የተሟላ ኑሮ

125/201

“በአፋዊ ሥራ አይደለም”

የእግዚአብሔር መንግስት የሚገኝ በአፋዊ ሥራ አይደለም፡፡ የሚገኘው ውስጣዊ ሰውነታችን በመንፈስ ቅዱስ ሲነካ፤ በእግዚአብሔር ቃል አነሳሽነት ሙሉ ሰውነታችን ሲመለስ፤ ነፍሳችን ከሕይወታችን ጌታ ጋር ሲተሳሰር ብቻ ነው፡፡ CLAmh 133.5

የክርስቶስ ተከታዮች የዓለም ብርሃን መሆን አለባቸው፡፡ እግዚአብሔር ግን የራሳቸውን ብርሃን እንዲያበሩ አላዘዛቸውም፡፡ CLAmh 133.6

የራሳቸውን ደግነት በመግለጥ ከሁሉ የበለጡ ደጎች መሆናቸው እንዲገልጡ አይፈልግም፡፡ ሕይወታቸው በሰማይ ሥነ ሥርዓት እንዲመራ ይፈልጋል፡፡ ከዓለም ጋር ሲገናኙ ብርሃናቸውን ለሌሎች ሊያሳዩ ይችላሉ፡፡ በዕምነታቸው ጸንተው ሲገኙ ብርሃቸውን አበሩ ማለት ነው፡፡ CLAmh 134.1

የእግዚአብሔርን ሥራ ወደፊት ለማራመድ ማዕረግ፣ ሐብት፣ ውድ መሣሪያዎች፣ የሚደሉ የቤት ዕቃዎች አገልግሎታቸው አጭር ነው፡፡ በሰው ዘንድ አድናቆትን የሚያስገኝ ክንውንነትና ያስተዳደር ችሎታም ብቻውን ለወንጌል ሥራ ከንቱ ነው፡፡ CLAmh 134.2

የዓለም ጌጣጌጥና ትርፍ በእግዚአብሔር ዘንድ ዋጋ የለውም፡፤ በእርሱ ዘንድ ከሚታየውና ከምድራዊ ይልቅ የማይታየውና ዘለዓለማዊው ከፍተኛ ዋጋ አለው፡፡ CLAmh 134.3

ምድራዊና የሚታየው ሰማያዊውንና የማይታየውን ሲደግፍ ብቻ ያን ጊዜ ዋጋ ይኖረዋል፡፡ የታወቀ ሰዓሊ የሳለው ግሩም ሥዕል ውበቱ በመንፈስ ቅዱስ ካጌጠ ጠባይ ውበት ጋር አይስተካከልም፡፡ እግዚአብሔር ልጁን ወደ ዓለም ሲልክ በማይጠፋ ሀብት አበለጸገን፡፡ ያ ሀብት ከዓለም ሁሉ ሀብት ጋር ቢመዛዘን የዓለምን ሀብት እንደሌለ ያስቆጥረዋል፡፡ CLAmh 134.4

የሱስ ወደ ዓለም መጥቶ በዘለዓለም ፍቅር በሰዎች ልጆች ፊት ቆመ፡፡ ከእርሱ ጋር በምናደርገው ግንኙነት ሊኖረን፤ ልንቀበለው፤ ልናስተላልፈውና ለሌሎች ልንሰጠው የሚገባን የከበረ ሀብት ይህ ነው፡፡ CLAmh 134.5

የሰብዓዊ ፍጡር ጥረት ለወንጌል ሥራ ተቀባይነት የሚኖረው ሠራተኛው ራሱን በሙሉ ለጌታ ሲያስረክብና የክርስቶስን ኃይል ሲገልጥ ብቻ ነው፡፡ ከዓለም የምንለየው እግዚአብሔር ማኅተሙን ሲያትምብን፤ የራሱን የፍቅር ባሕሪይ በእኛ አማካይነት ለሌሎች ሲገልጥ ነው፡፡ አዳኛችን በጽድቁ ያጎናጽፈናል፡፡ CLAmh 134.6

እግዚአብሔር ለሥራው የሚመርጣቸው ሰዎች ሀብታም፣ የተማሩ፣ ንግግር አዋቂዎች የመሆን ግዴታ የለባቸውም፡፡ ቃሌን በከናፍራቸው ላስተላልፍ እችላለሁ? እኔን ሊወክሉ ይችላሉ? ከእኔ ለመማር ትሁታን ናቸው? ብሎ ይጠይቃል፡፡ CLAmh 134.7

እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ ሰው መንፈሱን ያደለውን ያህል ሊያሠራው ይችላል፡፡ በእርሱ ዘንድ ተቀባይነት የሚኖረው ሥራ እርሱነቱን የሚገልጥ ሥራ ነው፡፡ አገልጋዮቹ ሊኖራቸው የሚገባው ማዕረግ በማይሻረው ደንቡ የሚገልጠውን የማይለወጥ ባሕርይውን ነው፡፡ የሱስ በከተማዎች አውራ መንገዶች እየዞረ ሲያገለግል እናቶች በጠና የታመሙ ልጆቻቸውን እየያዙ ወደ እርሱ ይጎርፉ ነበር፡፡ እንዲያያቸውና የርዳታ እጁን እንዲዘረጋላቸው ምኞታቸው ነበር፡፡ CLAmh 134.8