የተሟላ ኑሮ
ጠቃሚ የፍቅር ኃይል
ወንጌል በሙሉ ልብ ተቀባይነት ካገኘ በኃጢአት መዘዝ ከመጡት በሽታዎች ሁሉ ይፈወሳል፡፡ “የጽድቅ ጸሐይ ፈውስ በክንፎቹ ውስጥ ይሆናል፡፡” (ሚልክያስ 4፡2) የዚህ ዓለም ቅርስና ሀብት ያዘነን ልብ ሊያጽናና፤ የአእምሮ ሰላም ሊሰጥ፤ ወይም ጭንቀትንና በሽታን ሊያግድ አይችልም፡፡ ዝና፣ ጥበብ፣ አስተዋይነት ያዘነን ልብ ለማስደሰት ወይም የተጎሳቈለውን ሕይወት ለመጠገን ኃይል የላቸውም፡፡ ሰው ተስፋ የሚኖረው የእግዚአብሔር ሕይወት በውስጡ ሲያድር ብቻ ነው፡፤ CLAmh 96.4
ክርስቶስ ለሰዎች የሚሰጠው ፍቅር ጠቃሚ ኃይል ነው፡፡ አእምሮን፣ ልብን፣ ነርቮችን በፍቅሩ ይነካቸዋል፡፡ በእርሱ አማካይነት የሰውየው ሙሉ ኃይል ለሥራ ይሰለፋል፡፤ መንፈስን ከሚደመስሱት ከኀዘን፣ ከጭንቀት፣ ሰውየውን ነፃ ያወጣዋል፡፡ ኃይና ብርታት ይሰጠናል፤ ምንም ምድራዊ ነገር ሲሽረው የማይችል፤ ጤና ሰጭ፤ ሕይወት ሰጭ የመንፈስ ቅዱስ ደስታ ይሰጠናል፡፡ CLAmh 96.5
“ኑ እላንት ደካሞች ዕረፍት እሰጣችኋለሁ” የሚለው የጌታ ቃል ለአካል፣ ለአእምሮ፣ ለመንፈስ ፈውስ ነው፡፡ CLAmh 97.1
ምንም እንኳን ሰዎች በጥፋታቸው ታማሚዎች ቢሆኑ እግዚአብሔር ያዝንላቸዋል፡፡ ከእርሱ ዘንድ እርዳታ ሊያገኙ ይችላሉ፡፡ CLAmh 97.2
ለሚያምኑበት ትልቅ ነገር ያደርግላቸዋል፡፡ ለብዙ ዘመናት ኃጢአት በሰብአዊ ዘር ውስጥ ሥር ሰዶአል፡፡ የእግዚአብሔርን ቃል አጣሞ በመተርጎም ጥላውን ጥሎበታል፡፡ ቢሆንም የአብ ፍቅርና ምሕረት ወደ ምድር ከመፍሰስ አልተቋረጠም፡፡ ሰብአዊ ፍጡር በፈቃደኝነት የነፍሳቸውን መስኮት ቢከፍቱ የፈውስ ጠል ሳያቋርጥ በዘነበላቸው ነበር፡፡ CLAmh 97.3