የተሟላ ኑሮ

73/201

ሻይና ቡና

ሻይ ሰውነትን ከሚያነቃቁ ነገሮች አንዱ ነው፡፡ አይብዛ እንጂ የስካርን ስሜት የመፍጠር ሁኔታ አለው፡፡ የቡናና የሌሎች የተለመዱ መጠጦች ጠባይም ከዚሁ የተለየ አይደለም፡፡ የመጀመሪያው ሞያው የአካልን የስራ ይዞታ ማፋጠን ነው፡፡ CLAmh 75.1

የሆድ ሕዋሳት ይረበሻሉ፤ ይህ ሁኔታ የአእምሮን መታወክ ያስከትላል፡፡ ከዚያም የልብ ትርታና ሥራ ይፋጠንና ጠቅላላው የአካል ተግባር ኃይል የተጨመረለት ይመስላል፡፡ ድካምና መታከት ይረሳል፡፡ የማሰብ ችሎታ የጎለመሰ ይመስላል፤ አሳቡ ብሩህ የሆነ መስሎ ይታያል፡፡ CLAmh 75.2

ስለዚህ ብዙ ሰዎች ሻይና ቡና የጠቀሟቸው ይመስላቸዋል፡፡ ግን የተሳሳተ ግምት ነው፡፡ ሻይና ቡና የአካላችንን ተግባር አያሻሽሉትም፡፡ CLAmh 75.3

ይህ ሁኔታ የሚፈጠረው ከምግብ መፈጨትና መዋሃድ በፊት ነው፤ ስለዚህ ብርታት የተገኘ የሚመስለው ነርቮች በመረበሻቸው ብቻ ነው፡፡ CLAmh 75.4

የአካል አነቃቂው ተግባር ሲያበቃ ያ የነበረው ብርታት ይጠፋል፡፡ በቦታው ድካምና ማዛጋት ይተካል፡፡ ይህ ነርቭን የሚያቃውስ መጠጥ ወይም ምግብ ሲዘወተር ራስ ምታት፣ እንቅልፍ ማጣት፣ ልብ በፍጥነት መምታት፣ የምግብ አለመዋሃድ፣ መንቀጥቀጥና ሌሎችም መጥፎ ነገሮች ጓዛቸውን ጭነው ይመጣሉ፡፡ ዋናውን ኃይል ያ ያልተገባ ምግብ ወይም መጠጥ ስለበዘበዘው ነው፡፡ የደከሙ የአካል ሕዋሳት ዕረፍት እንጂ አነቃቂና ከአቅም በላይ ሥራ አያሻቸውም፡፡ ስነ ፍጥት (ተፈጥሮ) የተበላውን ኃይሏን ለማደስ ጊዜ ያስፈልጋታል፡፡ ኃይሏ በአነቃቂ ነገር ሲገደድ ለጊዜው ብዙ ጉልበት ታወጣለች፡፡ ግን መበዝበዙ ሲበዛባት የተፈለገውን ተግባር ለማከናወን ጉልበቷ ይንጠፈጠፋል፡፡ የእነዚህ የአነቃቂ ነገሮች ፍላጎት እየተዘወተረና እያየለ ሲሄድ አምሮትን መቆጣጠር ያቅትና ያለፈቃድ ከመውሰድ ደረጃ ይደርሳል፡፡ እነዚህ ሱስ የሆኑ ነገሮች በመጨረሻ የአካልን ኃይል አሟጠው እስቲጨርሱ ድረስ የሰውን ኃይል በእጃቸው ያደርጋሉ፡፡ CLAmh 75.5