የተሟላ ኑሮ
ክርስቶስ ተስፋችን
ኃይሉና ፈቃዱ ቢዳከምም በክርስቶስ ተስፋ አለው፡፡ በልቡ መልካም ምኞትና ቅዱስ ተስፋ ያሳድርበታል፡፡ በወንጌል የተሰጠውን ተስፋ እንዲያምንበት አስረዱት፡፡ (አደፋፍሩት)፡፡ ለተፈተነው ሰው መጽሐፍ ቅዱስን ደጋግማችሁ አስረዱት፤ አንብቡለትም፡፤ የእግዚአብሔር ተስፋ እንደ ሕይወት ዛፍ ቅጠል መድኃኒት ይሆንለታል፡፡ CLAmh 88.3
ያ የተፈታኙ እጅ የክርስቶስን እጅ በደስታ እስኪጨብጥ ድረስ ጥረትህን አታቋርጥ፡፡ ልትረዳው የምትሞክረውን ሰው አጥብቀህ ካልያዝህ ድል ያንተ አይሆንም፡፡ በየጊዜው ፈተና ይበረታባቸዋል፡፡ በመጠጥ ሱስ ይሸነፋሉ፡፤ በየጊዜውም ይወድቁ ይሆናል፡፡ ሆኖም ጥረትህን አታቋርጥ፡፡ CLAmh 88.4
ከክርስቶስ ጋር ለመኖር ምኞት አላቸው፤ ግን ኃይላቸው ስለደከመ ይጠቃሉ፡፡ ግን ነፍሳትን የመጠበቅ ግዴታ ያለባቸው ሰዎች በጥንቃቄ ሊጠብቋቸው ይገባል፡፡ CLAmh 88.5
የጠፋውን ሰውነታቸውን እንደገና ማስመለስ ይገባል፤ ማረም ያሻቸዋል፡፤ ያልተወሰነ ሱስ፣ መጥፎ የምግብ ፍላጎት በውርስ ያገኙት ሊሆን ይችላል፡፡ እነዚህም ነገሮች ሊታሰብባቸው ይገባል፡፡ ከውጭም ከውስጥም መልካምና ክፉ አንዱ አንዱን ለመጣል ይተናነቃሉ፡፡ ያልደረሰባቸው ሰዎች የሱስን አስቸጋሪነት አያውቁትም፡፡ አመልን ለማሸነፍ የሚደረገውን ብርቱ ጦርነት አያስተውሉትም፡፡ ጦርነቱ ሳያቋርጥ ለብዙ ጊዜ ይቀጥላል፡፤ የክርስቶስ ነን የሚሉ ብዙ ሰዎች በሱስና በአመል ላይ ጦርነቱን ለማወጅ ችላ ይላሉ፡፡ ግን ሠራተኛው በሁኔታው ተስፋ መቍረጥ የለበትም፡፡ ወደኋላ የሚያፈገፍጉት ከአመል ዝቃጭ ነፃ የወጡት ብቻ ናቸው እንዴ? CLAmh 88.6
ብቻህን አለመሆንህን እወቅ፡፡ አገልጋይ መላዕክት በአደጋ ላይ ያሉትን ልጆች ለማዳን ከሰው ጋር በኅብረት ይሠራሉ፡፡ መላሹም ክርስቶስ ራሱ ነው፡፡ ታላቁ ሐኪም በአገልጋዩ ጎን ቆሞ “ልጄ ሆይ ኃጢአትህ ቀረችልህ” ይላል፡፡ (ማር 2፡5) CLAmh 89.1
የተናቁ ሳሉ በወንጌል ያለውን ተስፋ የጨበጡ ሰዎች መንግሥተ ሰማያት ሊገቡ ታላቅ ዕድል ተስጥቷቸዋል፤ ብርሃኑ በርቶላቸው ያልተጠቀሙበት ግን በጨለማ ይቀራሉ፡፡ CLAmh 89.2