የተሟላ ኑሮ

95/201

19—ቀላል ፈውስ

በሽታ ያለምክንያት አይመጣም፡፡ በሽታ የጤናን ሕግ ባለመጠበቅ መንገዱ ሲጠረግለት ከተፍ ይላል፡፡ ብዙዎች በወላጆቻቸው ጥፋት ይሰቃያሉ፤ ምንም እንኳን በወላጆቻቸው ጥፋት ቢደርስባቸው የጤናን ሕግ ተቃራኒ ለይተው ማወቅ ይኖርባቸዋል፡፡ የወላጆቻቸውን መጥፎ ልማድ እንደጨርቅ አውልቀው በመጣል ራሳቸውን በመልካም ይዞታ ይጠብቁ፡፡ CLAmh 97.4

ግን በቁጥር የሚበዙት በራሳቸው ጥፋት ይጎዳሉ፡፡ የጤናን ደንብ በአለባበስ፤ በአመጋገብና በመጠጥ ችላ ይሉታል፡፡ የተፈጥሮን ሕግ በመተላለፍ የማይቀር ችግር ይደርስባቸዋል፡፡ በበሽታ ሲለከፉ ብዙዎች የነገሩን ዕውነተኛ መነሻ በመዘንጋት ስለደረሰባቸው ሥቃይ እግዚአብሔርን ያማርራሉ፡፡ ግን የተፈጥሮን ሕግ ተላልፈው ለደረሰባቸው ሕመም እግዚአብሔር ኃላፊነት የለበትም፡፡ እግዚአብሔር የተወሰነ ኃይል አድሎናል፡፡ ደግሞም የኑሮን አቋም ሊጋፈጡ የሚችሉ የአካላት ክፍሎች ፈጥሮልናል፡፡ እነዚህ የአካል ክፍሎችም በኅብረት እንዲሠሩ ታቅዶላቸዋል፡፤ የተሰጠንን ኃይል ብንንከባከበው ግሩም የሆኑትን አካል ክፍሎች በሥርዓት ብንጠብቃቸው ጤናማዎች እንሆናለን፡፡ ግን ኃይላችን ያለአግባብ ከተበዘበዘ ነርቮቻችን ከተቀማጩ ኃይል ሥራቸውን የሚያካሂዱበት ጉልበት ይወስዳሉ፤ አንድ የአካል ክፍል ከተጎዳ ጠቅላላው አካል ይነካል፡፡ ስነ ፍጥረት በቂ መከላከያ ሳይኖራት ለአደጋ ትጋለጣለች፤ የመጣባትን በሽታ ለመከላከል ከአቅሟ በላይ ትሠራለች፡፡ ይህን ከፍተኛ ሥራ ስታከናውን ድካሟ በትኩሳት ወይም በሌላ ሕመም አማካይነት ይገለጣል፡፤ CLAmh 97.5

ጤና ተጎሳቁሎ በሽታ ሲጠና በሽተኛው ሌላ ሰው ሊሠራለት የማይችለውን የግሉን ሥራ መሥራት አለበት፤ መጀመሪያ የበሽታውን ምንነት ለይቶ ማወቅ ያስፈልጋል፤ ከዚያም ለሕመሙ ጠንቅ የሆነውን ነገር መተው ያስፈልጋል፡፡ ጤናህ የታወከው በሥራ ብዛት፣ በምግብ ወይም በመጠጥ ብዛት ወይም ደግሞ በሌላ ከሥርዓት ውጭ በሆነ ነገር ከሆነ ጤናህን በመድኃኒት ለማስተካከል በመሞከር አካልህን በመርዝ አትጉዳው፡፡ CLAmh 98.1