ግንኙነት።--ኢየሱስ በየትኛውም የሰዎች መደብ ውስጥ ጃንደረባነትን እንደ ግዴታ አላስቀመጠም። እርሱ የመጣው የተቀደሰውን የጋብቻ ግንኙነት ለማጥፋት ሳይሆን ከፍ ሊያደርገውና ወደ ቀድሞው ቅድስናው ሊመልሰው ነበር። ቅዱስና ራስ ወዳድነት የሌለበት ፍቅር የሚታይበትን ቤተሰብ በደስታ ይመለከተዋል። --MS 126, 1903. (AH 121.) {1MCP 220.4} 1MCPAmh 180.1
እርሱ [ክርስቶስ] ወንዶችና ሴቶች ቅዱስ በሆነ ጋብቻ አንድ በመሆን አባላቶቹ ክብርን በመጎናጸፍ የላይኛው ቤተሰብ አባላት ሆነው የሚታወቁባቸውን ቤተሰቦች እንዲያሳድጉ አዞአል። --MH 356 (1905). {1MCP 220.5} 1MCPAmh 180.2
በጋብቻ ውስጥ የእግዚአብሔር ዓላማ ተፈጽሟል።--በቅዱስ ዓላማ ወደ ጋብቻ ግንኙነት የሚገቡ ሁሉ--ባል የሴትን ልብ ንጹህ ፍቅር ለማግኘት፣ ሚስት የባሏን ባሕርይ በማለስለስና በማሻሻል ፍጹም ለማድረግ--እግዚአብሔር ለእነርሱ ያለውን ዓለማ ይፈጽማሉ። --MS 16, 1899. (AH 99.) {1MCP 220.6} 1MCPAmh 180.3
የጋብቻ ግንኙነት ልዩ ጥቅም/መብት።--እነርሱ [ያገቡ ክርስቲያኖች] እያንዳንዱን የጋብቻ ግንኙነት ልዩ ጥቅም በደንብ ከግምት ውስጥ ማስገባት አለባቸው፣ ቅዱስ መርህ የእያንዳንዱ ተግባር መሰረት መሆን አለበት። --2T 380 (1870). {1MCP 221.1} 1MCPAmh 180.4
‹‹የቤተሰብ ግንኙነትን ግላዊነትና ልዩ ጥቅሞች ቅዱስ አድርገው ስለሚጠበቁ ምሽጎች›› ጽፋለች። --2T 90 (1868). {1MCP 221.2} 1MCPAmh 180.5
የፍቅር ስሜቶች ነፃ የሚሆኑበት ጊዜ።- በቂ እድሜና ልምድ ፍቅርን የከበረና ያለ ችግር ነጻ ማድረግ የሚያስችል ጊዜ እስኪደርስ ድረስ የወጣቶች የፍቅር ስሜቶች ገደብ ሊደረግባቸው ይገባል። --AM 8, 1864. (MYP 452.) {1MCP 221.3} 1MCPAmh 180.6
ሕጋዊ የሆነውን ነገር ከልክ በላይ የማድረግ አደጋ።--መብላትና መጠጣት ወይም ማግባትና መጋባት በራሱ ኃጢአት የለበትም። ሕጋዊ የሆነው ነገር በተገቢ ሁኔታ ከተፈጸመና ኃጢአት እስኪሆን ድረስ ከልክ ካላለፈ በቀር ማግባት በኖህ ዘመንም ህጋዊ ነበር፣ አሁንም ሕጋዊ ነው።... {1MCP 221.4} 1MCPAmh 180.7
በኖህ ዘመን በተገቢ ሁኔታ ጥቅም ላይ ውሎ ቢሆን ኖሮ ሕጋዊ የነበረውን ጋብቻ ኃጢአት ያደረገው ተገቢ ያልሆነ፣ ከመጠን ያለፈ ፍቅር ነበር። በዚህ ዘመንም በጋብቻ ሀሳቦችና በጋብቻ ግንኙነት በራሱ በመመሰጥ ነፍሳቸውን እያጡ ያሉ ብዙዎች አሉ።... {1MCP 221.5} 1MCPAmh 180.8
እግዚአብሔር ሰዎችን በዓለም ውስጥ ስላስቀመጠ መብላት፣ መጠጣት፣ መነገድ፣ ማግባትና መጋባት መብታቸው ነው፤ ነገር ግን እነዚህን ነገሮች ማድረግ ከአደጋ ነጻ የሚሆነው በፈርሃ-እግዚአብሔር ከተደረገ ብቻ ነው። በዚህ ዓለም መኖር ያለብን ከዘላለማዊው ዓለም ጋር በተገናኘ መልኩ ነው። --RH, Sept 25, 1888. {1MCP 221.6} 1MCPAmh 181.1
ጋብቻ ፍትወተኛ የሆኑ የፍቅር ስሜቶችን ልጓም ለመልቀቅ ፈቃድ አይሰጥም።--የፍቅር ስሜቶቻቸውን መቆጣጠር ኃይማኖታዊ ግዴታቸው እንደሆነ የሚሰማቸው በጣም ጥቂቶች ናቸው። ከመረጡት ግለሰብ ጋር ራሳቸውን በጋብቻ ስላጣመሩ ጋብቻ ተራ (የወረደ) የፍቅር ስሜትን መፈጸምን ይቀድሰዋል የሚል መከራከሪያ ያቀርባሉ።እግዚአብሔርን እንደሚያመልኩ የሚናገሩ ወንዶችና ሴቶችም ቢሆኑ ፍትወተኛ የሆነውን የፍቅር ስሜታቸውን ልጓም ይለቁና በጣም አስፈላጊ የሆነውን ኃይል በማንጠፍጠፍ የሕይወት አያያዛቸውን የሚያደክምና መላ የአካል ክፍሎቻቸውን ኃይል የሚያሳጣውን ተግባር ስለመፈጸማቸው እግዚአብሔር እንደሚጠይቃቸው ምንም ሀሳብ የላቸውም። {1MCP 221.7} 1MCPAmh 181.2
የጋብቻ ቃል ኪዳን እጅግ የጠቆሩትን ኃጢአቶች ይሸፍናል። እግዚአብሔርን እናመልካን የሚሉ ወንዶችና ሴቶች በተበላሹ የፍቅር ስሜቶቻቸው አማካይነት አካሎቻቸውን እያዋረዱ ደስ ከማይል ፍጥረት በታች ራሳቸውን ዝቅ ያደርጋሉ። በቅድስናና በክብር እንዲጠበቁ እግዚአብሔር የሰጣቸውን ኃይሎች ያለ አግባብ ይጠቀማሉ። ጤንነትና ሕይወት ተራ በሆኑ የፍቅር ስሜቶች መሠዊያ ላይ ተሰውተዋል። ከፍ ያሉና የከበሩ ኃይሎች ለእንስሳዊ የተፈጥሮ ዝንባሌዎች ተገዥ ሆነዋል። በዚህ ሁኔታ ኃጢአት የሚሰሩ ሰዎች ከሚሄዱበት መንገድ ውጤት ጋር አልተዋወቁም። --2T 472 (1870). {1MCP 222.1} 1MCPAmh 181.3
በፍቅርና ፍትወተኛ በሆነ የፍቅር ስሜት መካከል ያለው ረቂቅ ሚዛን።--ሚስቱን የእርሱን ፍትወት የምታገለግል መሳሪያ እንድትሆን የሚያደርግ ፍቅር ንጹህ ፍቅር አይደለም። ይህ ለመፈጸም የማያቋርጥ ጩኸት የሚያሰማ እንስሳዊ የፍቅር ስሜት ነው። {1MCP 222.2} 1MCPAmh 181.4
ሐዋርያው በገለጸው ሁኔታ ፍቅራቸውን የሚያሳዩ ሰዎች ምንኛ ጥቂት ናቸው፡- ‹‹ክርስቶስ ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደዳት፣ በውኃ መታጠብና ከቃሉ ጋር አንጽቶ እንዲቀድሳት፣ እድፈት ወይም የፊት መጨማደድ ወይም እንዲህ ያለ ነገር ሳይሆንባት ቅድስትና ያለ ነውር ትሆን ዘንድ ስለ እርስዋ ራሱን አሳልፎ እንደ ሰጠ እንዲሁ ባሎች ሚስቶቻችሁን ውደዱ›› (ኤፌሶን 5፡ 25-27)። እግዚአብሔር ቅዱስ ስለመሆኑ እውቅና የሚሰጠው በጋብቻ ውስጥ ያለ ፍቅር ብቃት ይህ ነው። {1MCP 222.3} 1MCPAmh 181.5
ፍቅር ንጹህና ቅዱስ መርህ ነው፣ ነገር ግን ፍትወተኛ የፍቅር ስሜት ገደብን አይቀበልም፣ ለአእምሮ የማገናዘብ ችሎታም አይገዛም፣ ወይም እንዲቆጣጠረው ፈቃደኛ አይሆንም። ለውጤቶቹ እውር ነው፤ መንስኤና ውጤቱ ምን ይሆናል ብሎ አያስብም። {1MCP 222.4} 1MCPAmh 182.1
ብዙ ሴቶች የአካላቸው ሕጎች እየተጠበቁ ስላልሆነ ከፍተኛ የሆነ የአካል ድክመት እየደረሰባቸውና በቆዩ በሽታዎች እየተሰቃዩ ናቸው፤ የተፈጥሮ ሕጎች እየተረገጡ ናቸው። የአእምሮ ነርቭ ኃይል ተራ የሆኑ የፍቅር ስሜቶችን ለማርካት ተፈጥሮአዊ ያልሆነ ተግባርን እንዲፈጽም ወንዶችና ሴቶች በማድረጋቸው ባክኖአል፤ ይህ አስቀያሚ ነገር--ተራ የሆነ፣ የወረደ የፍቅር ስሜት--አስደሳች የሆነ የፍቅርን ስም ይይዛል። --2T 473, 474 (1870). {1MCP 222.5} 1MCPAmh 182.2
ፍቅር ተፈጥሮአዊ ከሆነው ሰብአዊ ልብ የፍቅር ስሜት ጋር ሲነጻጸር።--ፍቅር…ማገናዘብ የማይችል አይደለም፤ እውር አይደለም። ፍቅር ንጹህና ቅዱስ ነው። ነገር ግን የተፈጥሮ ልብ የፍቅር ስሜት ሙሉ በሙሉ ሌላ ነገር ነው። ንጹህ ፍቅር በእቅዶቹ ሁሉ እግዚአብሔርን የሚያስገባና ከእግዚአብሔር መንፈስ ጋር ፍጹም የሆነ መጣጣም ያለው ሲሆን ስሜት ግን ሀሳበ-ግትር፣ ችኩል፣ ምክንያታዊ ያልሆነ፣ ቁጥጥርን ሁሉ የሚቃወም ስለሆነ የመረጠውን ነገር ጣዖቱ ያደርጋል። እውነተኛ ፍቅር ባለው ሰው ጠባይ ሁሉ የእግዚአብሔር ጸጋ ይታያል።--RH, Sept 25, 1888. (AH 50.) {1MCP 223.1} 1MCPAmh 182.3
የአእምሮ ትዕዛዝ መቆጣጠር አለበት።--የጋብቻ ግንኙነትን ከእግዚአብሔር ቅዱስ ትዕዛዛት እንደ አንዱ አድርገው የሚመለከቱ ሰዎች፣ በእርሱ ቅዱስ ቃል ተጠብቀው፣ በአእምሮ ትዕዛዝ ቁጥጥር ሥር ይሆናሉ። --HL, No. 2, p 48, 1865. (2SM 440.) {1MCP 223.2} 1MCPAmh 182.4
በቅዱስ የቤተሰብ ክበብ ውስጥ ምስጢርን ጠብቁ። በእያንዳንዱ ቤተሰብ ዙሪያ ሳይሰበር መጠበቅ ያለበት ቅዱስ ክበብ አለ። በዚህ ክበብ ውስጥ ማንም ሌላ ሰው የመግባት መብት የለውም። ባል ወይም ሚስት ለእነርሱ ብቻ የሆነውን ምስጢር ሌላ ሰው እንዲካፈል መፍቀድ የለባቸውም። --MH 361 (1905). {1MCP 223.3} 1MCPAmh 182.5
(ለ) አሉታዊው (የእቀባና የማስጠንቀቂያ ቃላት)
ጋብቻ ፍትወተኛነትንና ወራዳ ልምምዶችን ለመሸፈን የታቀደ አይደለም።--እግዚአብሔር ጋብቻን ያቀደው በፍጹም እየተፈጸሙ ያሉ በርካታ ኃጢአቶችን ለመሸፈን አይደለም። በጋብቻ ግንኙነት ውስጥ የሚፈጸሙ ፍትወተኛነትና የወረዱ ልምምዶች አእምሮንና ግብረገብን ከጋብቻ ግንኙነት ውጭ ለሚፈጸሙ የወረዱ ልምምዶች እያስተማሩ ናቸው። --RH, May 24, 1887. {1MCP 223.4} 1MCPAmh 183.1
ወሲብን ከመጠን በላይ መፈጸም ጤናንና ሕይወትን ለአደጋ ያጋልጣል።--ሚስት ጤንነቷንና ሕይወቷን እየጎዳች የባለቤቷን እንስሳዊ የተፈጥሮ ዝንባሌ እንድታረካ የሚመራ ፍቅር ንጹህና ቅዱስ ፍቅር አይደለም። ... {1MCP 223.5} 1MCPAmh 183.2
እርሱ (ባሏ) ደስ ባይለውም ከመጠን ላለፈ ወሲብ ራሷን አሳልፋ በመስጠት አካሏን ማዋረድ እንደማትችል በትህትናና በፍቅር መግለጽ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል። በገርነትና በደግነት እግዚአብሔር በመላ አካሏ ላይ የመጀመሪያና ከፍተኛ ባለቤትነት እንዳለውና ይህንን ባለቤትነቱን ችላ ማለት እንደማትችል፣ ይህን አድርጋ ከተገኘች ደግሞ በታላቁ የእግዚአብሔር ቀን ተጠያቂ እንደምትሆን ልታሳስበው ይገባል። --2T 475 (1870). {1MCP 224.1} 1MCPAmh 183.3
ወሲብን ከመጠን በላይ መፈጸም ለአምልኮ ልምምዶች ያለውን ፍቅር ውጤቱ በሚታይበት ሁኔታ ያጠፋል፣ ከአእምሮ ውስጥ አካልን ለመመገብ አስፈላጊ የሆነ ነገርን ይወስዳል፣ በተሳካ ሁኔታ የአካል ብርታትን ያሟጥጣል። --2T 477 (1870). {1MCP 224.2} 1MCPAmh 183.4
የተቀደሰ ተቋምን ማጣመም።--ብዙዎች ወደ ጋብቻ ግንኙነት ስለገቡ የተፈጥሮ እንስሳዊ ስሜቶች እንዲቆጣጠሩአቸው መፍቀድ የሚችሉ ይመስላቸዋል። ይህን ቅዱስ ተቋም እንዲያጣምሙ በሚያታልላቸው በሰይጣን ተመርተዋል። አእምሮዎቻቸው በሚይዙት ዝቅ ባለ ደረጃ በደንብ ይደሰታል፣ ለዚህ ምክንያቱ በዚህ አቅጣጫ የሚያተርፈው ብዙ ነገር ስላለው ነው። {1MCP 224.3} 1MCPAmh 183.5
ተራ የሆኑ የፍቅር ስሜቶችን ማነሳሳት ቢችልና እያደጉ እንዲሄዱ ቢያደርግ በክርስቲያናዊ ልምምዳቸው የሚረብሸው ምንም ነገር እንደማይኖር ያውቃል፤ ይህ የሚሆነው እንስሳዊ የተፈጥሮ ዝንባሌዎች የበላይነት ሲይዙና ወደ ላይ እየወጡ ሲሄዱ የሞራልና የአእምሮ ማስተዋል ኃይሎች ተገዥ ስለሚሆኑ ነው። እነዚህ ተራ የሆኑ የፍቅር ስሜቶች ሥራ ላይ ሲውሉና እየጠነከሩ ሲሄዱ የከበሩ ባሕሪያት ደግሞ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየደከሙ ይሄዳሉ። --2T 480 (1870). {1MCP 224.4} 1MCPAmh 183.6
በጋብቻ ውስጥ የወሲብ ልዩ መብቶችን ያለ አግባብ መጠቀም።--እንስሳዊ ስሜቶች፣ እንክብካቤ ሲደረግላቸውና ሲፈጸሙ፣ በዚህ ዘመን እጅግ ስለሚጠነክሩ እርግጠኛ የሆነ ውጤታቸው በጋብቻ ሕይወት ውስጥ ሊነገሩ የማይቻሉ ክፋቶችን ማምጣት ነው። አእምሮ በማደግና የመቆጣጠር ኃይል በመሆን ፋንታ ከፍ ያሉና የከበሩ ኃይሎች ለእንስሳዊ ዝንባሌዎች ተገዥ እስኪሆኑ ድረስ እንስሳዊ ፍላጎቶች ይገዛሉ። ውጤቱ ምንድን ነው? የሴቶች ስስ የአካል ክፍሎች ይጎዱና ለበሽታ ይጋለጣሉ፤ ያለ ችግር ልጅን መውለድ የማይቻል ይሆናል፤ የወሲብ ልዩ መብቶች ያለ አግባብ ጥቅም ላይ ውለዋል። {1MCP 224.5} 1MCPAmh 184.1
ወንዶች የራሳቸውን አካል እያበላሹ ናቸው፣ በዓይኖቻቸው ፊት እግዚአብሔርን መፍራት እስከማይኖር ድረስ ሚስቶች የእነርሱን መረን የለቀቁ፣ ተራ ፍትወቶች ለማርካት የአልጋ ባሪያዎች ሆነዋል። አካልንና ነፍስን የሚያዋርደውን ስሜት መፈጸም የጋብቻ ሕይወት ሥርዓት ሆኗል። --MS 14, 1888. {1MCP 225.1} 1MCPAmh 184.2
ከወሊድ በፊት ተጽእኖዎች።--ሰይጣን የራሱን ጥላቻ የተሞላበት ምስል በልጆቻቸው ላይ ማተም እንዲችል አእምሮዎቻቸውን ማርከስ ይፈልጋል።. . . {1MCP 225.2} 1MCPAmh 184.3
የወላጆችን አእምሮዎች በዚህ መልክ በመቆጣጠር በእነርሱ አማካይነት ለልጆቻቸው የራሱን የባሕሪ አሻራ መስጠት ስለሚችል ከወላጆች ይልቅ ልጆቻቸውን በቀላሉ መቅረጽ ይችላል። ከዚህ የተነሣ ብዙ ልጆች በአብዛኛው ከትውልድ ወደ ትውልድ እያደጉ የሚሄዱ እንስሳዊ ስሜቶችን ይዘው ይወለዳሉ፣ በተቃራኒው የሞራል ኃይሎች እየደከሙ ይሄዳሉ። የእነዚህ ልጆች የሞራልና የአእምሮ እውቀት ኃይሎች መምራት እንዲችሉ ለማውጣት፣ ለማጠንከርና ለማሳደግ እጅግ ጥንቃቄ የተሞላበት አስተዳደግ ያስፈልጋቸዋል። --2T 480 (1870). {1MCP 225.3} 1MCPAmh 184.4
ዝቅ የማድረግ (የማዋረድ) ሂደት።--የወንድም ሆነ የሴት አእምሮ ከንጽህናና ከቅድስና ወደ ሕገ ወጥነት፣ ብልሽትና ወንጀል በቅጽበት አይወርድም። ሰብአዊውን ወደ መለኮታዊ ለመለወጥ ወይም በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠሩትን ወደ ጨካኝነት ወይም ሳይጣናዊነት ለመለወጥ ጊዜ ይወስዳል።{1MCP 225.4} 1MCPAmh 184.5
በማየት እንለወጣለን። ምንም እንኳን በፈጣሪው ምሳሌ ቢፈጠርም፣ በአንድ ወቅት እጅግ ይጠላ የነበረው ኃጢአት አስደሳች እስኪሆንለት ድረስ አእምሮውን ማስተማር ይችላል። መንቀትና መጸለይን ሲያቆም፣ የራሱን ልብ መጠበቁን ያቆምና ኃጢአትንና ወንጀልን በመስራት ላይ ይሰማራል። አእምሮ ስለረከሰ፣ የሞራልና የአእምሮ ኃይሎችን ባሪያ ለማድረግና ላልታረሙ የፍቅር ስሜቶች ለማስገዛት እየተማረ ስለሆነ፣ ከሥነ-ምግባር ውድቀት ለማንሳት አይቻልም። {1MCP 225.5} 1MCPAmh 184.6
ሥጋዊ ከሆነ አእምሮ ጋር የማያቋርጥ ጦርነት መደረግ አለበት፤ በጦርነቱ ላይ አእምሮን ወደ ላይ በሚስበውና ንጹህና ቅዱስ ነገሮች ላይ እንዲያሰላስል መኖሪያው በሚያደርግ፣ የማንጻት ተጽእኖ ባለው የእግዚአብሔር ጸጋ መረዳት አለብን። --2T 478, 479 (1870). {1MCP 225.6} 1MCPAmh 185.1
ምክር ለሴቶች።--በዚህ ዘመን ያሉ ሴቶች፣ ያገቡትም ሆኑ ያላገቡት፣ እጅግ ብዙ ጊዜ አስፈላጊ የሆነውን የተጠበቀ ነገር በደንብ አለመንከባከባቸውን ባዘነ ልብ ሆኜ እጽፋለሁ። እንደ መሽኮርመም ያደርጋቸዋል። ወንደላጤዎችም ሆኑ ያገቡ ወንዶች ትኩረታቸውን በእነርሱ ላይ እንዲያደርጉ ስለሚያደፋፍሩ በግብረ ገብ ኃይላቸው ደካማ የሆኑት ወጥመድ ውስጥ ይገባሉ። {1MCP 226.1} 1MCPAmh 185.2
እነዚህ ነገሮች፣ ከተፈቀዱ፣ ወንጀል ኃጢአት መስሎ እስከማይታይ ድረስ ግብረ ገብን ይገድሉና አእምሮን ያሳውራሉ። ሴት በሙሉ ጨዋነትና አሳቢነት ቦታዋን ብትጠብቅ ኖሮ ሊቀሰቀሱ የማይችሉ ሀሳቦች አይቀሰቀሱም ነበር። ለራሷ ሕገወጥ የሆነ ዓላማ ወይም ምክንያት ላይኖራት ይችላል፣ ነገር ግን ለእነዚያ ለተፈተኑት ወንዶች እና ከእነርሱ ጋር ግንኙነት ከፈጠሩአቸው ማግኘት የሚችሉትን ሁሉ እርዳታ ለሚፈልጉት ማደፋፈሪያ ሰጥታለች።{1MCP 226.2} 1MCPAmh 185.3
ጥንቁቅና ቁጥብ በመሆን፣ ለራስ ነጻነትን ባለመስጠት፣ ያለ አግባብ የሆኑ ትኩረቶችን ባለመቀበል፣ ነገር ግን ከፍተኛ የሆነ የግብረ ገብ ቅኝትና ተገቢ የሆነ ክብር በመጠበቅ፣ ከብዙ ክፋት መዳን ይቻል ነበር።--MS 4a, 1885. (AH 331, 332.) {1MCP 226.3} 1MCPAmh 185.4
ሴቶች እንደ ፈታኞች።--አግባብነት ለሌለው ትውውቅ እጅግ አነስተኛ የሆነ ማደፋፈሪያ እንኳን እንዳይሰጥ እውነትን እንደሚቀበሉ የሚናገሩ ሴቶች ራሳቸውን አጥብቀው አይጠብቁምን? ሁል ጊዜ ጥብቅ የሆነ ቁጥብነትና የጠባይ ጨዋነት ቢጠብቁ ኖሮ ብዙ የፈተና በሮችን ይዘጉ ነበር።--5T 602 (1889). {1MCP 226.4} 1MCPAmh 185.5
ብዙ ጊዜ ሴቶች ፈታኞች ናቸው። በአንድ ወይም በሌላ መንገድ በማስመሰል፣ ያገቡትን ወይም ያላገቡትን ወንዶች ትኩረት ይስቡና ፣ ጠቃሚነታቸው እስኪበላሽ ድረስ፣ እና ነፍሳቸው በአደጋ ላይ እስክትሆን ድረስ የእግዚአብሔርን ሕግ ወደ መተላለፍ ይመሩአቸዋል። --5T 596 (1889). {1MCP 226.5} 1MCPAmh 185.6
ርኅሩኅ ፓስተር።--ትርፍ በምታገኙበት ወገን የእግዚአብሔር ሰዎች ሁኑ። እውቀት የሚመኙአት ሰዎች በሚደርሱበት ቦታ ትገኛለች። አእምሮ ብርቱ፣ አጥልቆ የሚያስብ፣ ሙሉና ጥርት ያለ እንዲሆን የእግዚአብሔር እቅድ ነው። ሄኖክ እንዳደረገው ከእግዚአብሔር ጋር ተራመዱ፤ እግዚአብሔርን አማካሪያችሁ ካደረጋችሁ ትሻሻላላችሁ።. . . {1MCP 226.6} 1MCPAmh 186.1
የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት እንጠብቃለን የሚሉ፣ በእነርሱ ኃላፊነት ሥር ያሉ መንጎችን በመጎብኘት ያልተጠነነቁ ነፍሳትን እፍረት ወደ ሌለበት ነጻነትና ትውውቅ የሚመሩ ወንዶች አሉ።. . . {1MCP 227.1} 1MCPAmh 186.2
እርሱ [አገልጋይ] ቤተሰቦችን ሲጎበኝ፣ የጋብቻ ሕይወት ምስጢሮቻቸውን መጠየቅ ይጀምራል። ከባሎቻቸው ጋር በደስታ አብረው ይኖራሉን? እንደሚያደንቁአቸው ይሰማቸዋልን? በጋብቻ ሕይወታቸው መጣጣም አለን? በዚህ መልኩ የማትጠራጠር ሴት ከእነዚህ አጥማጅ ጥያቄዎች የተነሣ የምስጢር ሕይወቷን፣ ተስፋ መቁረጦቿን፣ ትናንሽ ፈተናዎቿንና ቅሬታዎቿን፣ ካቶሊኮች ለካህናቶቻቸው እንደሚያደርጉት ለእንግዳው ወደ መግለጥ ትመራለች። {1MCP 227.2} 1MCPAmh 186.3
ከዚያ በኋላ ይህ ርኅሩኅ ፓስተር የራሱን ልምምድ ምዕራፍ ጣልቃ ማስገባት ይጀምራል፤ ባለቤቱ እርሱ የመረጣት እንዳልሆነች፣ በመካከላቸው እውነተኛ የሆነ ጥብቅ ግንኙነት እንደሌለ ይናገራል። ሚስቱን አይወዳትም። እርሱ እንደጠበቀው አልሆነችለትም። በዚህ መልክ በመካከል ላይ ያለው መለያ ይሰበርና ሴቶች ይታለላሉ። ሕይወታቸው ትልቅ ተስፋ አስቆራጭ እንደሆነና ይህ እረኛ ለመንጋው ትልቅ ርኅራኄ እንዳለው ይሰማቸዋል። የዚህ ዓይነት ሥራ ሰባተኛውን ትዕዛዝ ወደ ማፍረስ ካልመራ፣ የፍቅር ሕመምተኛነት ስሜት ይደፋፈርና የአእምሮና የነፍስ ንጽህና ይጎድፋል። {1MCP 227.3} 1MCPAmh 186.4
የተበከሉ አስተሳሰቦች ሲስተናገዱ ልማድ ስለሚሆኑ ነፍስ ጠባሳ ይፈጥርና ይበከላል። አንድ ጊዜ የስህተት ተግበር ከተፈጸመ ከክርስቶስ ደም በስተቀር ምንም ነገር ሊፈውሰው የማይችል ነቁጣ ይፈጠራል፤ ከዚህ ልማድ በጽኑ ውሳኔ ካልተመለስን በቀር ነፍስ ይበላሽና ከዚህ ከተበከለ ምንጭ የሚፈሰው ውኃ ሌሎችን ያበላሻል። ይህን ሥራ መስራታቸውን የሚቀጥሉትን ሁሉ እግዚአብሔር በእርግጠኝነት ያጠፋቸዋል። . . . {1MCP 227.4} 1MCPAmh 186.5
ከፍ ያልን፣ የከበርን እና የተቀደስን መሆን አለብን። ለማሸነፍ ከክርስቶስ ብርታትን ልናገኝ እንችላለን፤ ነገር ግን ባሕርይ ንጽህናውን ሲያጣ፣ ኃጢአት የባሕርይ አካል ሲሆን፣ ከአስካሪ መጠጥ ጋር እኩል የሆነ የአስማት ኃይል አለው። ራስን የመቆጣጠርና የማገናዘብ ኃይል መላው አካልን በሚበክሉ ልምምዶች ይሸነፋል፤ እነዚህ የኃጢአት ልምምዶች ከቀጠሉ አእምሮ ይደክማል፣ ይታመማል፣ ሚዛኑንም ያጣል።--Lt 26d, 1887. {1MCP 227.5} 1MCPAmh 186.6
ወንዶች፣ ሴቶችና ወጣቶች በሞራል ብልሽት ላይ ተሳትፎ አላቸው።--ሽማግሌዎችና ወጣቶች በሙሉ የተጋለጡባቸው አደጋዎች በየቀኑ እየጨመሩ ናቸው። የሥነ-ምግባር ጉድለት ብለን የምንጠራው የሞራል እብደት ለመስራት ከበቂ በላይ ቦታ ያገኛል፣ ክርስቲያን ነን በሚሉ ወንዶች፣ ሴቶችና ወጣቶች የወረደ፣ ፍትወተኛና ሰይጣናዊ የሆነ ተጽእኖ ሥራ ላይ ውሏል። --Lt 26d, 1887. {1MCP 228.1} 1MCPAmh 187.1
ሰይጣን ወንዶችን፣ ሴቶችን፣ ልጆችንና ወጣቶችን እርኩስ በሆኑ ልምምዶች ላይ ለማሳተፍ ጥበብ የተሞላበትን ጥረት እያደረገ ነው። እናምናለን በሚሉት ቅዱስ እውነት ስላልጎለመሱ፣ ስላልነጹ፣ ስላልተሻሻሉ፣ እና ስላልከበሩ ፈተናዎቹ በብዙ ልቦች ውስጥ ተቀባይነትን ያገኛሉ። በአስተሳሰባቸው የወረዱና የረከሱ፣ በንግግራቸውና በጸባያቸውም ተራ ከመሆናቸው የተነሣ የሰይጣን ፈተናዎች ሲመጡ ለመቋቋም የሞራል ኃይል ስለሌላቸው በቀላሉ የእርሱ ሲሳይ የሚሆኑ ጥቂቶች አይደሉም። --Lt 26d, 1887. (HP 199.) {1MCP 228.2} 1MCPAmh 187.2
ቁልቁል እርምጃ።--የሰይጣን የማያቋርጡ ፈተናዎች የተዘጋጁት ሰው በራሱ ልብ ላይ ያለውን ገዥነትና ራሱን የመቆጣጠር ኃይል ለማዳከም ነው። ሰውን ከፈጣሪው ጋር ቅዱስና ደስታ ባለበት አንድነት ያስተሳሰሩትን ገመዶች እንዲቆርጥ ይመራዋል። {1MCP 228.3} 1MCPAmh 187.3
ከእግዚአብሔር ጋር ያለው ግንኙነት ሲቋረጥ የማገናዘብ ችሎታን ንዴት፣ መርህን ስሜት፣ ስለሚቆጣጠር በሀሳቡና በተግባሩ ኃጢአተኛ፣ ፍርድ አሰጣጡ የተዛባ፣ የማገናዘብ ችሎታው የደከመ፣ ስለሚሆን በእግዚአብሔር ቃል ብርሃን ራሱን በትክክል በማየት አስቀድሞ ወደ እግዚአብሔር በመመለስ ወደ ራሱ መመለስ ያስፈልገዋል። --Lt 24, 1890. {1MCP 228.4} 1MCPAmh 187.4
እርኩሰትን ከማንበብ፣ ከመመልከትና ከመስማት ራቁ።--በሰይጣን ወጥመዶች ውስጥ መውደቅ የማይፈልጉ ሰዎች የነፍስን መንገዶች በደንብ መጠበቅ አለባቸው፤ እርኩስ የሆኑ ሀሳቦችን የሚያቀርቡ ነገሮችን ከማንበብ፣ ከማየትና ከመስማት መቆጠብ አለባቸው። አእምሮ የነፍሳት ጠላት በሚያቀርበው በእያንዳንዱ ርዕስ ላይ በዘፈቀደ እንዲያርፍ መተው የለበትም። ልብ በታማኝነት መጠበቅ አለበት፣ ይህ ካልሆነ በውጭ ያሉ ክፋቶች በውስጥ ያሉ ክፋቶችን ይቀሰቅሱና ነፍስ በጨለማ ውስጥ ይባዝናል። --AA 518 (1911). {1MCP 228.5} 1MCPAmh 187.5
አእምሮአችሁን መቆጣጠርና ከንቱና የተበላሹ ሀሳቦች ነፍሳችሁን እንዳያጎድፉ መከላከል ከፈለጋችሁ ለዓይኖቻችሁ፣ ለጆሮዎቻችሁና ለስሜት ሕዋሳቶቻችሁ ሁሉ ታማኝ ዘብ መሆን አለባችሁ። ይህን እጅግ ተናፋቂ ሥራ መስራት የሚችለው የፀጋ ኃይል ብቻ ነው።--2T 561 (1870). {1MCP 229.1} 1MCPAmh 188.1
የወሲብ ስሜት ቀስቃሽ ልበ-ወለዶችና እርቃን የወሲብ ድርጊቶችን የሚያሳዩ ፊልሞች/መጻሕፍት ።--ንጹህ ያልሆኑ ስዕሎች (ፎቶዎች) የማርከስ ተጽእኖ አላቸው። ብዙዎች ልበ-ወለዶችን በታላቅ ጉጉት ስለሚከታተሉአቸው አስተሳሰባቸው ይረክሳል። {1MCP 229.2} 1MCPAmh 188.2
ብዙ ጊዜ በመኪናዎች ውስጥ እራቁታቸውን የተነሱ ሴቶች ፎቶዎች ለሽያጭ ይዘዋወራሉ። እነዚህ የሚያስጠሉ ፎቶዎች በፎቶ ስቱዲዎችም የሚገኙ ሲሆን ቅርጽ በሚሰሩ ሰዎች ግድግዳዎች ላይም ተንጠልጥለው ይገኛሉ። ይህ ዘመን እርኩሰት በየቦታው ሞልቶ እየተትረፈረፈ ያለበት ዘመን ነው።{1MCP 229.3} 1MCPAmh 188.3
በማየትና በማንበብ የዓይን ፍትወትና እርኩስ የፍቅር ስሜቶች ይቀሰቀሳሉ።…አእምሮ የወረዱና ተራ የሆኑ የፍቅር ስሜቶችን የሚቀሰቅሱ ትዕይንቶች ላይ በማሰላሰል ደስታን ያገኛል። እነዚህ እርኩስ ምስሎች፣ በረከሰ አእምሮ ሲታዩ፣ ግብረ ገብን በማበላሸት የተታለሉትና በወረት ፍቅር የተያዙት ፍጡሮች ፍትወተኛ የሆነ የፍቅር ስሜታቸውን ልጓም እንዲለቁ ያደርጓቸዋል። ከዚያ በኋላ በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠሩ ፍጡሮችን ወደ እንስሳነት ደረጃ ዝቅ በማድረግ በመጨረሻ ወደ ጥፋት የሚያሰምጡአቸው ኃጢአቶችና ወንጀሎች ይከተላሉ። እርኩስ ሀሳቦችን የሚያቀርቡላችሁን ነገሮች ከማንበብና ከማየት ራቁ። የግብረ ገብና የአእምሮ ኃይሎችን አሳድጉ። --2T 410 (1870). {1MCP 229.4} 1MCPAmh 188.4
አእምሮ ወሳኝ ነገር።--ጳውሎስ እንዲህ ብሏል፣ ‹‹በአእምሮዬ ለእግዚአብሔር ሕግ እገዛላሁ።›› ይህ አእምሮ እንስሳዊ የምግብ ፍላጎትንና የፍቅር ስሜትን በመፈጸም ሲጨልም የግብረ ገብ ኃይሎች ስለሚደክሙ ቅዱስና ተራ የሆኑ ነገሮችን መለየት ያቅታል። --Lt 2, 1873. {1MCP 229.5} 1MCPAmh 188.5
ሴጋ (ብልትን በመነካካት ዘርን በማፍሰስ ስሜትን ማርካት)፡ [ማስታወሻ፡-ደራሲዋ ይህን ርዕስ ቴስቲሞኒስ በሚል መጽሐፍ ሁለተኛው ቅጽ ላይ ገጽ 346-353 እና 480-482 ላይ እና ከሕትመት ውጭ በሆነ በራሪ ጽሁፍ ላይ ተማጽእኖ ለእናቶች (1864) በሚል ርዕስ በስፋት ገልጻለች። በዚህ ርዕስ ላይ ከታተሙትና ካልታተሙት ምንጮች የተወሰዱ አጠቃላይ ሀሳቦችን ለማግኘት ቻይልድ ጋይዳንስ በሚል መጽሐፍ 17ኛው ክፍል ውስጥ ‹‹የግብረ ገብ ሀቀኝነትን መጠበቅ›› የሚለውን ርዕስ ገጽ 439-468ን ይመልከቱ።--አሰባሳቢዎች]።-- ከሁለቱም ፆታ የሆኑ ልጆችና ወጣቶች በግብረ ገብ ብክለት [ሴጋ] ላይ በመጠመድ ይህን አስቀያሚ የሆነ፣ ነፍስንና አካልን የሚያጠፋ እርኩሰት ይለማመዳሉ። {1MCP 230.1} 1MCPAmh 188.6
ብዙ ክርስቲያን ነን ባዮች ከዚህ ልምምድ የተነሣ ስለደነዘዙ፣ ግብረገብን የሚመለከቱ የስሜት ኃይሎቻቸው ኃጢአት መሆኑን ለመረዳት ሊቀሰቀሱ ስለማይችሉ፣ ይህን ተግባር መፈጸማቸውን ከቀጠሉ ውጤቶቹ ሙሉ በሙሉ የአካልና የአእምሮ ውድመት ናቸው። ሰው፣ በምድር ላይ እጅግ የከበረው ፍጡር፣ በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረ፣ ራሱን ወደ እንስሳነት ይለውጣል! ራሱን ደደብና ሥነ-ምግባር የጎደለው ያደርጋል። {1MCP 230.2} 1MCPAmh 189.1
እያንዳንዱ ክርስቲያን ስሜቶቹን መቆጣጠርንና በመርህ መገዛትን መማር አለበት። ይህን ካላደረገ በስተቀር የክርስትናን ስም ለመያዝ የተገባ አይደለም። {1MCP 230.3} 1MCPAmh 189.2
አንዳንድ ከፍተኛ ሙያ ያላቸው ሰዎች ራስን ያለ አግባብ የመጠቀምን ኃጢአትና የሚያስከትላቸውን እርግጠኛ የሆኑ ውጤቶች አይገነዘቡም። ለረዥም ጊዜ ጸንቶ የቆየ ልማድ የመረዳት ችሎታቸውን አሳውሮታል። የዚህን የአካል ክፍሎችን የሚያደክምና የአእምሮ ነርቭ ኃይሎችን የሚያጠፋ አዋራጅ ኃጢአት ከመጠን ያለፈ ኃጢአተኝነት አይገነዘቡም። {1MCP 230.4} 1MCPAmh 189.3
የግብረገብ መርህ ተመስርቶ ከቆየ ልማድ ጋር ግጭት ሲፈጥር እጅግ በጣም ደካማ ነው። ከሰማይ የተላኩ አስፈሪ መልእክቶች ይህን አዋራጅ እርኩሰት እንዳይፈጽም ያልታጠረውን ልብ ሊነኩ አይችሉም። ተፈጥሮአዊ ያልሆነ ፍላጎትን ለማርካት ሲባል ፍትወትን በመፈጸም መጥፎ ፍቅር ከተለከፈ የወሲብ ስሜት መነሳሳት የተነሣ በቀላሉ ሊጎዱ የሚችሉ የአእምሮ ነርቮች ጤናማ ቅኝታቸውን አጥተዋል። ከመላው የአካል ክፍሎች ጋር ግንኙነት የሚፈጥሩ የአእምሮ ነርቮች እግዚአብሔር ከሰው ጋር በመገናኘት ውስጣዊ ሕይወቱን ሊነካ የሚችልባቸው ብቸኛ መንገድ ናቸው።{1MCP 230.5} 1MCPAmh 189.4
በነርቭ ሥርዓት ውስጥ የኤሌክትሪክ ኃይል ፍሰት (ዝውውር) እንዳይካሄድ የሚረብሽ ማንኛውም ነገር የዋና ኃይሎችን ብርታት የሚቀንስ ሲሆን ውጤቱ የአእምሮ ስሜቶችን መግደል (ምንም ነገር እንዳይሰማቸው ማድረግ) ነው። --2T 347 (1870). {1MCP 230.6} 1MCPAmh 190.1
አንዳንድ ልጆች ራሳቸውን የመበከል ልምምድ የሚጀምሩት ገና በሕጻንነታቸው ነው፤ እድሜያቸው እየጨመረ ሲሄድ ፍትወተኛ የፍቅር ስሜቶች ከእድገታቸው ጋር እያደጉ ይሄዱና ከጥንካሬያቸው ጋር እየጠነከሩ ይሄዳሉ። አእምሮአቸው እረፍት የለውም። ልጃገረዶች ከወንድ ልጆች ጋር አብረው መሆን ይፈልጋሉ፣ ወንድ ልጆችም ከልጃገረዶች ጋር አብረው መሆን ይፈልጋሉ። ፀባያቸው ቁጥብ ያልሆነና ጨዋነት የጎደለው ነው። ደፋርና ያለ ጊዜያቸው ያደጉ ስለሆኑ ጋጠወጥ ነጻነትን ያሳያሉ። ራስን ያለ አግባብ የመጠቀም ልማድ አእምሮአቸውን አርክሶታል፣ ነፍሳቸውንም በክሎታል።--2T 481 (1870). {1MCP 231.1} 1MCPAmh 190.2
ከጋብቻ በፊት የግብረ ሥጋ ግንኙነት (ለሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት የተሰጠ ምክር)።--ለወጣት ወንዶች ከሚቀርቡላቸው ፈተናዎች ሁሉ ፍትወትን ለመፈጸም ከሚቀርበው ፈተና የበለጠ ገዳይ የሆኑ ፈተናዎች ጥቂት ናቸው፣ ለማድረግ ከተሸነፉ ለአሁንና ለዘላለም ነፍስንና አካልን በማያዳግም ሁኔታ የሚያወድም እንደዚህ ያለ ሌላ ምንም የለም።... {1MCP 231.2} 1MCPAmh 190.3
ሌሊቱን ከእሷ [ከኤን]ጋር አብረህ የነበርክባቸውን ሰዓታት እንዳይ ተደርጌያለሁ፤ እነዚህ ሰዓቶች በምን ሁኔታ እንዳለፉ አንተ በተሻለ ሁኔታ ታውቃለህ። የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት መጣስ አለመጣስህን ለመናገር ደውለህልኝ ነበር። እኔም መልሼ ልጠይቅህ፣ ትዕዛዛቱን አልጣስክምን? {1MCP 231.3} 1MCPAmh 190.4
በየሌሊቱ አብራችሁ በነበራችሁባቸው ሰዓታት ጊዜያችሁ ለምን ተግባር ነበር የዋለው? አቋማችሁ፣ አመለካከታችሁ፣ ፍቅራችሁ ሁሉ በሰማይ መዝገብ እንዲመዘገቡ የምትፈልጉአቸው ናቸውን? መላእክትን የሚያሳፍሩ ነገሮችን አይቻለሁ፣ ሰምቻለሁም።…በኤን ላይ ያደረግከውን ነገር እስካላገባት ድረስ ማንኛውም ወጣት ማድረግ የለበትም፤ ይህ ጉዳይ እጅግ ጥልቅ በሆነ ሁኔታ ስላልተሰማህ እጅግ ተገርሜያለሁ።{1MCP 231.4} 1MCPAmh 190.5
አሁን እየጻፍኩልህ ያለሁት ለነፍስህ ብለህ ከአሁን በኋላ ከፈተና ጋር ጊዜህን እንዳታባከን ለመለመን ነው። እንደ አስፈሪ ቅዠት በላይህ ተንጠልጥሎ ያለውን አስማት ለመስበር አጠር ያለ ሥራ ስራ። በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ለማግኘት ፍላጎት ካለህ ለአሁንና ለዘላለም ራስን ከዚህ እስራት ፍታ።... {1MCP 231.5} 1MCPAmh 190.6
ሁለታችሁ በወረት ፍቅር ስለተያዛችሁ ከእርሷ ጋር የሌሊቱን ሰዓታት አብራችሁ አሳልፋችኋል።…በጌታ ስም ትኩረትህን ከኤን ላይ አንሳ ወይም አግባት።…እሷንም ማግባት የምትችለው አብረሃት ልትሆንና ባልና ሚስት ከእርስ በርሳቸው ጋር ሊኖራቸው የሚገባው ዓይነት ግንኙነት እንዲኖራችሁ ነው።... {1MCP 231.6} 1MCPAmh 191.1
አሁን ከኤን ጋር መሆን እንዳስደሰተህና እንደማረከህ በሕይወትህ ዘመን ሁሉ ከእሷ ጋር አብረህ በመሆን መደሰት ከፈለግክ አሁን ከሄድከው እርምጃ ሌላ ተጨማሪ አንድ እርምጃ በመሄድ ለምን ራስህን ህጋዊ ከለላዋ በማድረግ ከእሷ ጋር ያለ ተቀናቃኝ የፈለግከውን ያህል ሰዓት አብረህ የመሆንን መብት የራስህ አታደርግም? ድርጊትህና ንግግርህ ለእግዚአብሔር የሚያስጠላ ነው። --Lt 3, 1879. {1MCP 231.7} 1MCPAmh 191.2
የተበላሹ የሶዶም ግብረገቦች።--ሶዶም ከኗሪዎቿ ክፋት የተነሳ ስለደረሰባት ውድቀት የማያውቅ ሰው የለም። ነቢዩ በዚህ ቦታ [ሕዝቅኤል 16፡ 49] ወደ ተበላሹ ግብረገቦች የመሩ ልዩ የሆኑ ክፋቶችን ጠቅሶአል። ዛሬ በሶዶም ላይ የእግዚአብሔር ቁጣ እንዲወርድና ፈጽማ እንድትጠፋ ያደረጉት እነዚያው ኃጢአቶች በዓለም ላይ እንዳሉ እናያለን። --HR, July, 1873. (4BC 1161.) {1MCP 232.1} 1MCPAmh 191.3
ከውኃ ጥፋት በፊት የነበረው ዓለምና የሶዶም ኃጢአቶች እየጨመሩ በመሄድ ላይ ናቸው።--በየቦታው የሰብአዊነት ብልሽት፣ የቤተሰብ መሠዊያዎች ችላ መባል፣ ትዳርን መፍታት ይታያሉ። እንግዳ የሆነ መርህን መተው፣ የግብረገብ መስፈርት መውረድ አለ፤ ምድር በውኃ እንድትጠፋ እና ሶዶም በእሳት እንድትቃጠል የእግዚአብሔር ፍርድ እንዲፈስ ያደረጉ ኃጢአቶች በፍጥነት በመጨመር ላይ ይገኛሉ። --5T 601 (1889). {1MCP 232.2} 1MCPAmh 191.4
ዛሬ ቤተ ክርስቲያንን እየወረረ ነው።--ዛሬ የክርስቶስ ተከታዮች ነን በሚሉት መካከል እንኳን ሳይቀር እርኩሰት ተስፋፍቷል። የስሜት ልጓም ተለቆአል፤ እንስሳዊ የተፈጥሮ ዝንባሌዎች ከመፈጸማቸው የተነሣ ጥንካሬ እያገኙ ሲሄዱ የግብረገብ ኃይሎች ደግሞ ያለማቋረጥ እየደከሙ በመሄድ ላይ ናቸው። ... {1MCP 232.3} 1MCPAmh 191.5
ከውኃ ጥፋት በፊት በሜዳማ ቦታዎች ላይ የነበሩ ከተሞችን ያጠፉ ኃጢአቶች ዛሬም አሉ። እነዚህ ኃጢአቶች ያሉት በአህዛብ አገሮች ወይም ክርስትናን እንከተላለን በሚሉ ታዋቂ ሰዎች መካከል ብቻ ሳይሆን የእግዚአብሔርን ልጅ መገለጥ እንጠብቃለን በሚሉ ሰዎች መካከልም ነው። እግዚአብሔር እነዚህ ኃጢአቶች በእርሱ ፊት በሚታዩበት መልክ በፊታችሁ ቢያቀርብላችሁ ኖሮ በሀፍረትና በሽብር ትሞሉ ነበር። --5T 218 (1882). {1MCP 232.4} 1MCPAmh 191.6
ብርሃንን ላለማየት ዓይኖችን መጨፈን።--እጅግ የወረዱ የፍቅር ስሜቶችን መፈጸም ብዙዎች ብርሃንን ላለማየት ዓይኖቻቸውን እንዲጨፍኑ ይመራቸዋል፤ ይህን የሚያደርጉት ለመተው ፈቃደኛ ያልሆኑ ኃጢአቶችን ለማየት ስለሚፈሩ ነው። ፈቃደኞች ከሆኑ ሁሉም ማየት ይችላሉ። ከብርሃን ይልቅ ጨለማን ከመረጡ ወንጀለኛነታቸውም በዚያው ልክ ይሆናል። {1MCP 232.5} 1MCPAmh 192.1
ወንዶችም ሆኑ ሴቶች የአካል፣ የአእምሮና የግብረገብ ብርታታቸውን በማያዳግም ሁኔታ የሚጎዱትን እነዚህን ነገሮች በተመለከተ በማንበብ አዋቂዎች የማይሆኑት ለምንድን ነው? እግዚአብሔር እንድትጠብቁትና ለእርሱ አገልግሎትና ክብር በተሻለ ሁኔታ እንድታቆዩት አካልን ሰጥቶአችኋል። አካሎቻችሁ የራሳችሁ አይደሉም። --2T 352 (1885). {1MCP 233.1 1MCPAmh 192.2
(ሐ) ሚዛንና ድል (የቃል ኪዳንና የተስፋ ቃላት) 1MCPAmh 192.3
ልባዊ የሆነ ንስሃና ቆራጥ ጥረት አስፈላጊ ነው።--የራሳቸውን አካል የሚያበላሹ ሰዎች ከልባቸው ተናዝዘው ሙሉ ተሃድሶ እስኪያደርጉና እግዚአብሔርን በመፍራት ቅድስናን እስኪፈጽሙ ድረስ እግዚአብሔር ያደረገላቸው መልካም ነገር አያስደስታቸውም። --AM 29 (1864). {1MCP 233.2} 1MCPAmh 192.4
መጥፎ ልማዶችን እየተለማመዱ ያሉ ሰዎች፣ በዚህች ምድር ላይ ለጤንነታቸው እና በሚመጣው ዓለም ደግሞ ለሚያገኙት ድነት ዋጋ የሚሰጡ ከሆነ፣ ያላቸው ብቸኛው ተስፋ እነዚህን ክፉ ልማዶች ለዘላለም መተው ነው። እነዚህ ልማዶች ረዘም ላለ ጊዜ እየተፈጸሙ ከቆዩ፣ ፈተናን ለመቋቋምና ብልሹ ድርጊትን ላለመፈጸም ቆራጥ የሆነ ጥረትን ይጠይቃል። --AM 27 (1864). {1MCP 233.3} 1MCPAmh 192.5
በዓይነ ህሊና የማየት ችሎታን ተቆጣጠሩ።--ጠንካራ የሆኑ የፍቅር ስሜቶች ለማገናዘብ ችሎታ፣ ለህሊና እና ለባሕርይ መገዛት ካለባቸው፣ የማሰብ ችሎታ በአዎንታዊነትና በቀጣይነት ቁጥጥር ሊደረግበት ይገባል። --2T 562 (1870). {1MCP 233.4} 1MCPAmh 192.6
ለእግዚአብሔር ፈቃድ ተገዥ የሆነ።--ክርስቲያን መሆን ስለሚያቅፋቸው ነገሮች እውነተኛ የሆነ ስሜት ያላቸው ሁሉ የክርስቶስ ተከታዮች የፍቅር ስሜቶቻቸውን፣ አካላዊና አእምሮአዊ ችሎታዎቻቸውን ሁሉ እንደ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ለእርሱ ፈቃድ ፍጹም የማስገዛት ግዴታ እንዳለባቸው ያውቃሉ። ስሜቶቻቸው የሚቆጣጠሩአቸው ሰዎች የክርስቶስ ተከታዮች መሆን አይችሉም። የተበላሹ ልማዶቻቸውን ለመተውና የክርስቶስን አገልግሎት ለመምረጥ እስከማይችሉ ድረስ የክፋት ሁሉ መስራች የሆነውን ጌታቸውን ለማገልገል ራሳቸውን ሰጥተዋል። -- AM 9, 10, 1864. (CG 445, 446.) {1MCP 233.5} 1MCPAmh 192.7
ሀሳብ በጣም ወሳኝ ነገር።--ንጹህ ያልሆኑ ሀሳቦች ንጹህ ወዳልሆኑ ተግባሮች ይመራሉ። ክርስቶስ የምናሰላስልበት ዋና ጉዳይ የሚሆን ከሆነ ሀሳቦች እርኩስ ወደ ሆነ ተግባር ከሚመራ ከእያንዳንዱ ርዕስ ሰፊ በሆነ ሁኔታ ይለያሉ። አእምሮ ከፍ በሚያደርጉ ሀሳቦች ላይ በማተኮር ይበረታታል። በንጽህናና በቅድስና መስመር እንዲሄድ ከሰለጠነ ጤናማና ብርቱ ይሆናል። መንፈሳዊ በሆኑ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ እንዲያተኩር ከሰለጠነ ተፈጥሮአዊ በሆነ ሁኔታ ያንኑ መስመር ይይዛል። ነገር ግን በእግዚአብሔር ላይ ያለውን እምነት ሳይለማመዱና ለእያንዳንዱ አስቸኳይ ሁኔታ በቂ የሚሆነውን ብርታትና ጸጋ ለማግኘት በእርሱ ላይ በጽናትና በትህትና ሳይደገፉ ሀሳብን ወደ ሰማያዊ ነገሮች መሳብ ሊገኝ አይችልም። --2T 408 (1870). {1MCP 234.1} 1MCPAmh 193.1
የመቃዠት ኃጢአት።--ስለምታስባቸው ሀሳቦች በእግዚአብሔር ዘንድ ሀላፊነት አለብህ። አእምሮህ ንጹህ ባልሆኑ ርዕሶች ላይ እንዲያተኩር በመፍቀድ ከንቱ የሆኑ ሀሳቦችን የምታስብ ከሆንክ ሀሳቦችህ በተግባር የተተረጎሙትን ያህል በከፍተኛ ደረጃ በእግዚአብሔር ፊት በደለኛ ነህ። ወደ ተግባር እንዳይቀየር የሚያደርገው ዕድሉ አለመገኘት ብቻ ነው። --2T 561 (1870). {1MCP 234.2} 1MCPAmh 193.2
አስተሳሰቦችን በቁጥጥር ሥር አድርጉ።--ሀሳቦቻችሁን መቆጣጠር አለባችሁ። ይህ ቀላል ሥራ አይሆንም፤ ቅርበት ባለውና ጥብቅ በሆነ ጥረት ካልሆነ በስተቀር ልትፈጽሙት አትችሉም። . . . {1MCP 234.3} 1MCPAmh 193.3
እግዚአብሔር የሚፈልግባችሁ ሀሳቦቻችሁን ብቻ ሳይሆን ስሜቶቻችሁንና ፍቅራችሁንም እንድትቆጣጠሩ ነው። ድነታችሁ እነዚህን ነገሮች በተመለከተ ራሳችሁን በመቆጣጠራችሁ ላይ ይደገፋል። ጠንካራ የሆኑ የፍቅር ስሜቶች ኃይለኛ ወኪሎች ናቸው። በስህተት ጥቅም ላይ ከዋሉ፣ ስህተት ከሆነ ምክንያት በመነሳት ሥራ ላይ ከዋሉ፣ ያለ ቦታቸው ከተቀመጡ፣ ያለ እግዚአብሔርና ያለ ተስፋ በማድረግ ጥፋታችሁን ለመፈጸምና አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ ከጥቅም ውጭ ሊያደርጉአችሁ እስከሚችሉ ድረስ ኃይለኛ ናቸው። --2T 561 (1870). {1MCP 234.4} 1MCPAmh 193.4
በውስጣችን ይዘን ያስተናገድናቸው ሀሳቦች ልማድ ይሆናሉ።--በውስጥ ያስተናገድናቸው የተበከሉ ሀሳቦች ልማድ ይሆናል፣ ነፍስም ጠባሳ ያለውና የረከሰ ይሆናሉ። አንድ ጊዜ የስህተት ተግባር ከተፈጸመ ከክርስቶስ ደም በስተቀር ምንም ሊያድነው የማይችል ነቁጣ ይፈጠራል፤ ልማድ በጽኑ ቁርጠኝነት ካልተቀየረ በቀር ነፍስ ትበላሻለች፣ ከዚህ ከሚበክል ምንጭ የሚፈሱ ጅረቶች ሌሎችን ያበላሻሉ። --Lt 26d, 1887. (HP 197.) {1MCP 235.1} 1MCPAmh 194.1
በትክክል ቁጥጥር የተደረገባቸው አስተሳሰቦች።-- አስተሳሰቦቻችንን በትክክል መቆጣጠር አእምሮንና ነፍስን ከጌታ ጋር በተጣጣመ ሁኔታ አብሮ ለመስራት ስለሚያዘጋጅ ለዚህ ሥራ ከፍተኛ ዋጋ መስጠት አለብን። ለአስተሳሰቦቻችን ክርስቶስን ማዕከል ማድረግ በዚህ ሕይወት ላለን ሰላምና ደስታ አስፈላጊ ነው። ሰው የሚሆነው እንደሚያስበው ነው። በግብረገብ ንጽህናችን የምናሳየው መሻሻል ትክክለኛ በሆነ ሀሳብና ትክክለኛ በሆነ ድርጊት ይደገፋል። . . . {1MCP 235.2} 1MCPAmh 194.2
ክፉ ሀሳቦች ነፍስን ያጠፋሉ።--የሚለውጠው የእግዚአብሔር ኃይል ሀሳቦችን በማጥራትና በማንጻት ልብን ይለውጣል። ሀሳቦች በክርስቶስ ላይ እንዲያተኩሩ ቁርጠኛ የሆነ ጥረት ካልተደረገ በቀር ጸጋ በሕይወት ውስጥ ራሱን ማሳየት አይችልም። አእምሮ በመንፈሳዊ ጦርነት ላይ መጠመድ አለበት። እያንዳንዱ ሀሳብ ለክርስቶስ ለመታዘዝ መማረክ አለበት። ልማዶች ሁሉ በእግዚአብሔር ቁጥጥር ሥር መሆን አለባቸው። {1MCP 235.3} 1MCPAmh 194.3
የንጹህ ሀሳቦች ክቡር የማድረግ ኃይልና የክፉ ሀሳቦች ጉዳት የማድረስ ተጽእኖ ሁል ጊዜ ሊሰማን ይገባል። ሀሳቦቻችንን ቅዱስ በሆኑ ነገሮች ላይ እናድርግ። ለማንኛውም ነፍስ ያለው ብቸኛው ደህንነት ትክክለኛ የሆነ አስተሳሰብ ስለሆነ አስተሳሰቦች ንጹህና እውነተኛ ይሁኑ። አስተሳሰቦቻችንን ለመግዛትና ለማሳደግ እግዚአብሔር በአጠገባችን ያስቀመጠልንን እያንዳንዱን ዘዴ መጠቀም አለብን። አእምሮአችን ከእርሱ አእምሮ ጋር እንዲጣጣም እናድርግ። የእርሱ እውነተኛ ፈቃድ እኛን፣ አካልን፣ ነፍስንና መንፈስን ስለሚቀድስ ከፈተናዎች በላይ እንድንሆን ያደርገናል። --Lt 123, 1904. (HP 164.) {1MCP 235.4} 1MCPAmh 194.4
አመጋገብ ወሳኝ ነገር።--ብዙ ጊዜ ወደ ሆድ የሚገባው ማንኛውም ነገር አካልን ብቻ ሳይሆን በመጨረሻ አእምሮንም ይነካል የሚለው አባባል እጅግ በጣም እንደተደጋገመ ሊነገር አይችልም። ጥራት የሌለውና አነቃቂ ምግብ ደምን ያፈላል፣ የነርቭ ስርዓትን ያነቃቃል፣ ብዙ ጊዜ የማገናዘብ ችሎታና ህሊና በፍትወት ስሜቶች እስኪወሰዱ ድረስ የሞራል እይታን ያደድባል። በአመጋገቡ መሻቱን ለማይገዛ ሰው ትዕግስተኛ መሆንና ራስን መቆጣጠር ከባድና ብዙ ጊዜ የማይቻል ነው። --CTBH 134, 1890. (CG 461.) {1MCP 235.5} 1MCPAmh 194.5
ሥጋ የወረዱ የፍቅር ስሜቶችን ይቀሰቅሳል፣ ያጠነክራልም።--ሥጋ በልጆቻችን ፊት መቀመጥ የለበትም። የእርሱ ተጽእኖ የወረዱ ስሜቶችን መቀስቀስና ማጠናከር ስለሆነ የግብረገብ ኃይሎችን ሙት የማድረግ ዝንባሌ አለው። በተቻለ መጠን ተፈጥሮአዊ ሁኔታቸው ሳይቀየር፣ ያለ ቅባት የተዘጋጁ ጥራጥሬዎችና ፍራፍሬዎች ወደ ሰማይ ለመነጠቅ እየተዘጋጁ ባሉ ሰዎች ጠረጴዛ ላይ የሚቀርቡ ምግቦች መሆን አለባቸው። ምግቡ ሰውነትን የማተኮስ አቅሙ አነስተኛ ሲሆን ስሜቶችን በቀላሉ መቆጣጠር ይቻላል። የአካል፣ የአእምሮ ወይም የግብረገብ ጤና ችላ ተብሎ የምግብ ጣዕምን ማርካት አይመከርም።--2T 352 (1869). {1MCP 236.1} 1MCPAmh 195.1
ፈተናን ግደሉት።--የወረዱ ስሜቶች መቀመጫቸው በሰውነት ውስጥ ስለሆነ በእርሱ አማካይነት ይሰራሉ። የሥጋ፣ ሥጋዊ ወይም አለማዊ ፍትወቶች የሚሉ ቃላት የወረደ፣ የተበላሸ ተፈጥሮን ያካትታሉ፤ ሥጋ በራሱ ከእግዚአብሔር ፈቃድ በተቃራኒ አይሰራም። ሥጋን ከከፉ መሻቱና ምኞቱ ጋር እንድንሰቅል ተመክረናል። ይህን እንዴት ነው ማድረግ የምንችለው? አካላችንን ማሰቃየት አለብን ማለት ነው? አይደለም፤ ነገር ግን ኃጢአትን እንድንሰራ የሚያደርገንን ፈተና መግደል ማለት ነው። {1MCP 236.2} 1MCPAmh 195.2
የተበላሸ አሳብ መወገድ አለበት።--እያንዳንዱ አሳብ የኢየሱስ ክርስቶስ ምርኮኛ መሆን አለበት። ሁሉም ተፈጥሮአዊ የሆኑ እንስሳዊ ዝንባሌዎች ከፍ ላሉ የነፍስ ኃይሎች መገዛት አለባቸው። የእግዚአብሔር ፍቅር የበላይነት ቦታን መያዝ አለበት፤ ክርስቶስ ያልተከፋፈለ ዙፋንን መያዝ አለበት። አካሎቻችን እርሱ የገዛቸው ንብረቶች እንደሆኑ ተደርገው መታየት አለባቸው። የአካል ክፍሎች የጽድቅ መሳሪያዎች መሆን አለባቸው። -- MS 1, 1888. (AH 127, 128.) {1MCP 236.3} 1MCPAmh 195.3
ንጹህ ያልሆኑ አስተያየቶችን ንጹህና ከፍ በሚያደርጉ አሳቦች ለውጡ።--አእምሮ ንጹህና ቅዱስ በሆኑ ርዕሶች ላይ እንዲያሰላስል መደረግ አለበት። ንጹህ ያልሆነ አስተያየት ወዲያውኑ ተቀባይነት እንዳያገኝ ተደርጎ ንጹህ፣ ከፍ የሚያደርጉ ሀሳቦችና ቅዱስ ምርምር መስተናገድ አለበት፣ በዚህ መልኩ አእምሮ ሰማያዊ በሆኑ ነገሮች ላይ እንዲያሰላስል በማሰልጠን ስለ እግዚአብሔር የበለጠ እውቀት ማግኘት ይቻላል። እያንዳንዱ ግለሰብ ታላቁን ፍጻሜ፣ የነፍስን ድነት፣ እንዲያገኝ እግዚአብሔር ቀላል የሆነ፣ በቂ መንገድ አዘጋጅቷል። {1MCP 236.4} 1MCPAmh 195.4
ከፍ ያለና ቅዱስ መስፈርት ላይ ለመድረስ ወስን፤ ዳንኤል እንዳደረገው በእርጋታ፣ ተግቶ በመሥራት፣ ጽኑ በሆነ ዓላማ ሥራ፤ ይህን ካደረግክ ጠላት ማድረግ የሚችለው ምንም ነገር ቢሆን እንዳትሻሻል መከልከል አይችልም። የሚያጋጥሙህ አለመመቻት፣ ለውጦችና ግራ መጋባቶች እንዳሉ ሆነው በአእምሮ ብርታትና በግብረገብ ኃይል ያለ ማቋረጥ ማደግ ትችላለህ።--Lt 26d, 1887. (HP 197.) {1MCP 237.1} 1MCPAmh 196.1
አንገብጋቢ ሁኔታን አትፍጠሩ።--እያንዳንዱ ቅዱስ ያልሆነ ስሜት በእያንዳንዱ አንገብጋቢ ሁኔታ ውስጥ እግዚአብሔር አትረፍርፎ በሚሰጠው ጸጋ አማካይነት ቅዱስ በሆነ የማገናዘብ ችሎታ ሥር መሆን አለበት። ነገር ግን አንገብጋቢ ሁኔታን ለመፍጠር ምንም ዓይነት ዝግጅት መደረግ የለበትም፣ አንድን ግለሰብ የፈተና ጥቃት በሚደርስበት ቦታ ወይም ሌሎች የንህዝላልነት በደል እንዳለበት በሚያስቡበት ቦታ የሚያስቀምጥ ከሁሉ ዝቅተኛ የሆነ አጋጣሚ ለመፍጠር በገዛ ፈቃድ የሚፈጸም ተግባርም አይኑር። --Lt 18, 1891. {1MCP 237.2} 1MCPAmh 196.2
ከገደል አፋፍ ራቁ።--በገደል አፋፍ ምን ያህል ተጠግተህ መሄድ እንደምትችልና ከአደጋ ነጻ እንደምትሆን አትይ። አስቀድመህ ወደ አደጋ መቅረብን ሽሽ። የነፍስ ጉዳይ ላይ መቀለድ አይቻልም። ዋና ንብረትህ ባህርይህ ነው። የወርቅ ሀብትን እንደምትንከባከብ ተንከባከበው። የሞራል ንጽህና፣ ለራስ ያለህ አክብሮት፣ ጠንካራ የሆነ የመቋቋም ኃይል በጽናትና ያለማቋረጥ እንክብካቤ ሊደረግለት ይገባል። . . . {1MCP 237.3} 1MCPAmh 196.3
ማንም ሰው ያለ እግዚአብሔር እርዳታ ማሸነፍ እንደሚችል አያስብ። የውስጥ ሕይወት ጉልበት፣ ብርታት፣ ኃይል በውስጣችሁ ማደግ አለበት። ያኔ እግዚአብሔርን የመምሰል ፍሬ ታፈሩና ክፋትን አጥብቃችሁ ትጠላላችሁ። ከምድራዊነት፣ ርካሽ ከሆነ ንግግር፣ ፍትወት ከሆነ ነገር ሁሉ ለመራቅ ያለ ማቋረጥ ጥረት እያደረጋችሁ የነፍስ ክቡርነትን እና ንጹህና እንከን የለሽ ባሕርይን ለማግኘት አልሙ። ስማችሁ ከማንኛውም ታማኝ ካልሆነ ወይም ኃጢአተኛ ከሆነ ነገር ጋር መገናኘት እስከማይችል ድረስ እጅግ ንጹህ ሆኖ ሊጠበቅ ከመቻሉም በላይ መልካምና ንጹህ በሆኑት ሁሉ ሊከበርና በበጉ የሕይወት መጽሐፍ ሊጻፍ ይችላል። -- MS 4a, 1885. (MM 143, 144.) {1MCP 237.4} 1MCPAmh 196.4
የሚቆጣጠረው ሰይጣን ወይም ክርስቶስ ነው።--አእምሮ በቀጥታ በእግዚአብሔር መንፈስ ተጽእኖ ሥር በማይሆንበት ጊዜ ሰይጣን በመረጠው መንገድ ሊቀርጸው ይችላል። የሚቆጣጠራቸውን የሚያገናዝቡ ኃይሎችን ሁሉ ሥጋዊ ያደርጋቸዋል። እግዚአብሔርንና የእርሱን ምርጫዎች፣ አመለካከቶች፣ የሚወዳቸውንና የሚጠላቸውን ነገሮች፣ የሚመርጣቸውን ነገሮችና ሥራዎቹን በቀጥታ ይቃወማል፤ እግዚአብሔር ለሚወዳቸው ወይም ማረጋገጫ ለሚሰጣቸው ነገሮች ፍቅር የለውም፣ ነገር ግን እርሱ በሚጠላቸው ነገሮች ይደሰታል።. . . {1MCP 238.1} 1MCPAmh 196.5
ክርስቶስ በልብ ውስጥ የሚኖር ከሆነ በሀሳቦቻችን ሁሉ ውስጥ ይሆናል። ጥልቅ ሀሳቦቻችን ስለ እርሱ፣ ስለ እርሱ ፍቅርና ንጽህና ማሰብ ይሆናሉ። እርሱ ሁሉንም የአእምሮ ክፍሎች ይሞላል። የፍቅራችን ማዕከል ኢየሱስ ይሆናል። ተስፋዎቻችንና ይሆናሉ ብለን የምንጠብቃቸው ነገሮች ሁሉ ከእርሱ ጋር የተገናኙ ይሆናሉ። አሁን በእግዚአብሔር ልጅ ባለን እምነት የምንኖረውን ሕይወት ለመኖር፣ ወደ ፊት መመልከትና የእርሱን መገለጥ መውደድ፣ የነፍስ ከፍተኛ ደስታ ይሆናል። እርሱ የደስታችን ዘውድ ይሆናል። --Lt 8, 1891. (HP 163.) {1MCP 238.2} 1MCPAmh 197.1
የእድሜ ልክ ንቃት።--በሕይወት እስካለን ድረስ የፍቅር ስሜቶቻችንንና ፍላጎቶቻችንን ጥብቅ በሆነ ዓላማ መጠበቅ ያስፈልጋል። የውስጥ ብልሽት አለ፣ የውጭ ፈተናዎች አሉ፣ የእግዚአብሔር ሥራ ወደፊት በሚገሰግስበት ሁሉ ፈተና ነፍስን ለማሸነፍ በሚችልበት ኃይል ሊመጣ የሚችልባቸውን ሁኔታዎች ለማዘጋጀት ሰይጣን ያቅዳል። በእግዚአብሔር ላይ ብቻ ካልታመንንና ሕይወታችን ከክርስቶስ ጋር በእግዚአብሔር ውስጥ ካልተደበቀ በቀር ለአፍታ እንኳን ከአደጋ ነፃ መሆን አንችልም። --Lt 8b, 1891. (2BC 1032.) {1MCP 238.3} 1MCPAmh 197.2
እግዚአብሔር ሕዝቡን እያዘጋጀ ነው።--የእግዚአብሔር ሕዝብ የእርሱን ፈቃድ ማወቅ ብቻ ሳይሆን በሥራ ላይ ማዋልም አለባቸው። እውነትን ከሚያውቁ ሰዎች መካከል ብዙዎች በእውነት ስላልተቀደሱ ይወገዳሉ። እውነት በግል ሕይወታቸው ከምድራዊነትና ከፍትወተኛነት ሊቀድሳቸውና ሊያነጻቸው ወደ ልባቸው መምጣት አለበት። የነፍስ መቅደስ መንጻት አለበት። እያንዳንዱ የምስጢር ተግባር በእግዚአብሔርና በቅዱሳን መላእክት ፊት፣ ሁሉም ነገር በፊቱ ግልጽ በሆነ እና ምንም ነገር ከእርሱ ሊደበቅ በማይችል አምላክ ፊት እንዳለ ነገር ነው። . . . {1MCP 238.4} 1MCPAmh 197.3
ሰዎች በፍርድ ቀን ንጹህ እጆችና ንጹህ ልቦች እንዲኖሩአቸው እግዚአብሔር ሕዝቡን እያነጻ ነው። መስፈርቱ ከፍ ማለት አለበት፣ አስተሳሰብ መንጻት አለበት፤ አዋራጅ በሆኑ ልምምዶች ዙሪያ እየተሰበሰበ ያለው የወረት ፍቅር መተው አለበት፣ ነፍስ ወደ ንጹህ ሀሳቦችና ቅዱስ ልምምዶች ከፍ ማለት አለበት። ከፊታችን እየጠበቀን ባለው ፈተናና ችግር የሚቆሙ ሁሉ በፍትወት አማካይነት በዓለም ውስጥ ካሉ እርኩሰቶች በማምለጥና ባለመሳተፍ የመለኮታዊ ባህርይ ተካፋዮች ይሆናሉ። --RH, May 24, 1887. {1MCP 239.1} 1MCPAmh 197.4