የተሟላ ኑሮ

58/201

የማይበላባቸው ጊዜያት

ሌላው ሊታረም የሚገባው ልማድ ደግሞ የመኝታ ጊዜ ሲቃረብ መብላት ነው፡፡ በተወሰነው ጊዜ ቢበላም ለቅንጦት ሲባል ሊተኙ ሲሉ የመብላት ልምድ ይዘወተራል፡፡ ቀስ በቀስ ልምዱ ይበረታና ካልበሉ መተኛት የማይቻል ይሆናል፡፡ አምሽቶ ከመብላት የተነሣ ምግብ የማዋሀድ ተግባሩን የሚያከናውነው የአካል ክፍል ሥራውን ሌሊቱን ሁሉ ያካሂዳል፡፡ ጨጓራ ሥራውን ቢቀጥልም ቅሉ ተግባሩን በሚገባ አያከናውንም፡፡ የእንቅልፍ ጊዜ በሚያባንን ቅዠት ይቋረጣል፡፡ ጧት ሰውየው ሲነቃ ይቀፈዋል፤ የቁርስ ፍላጎትም የሌለው ይሆናል፡፡ ስንተኛ ጨጓራችንም ሆነ ሌሎች የአካል ክፍሎቻችን ሥራቸውን አጠናቅቀው በሰላም ማረፍ አለባቸው፡፡ በተለይ ተቀምጦ የሚሠራ ሥራ ያላቸው ሰዎች አምሽቶ መብላት ይጎዳቸዋል፡፡ CLAmh 57.3

በዚህ ያመጋገብ ጉድለት ጠንቅ የሚመጡ በሽታዎች፤ ሞትን ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡ ማታ ምግብ የሚያሰኝና ትንሽ ድካም የሚሰማበት ምክንያት ምግብ የሚፈጨው የአካል ክፍል ቀን በኃይል ስለተጎዳ ነው፡፡ ከአንድ የምግብ ጊዜ በኋላ እነዚህ ምግብን የሚፈጩት ሕዋሳት ዕረፍት ያሻቸዋል፡፡በሁለት የምግብ ጊዜያት መካከል ሲያንስ 5 ወይም 6 ሰዓት ያስፈልጋል፡፡ ብዙ ሰዎች በዚህ መመሪያ ከተጠቀሙ በኋላ በቀን ሁለት ጊዜ ብቻ መመገብ የተሻለ መሆኑን አምነውበታል፡፡ CLAmh 57.4

ምግባችን በጣም የሞቀ ወይም በጣም የቀዘቀዘ መሆን የለበትም፡፡ ምግቡ በጣም የቀዘቀዘ እንደሆነ ጨጓራችን ምግብ ለማድቀቅ የሚያገለግለውን ኃይል ምግቡም ለማሞቅ ይጠቀምበታል፡፡ ቀዝቃዛ መጠጥም የዚያኑ ያህል ጉድለት ያስከትላል፡፡ የሞቀ መጠጥም ቢሆን CLAmh 57.5

ኃይሉን ያደክመዋል፡፡ እንዲያውም በምግብ ጊዜ ብዙ መጠጥ ከተጠጣ ምግቡ የመድቀቅና የመዋሀድ ችግር ያጋጥመዋል፡፡ ምክንያቱም ምግብ የማድቀቅ ተግባር ከመካሄዱ በፊት ውኃው ወይም ፈሳሹ መመጠጥ አለበት፡፡

ብዙ ጨው መመገብ አያስፈልግም፤ እርሾና ቅመም የበዛበት ምግብም አለመመገብ ነው፡፡ ብዙ ፍራፍሬ መብላት ጥሩ ነው፡፡ ስለዚህ በምግብ ጊዜ የሚቀሰቀሰው የውኃ ጥማት (ፍላጎት) ይወገዳል፡፡ CLAmh 58.1

ምግባችንን በችኮላ መመገብ የለብንም፡፡ ደግሞም በሚገባ መታኘክ አለበት፡፡ ይህ ነገር የሚረዳው ምግብን ከአፋችን ከሚመነጨው ፈሳሽ ጋር በደንብ ለማዋሀድና ምግቡ እንዲፈጭ የሚረዱት ፈሳሾች እንዲመነጩ ነው፡፡ CLAmh 58.2

አንዱ መጥፎ ነገር ደግሞ ባልሆነ ጊዜ መመገብ ነው፡፡ ከከባድ ሥራና አድካሚ የሰውነት ማጠንከሪያ ልምምድ ከሠሩ በኋላ ወዲያውኑ መብላት መጥፎ ነው፡፡ ሙቀት ሲሰማና አካል ሲዝል ምግብ መቅመስ አያሻም፡፡ CLAmh 58.3

ከምግብ በኋላ ነርቮች ከባድ ሥራ ይጠብቃቸዋል፡፡ ስለዚህ ከምግብ በፊት ወይም ወዲያው እንደበሉ የአእምሮ ወይም ከባድ የአካል ሥራ መሥራት የምግብን መዋሀድ (መፈጨት) ያጨናጉለዋል፡፡ ስለዚህ ከቸኮላችሁ ከደነገጣችሁና ከተበሳጫችሁ ዕረፍትና ሰላም እስክታገኙ ባትበሉ መልካም ነው፡፡ CLAmh 58.4

ጨጓራችንና አዕምሯችን የቅርብ ግንኙነት አላቸው፡፤ ስለዚህ የጭንቅላታችን ነርቮች ወደ ተዳከመው የምግብ መፍጫ የአካል ክፍል ለርዳታ በአስቸኳይ ይላካሉ፡፡ ይህ ዓይነት ነገር ከተደጋገመ አእምሮአችን ይጎዳል፡፡ አእምሮአችን ሥራ የሚበዛበት ከሆነና የጉልበት ሥራ እምበዛም የማነሠራ ከሆንን ቀላል ምግብ እንኳን በመጠኑ መመገብ ይኖርብናል፡፤ CLAmh 58.5

በምግብ ጊዜ ችግራችሁንና አሳባችሁን እርሱት፡፡ አትቸኩሉ፤ ተዝናንታችሁና ተደስታቸሁ ብሉ፡፡ እግዚአብሔር ለሰጣችሁ በረከት ሁሉ በልባችሁ አመስግኑት፡፡ CLAmh 58.6