የተሟላ ኑሮ

6/201

የደስተኛ ሕይወት መሰረት

ወላጆች ለልጆቻቸው ጤነኛና ተደሳች የሆነ ሕይወት መሠረት ሊጥሉ ይችላሉ፡፡ ልጆቻቸው ቤታቸውን ሲለቁ ፈተናን ለመቋቋም የሞራል ብርታትና የሕይወትንም ችግር ለመጋፈጥ ድፍረት፣ ጥንካሬ እንዲኖራቸው ማድረግ ይገባቸዋል፡፡ ልጆቻቸው ሕይወታቸውን ለእግዚአብሔር ክብርና ለዓለም በረከት እንዲሆን ያደርጉ ዘንድ ሊያደፋፍሯቸው ይገባል፡፡ ወላጆች ልጆቻቸው በደስታም ሆነ በችግር ጊዜ ወደ ክብር ቦታ የሚጓዙበትን ቀጥተኛ መንገድ መጥረግ አለባቸው፡፡ CLAmh 10.4

የቤተሰብ ሥራ በቤት ውስጥ ለሚገኙ ሰዎች ብቻ የተወሰነ አይደለም፡፡ የክርስቲያን ቤተሰብ ግሩም የሆኑትን እውነተኛ የሕይወት ደንቦች የሚገልጽ ምሳሌ መሆን አለበት፡፡ የዚህ አይነት ምሳሌነት በዓለም ውስጥ ጠቃሚ ኃይል ይሆናል፡፡ ከማንኛውም ስብከት ይልቅ የሰውን ልብና ሕይወት በበለጠ ሊለውጥ የሚችል የጥሩ ቤተሰብ ምሳሌነት ነው፡፡ ወጣቶች ከእንደዚህ ያለ ቤተሰብ ሲወጡ የተማሩት ትምህርት ለሌሎች ይዳረሳል፡፡ የተከበሩ የሕይወት ደንቦች ወደሌላ ቤተሰቦች ሲዳረሱ በቀበሌው ውስጥ የሚያነቃቃ ስሜት ይሰፍናል፡፡ CLAmh 10.5

ቤተሰባችን ለብዙ ሰዎች በረከት ሊሆን ይችላል፡፡ ማኅበራዊ ግብዣዎቻችን በክርስቶስ መንፈስና በቃሉ እንጂ በዓለማዊ ልማድ መመራት አይገባቸውም፡፡ ኢየሱስ እንደዚህ ይላል፡፡ “ምሳ ወይም እራት ባደረግህ ጊዜ እነርሱ ደግሞ በተራቸው ምናልባት እንዳይጠሩህ ብድራትን እንዳይመልሱልህ፣ ወላጆችህንና ወንድሞችህን፣ ዘመዶችህንም፣ ባለጠጎች ጎረቤቶችህንም አትጥራ፡፡ ነገር ግን ግብዣ ባደረግህ ጊዜ ድኆችንና ጉንድሾቸን፣ አንካሶችንም፣ እውሮችንም ጥራ፡፡ የሚመልሱት ብድራት የላቸውምና ብፁዕ ትሆናለህ፡፡ በጻድቃን ትንሣኤ ይመለስልሃል” ሉቃስ 14፡12-14፡፡ CLAmh 11.1

እኒህን ዓይነቶች እንግዶች ማስተናገድ ብዙ ችግርን አያስከትልም፡፡ ብዙ ገንዘብ የሚያስወጣ ትልቅ ግብዣ አያስከትልም፡፡ ብዙ ገንዘብ የሚያወጣ ትልቅ ግብዣ አይጠይቁም፡፡ የታይታ ዝግጅት አያሻም፡፡ ለብዙዎች ልባዊ አቀባበል፣ አብሮ እሳት መሞቅ፣ ከአንድ ማዕድ አብሮ መብላትና አብሮ የመጸለይ እድል የሰማይን ሕይወት እንደመቅመስ ያህል ነው፡፡ CLAmh 11.2

ርኅራኄአችን ከራሳችንና ከቤተሰባችን አልፎ ለሌሎች መድረስ አለበት፡፡ ቤታቸውን ለሌሎች መባረኪያ ለማድረግ ለሚፈልጉ ሁሉ ጥሩ እድል ሞልቷል፡፡ ባካባቢው ውስጥ ታዋቂ መሆን አስገራሚ ኃይል ነው፡፡ ፈቃደኞች ከሆንን ይህንን ኃይል ሌሎችን ለመርዳት ልንጠቀመበት እንችላለን፡፡ CLAmh 11.3