የተሟላ ኑሮ
17—መሻትን አለመግዛት ሊድን (ሊፈወስ) ይችላል
መሻትን መግዛት ከጎደላቸው ሰዎች መካከል ልዩ ልዩ ማዕረግና ሹመት ያላቸው አሉ፡፡ ከፍተኛ ደረጃ ያላቸው፤ ግሩም ችሎታ ያላቸው፤ ከፍተኛ ትምህርት ያላቸው ሰዎች ሁሉ መሻታቸውን መግዛት ስላቃታቸው ፈተናን መቋቋም አልቻሉም፡፡ ዱሮ የሐብትና የማዕረግ ጌታ የነበሩት ዛሬ የዕለት ጉርስ፤ የዓመት ልብስ አጥተው ወዳጅ ዘመድ ሸሽቷቸው፤ የጥቃት ፣ የውርደት፣ የድኅነት መጫወቻ ሆነዋል፤ ራሳቸውን መግዛት ተስኖአቸዋል፡፡ ረዳት ካካልደረሰላቸው የመጨረሻ ወራዳዎች ከመሆን አይድኑም፡፡ CLAmh 87.3
ይህ ራስን አለመቆጣጠር የሚያስከትለው የመንፈስን ውድቀት ብቻ ሳይሆን የአካልንም ድካም ነው፡፤ እነዚህን ሰዎች ለመርዳት ልናደርግ የሚገባን የሱስ ያደርግ እንደነበረው የአካል ይዞታቸውን መመልከት ያስፈልገናል፡፡ CLAmh 87.4
አካልን የማይጎዳ ምግብ፤ ለጤና ተስማሚ መጠጥ፤ ንጹሕ ልብስ፤ የአካላቸውን ንጽሕና ለመጠበቅ እድል ማግኘት ያስፈልጋቸዋል፡፡ ርዳታ በተሞላበት በክርስትና አካባቢ ሊኖሩ ይገባል፡፡ በየከተማው በክፉ ልምድ የታሠሩ ሰዎች ከተተበተቡበት መጥፎ ሰንሰለት እንዲፈቱ ርዳታ የሚያገኙበት ልዩ ቦታ መኖር አለበት፡፡ CLAmh 87.5
ብዙዎች በብስጭት ጊዜ ደስታን የሚያመጣ የአልኮሆል መጠጥ ይመስላቸዋል፡፡ እንደ ካህኑና እንደ ሌዋዊው ከማድረግ ይልቅ ክርስቲያኖች እንደመልካሙ ሳምራዊ ቢሠሩ ይህ አስታያየት በተለወጠ ነበር፡፡ CLAmh 88.1
ሰካራሙ ከስካሩ ሲነቃ መንፈስ ሲታወክበት የምር ወዳጁ መሆናችሁን ግለጡለት፡፡ የትችት ቃል አትሰንዝሩበት፡፡ በአስተያየትም ሆነ በቃል ነቀፌታ አትሰንዝሩበት፡፡ ዕምነቱን በሚያበረቱ ቃላት አነጋግሩት፡፤ ያለውን መልካም ጠባይ የሚያሳድግ ነገር ንገሩት፡፤ እንደከበረ ሆኖ መኖር መቻሉን እግዚአብሔር መልካም ስጦታ እደሰጠውና ራሱ እንደተጠቀመበት አስገንዝቡት፡፡ CLAmh 88.2