የተሟላ ኑሮ

4/201

መታዘዝ ነጻነትን ያስገኛል

ለእግዚአብሔር መታዘዝ ከኃጢአት እንቅፋት ነጻ መውጣትና ከሰብአዊ መጥፎ ስሜትና ዝንባሌ መዳን ነው፡፡ ሰው የራሱ የመጥፎ ዝንባሌውና የመንፈሳዊ ጨለማ ስልጣናት አሸናፊ ሊሆን ይችላል፡፡ ኤፌ 6፡12 CLAmh 8.3

ይህ ዓይነት ትምህርት ሊሰጥ የሚገባውና በበለጠም የሚጠቅመው በቤት ነው፡፡ ወላጆች የእያንዳንዱ ጠባይ መሠረት ጣዮች ናቸው፡፡ የቤተሰባቸው የሕይወት ዓላማ የሚወሰነው በእነርሱ ትምህርትና ምሳሌነት ነው፡፡ ልጆች ወላጆች እንዳደረጓቸው ይሆናሉ፡፡ CLAmh 8.4

ወላጆች የስራቸውን ውጤት እንዲከታተሉና እንዲሁም በምሳሌነታቸውና በትምህርታቸው የኃጢአትን ወይም የጽድቅን ሐይል እንዲሚያደረጁ ቢረዱት ያለጥርጥር መለወጥ ባሳዩ ነበር፡፡ ብዙዎች የተለምዶን ኑሮ ችላ ብለው የመለኮትን የሕይወት ደንቦች በተቀበሉ ነበር፡፡ CLAmh 8.5