የተሟላ ኑሮ

74/201

የትንባሆ ዝግተኛ መርዝ

ትንባሆ ዝግተኛና የማይታወቅበት በጣም አደገኛ መርዝ ነው፡፡ በማንኛውም መልክ ቢወሰድ ለአካል ጠንቅ መሆኑ አይቀርም፡፡ CLAmh 76.1

ጉዳቱ ቀስ በቀስ በመሆኑና በመጀመሪያ ስለማይታወቅ አደገኛነቱ የላቀ ነው፡፡ መጀመሪያ ነርቮችን ይረብሽና በኋላ ያበድናቸዋል፡፡ አእምሮን ያደንዛል፣ ከአስካሪ መጠጥ ይልቅ ነርቮችን ይጎዳል፡፡ ጉዳት ሲጀምር ሳያስታውቅ ስለሆነ ጠንቁን ከአካል ለማስወገድ አዳጋች ነው፡፤ ከተዘወተረ የጠንካራ መጠጥን ሱስ ይተክላል፡፡ ስለዚህ የጠጭነት መሠረቱና መነሻው ትንባሆ ማጨስ ነው፡፡ CLAmh 76.2

ትንባሆ ማጨስ የማይመች፣ ውድቅ፣ ቆሻሻ፣ ራስን አርክሶ ሌሎችን የሚያስቀይም ነው፡፡ የትንባሆ ተገዥ የሆኑ ሁሉ የትም ተቃውሞ ይገጥማቸዋል፡፤ በሕዝብ መካከል ስታልፉ አንድ ሰው የተመረዘ የትንባሆ ጭሱን ሲተነፍስበችሁ ምን ይሰማችኋል? በአልኮሆልና በትንባሆ ሽታ በተበከለ የሕዝብ መኪና ውስጥ ወይም ክፍል ውስጥ መቀመጥ አያስደስትም፤ ለጤናም አይስማማም፡፡ ሰዎች በትንባሆና በአልኮሆል ራሳቸውን ቢጎዱ አንሷቸው ሌላው ሕዝብ የሚስበውን አየር ለመበከል ምን መብት አላቸው? CLAmh 76.3