የተሟላ ኑሮ

57/201

ምግብ ማብሰል የጠለቀ ሳይንስ ነው

ምግብ የሚያበስሉ ሁሉ ለጤና የሚስማማ ምግብ ለማቅረብ መጣጣር የተቀደሰ ተግባራቸው ነው፡፡ ምግብ እንደሚገባ ባለመብሰሉ ምክንያት ብዙ ነፍሳት ጠፍተዋል፡፡ ጥሩ ምግብ አብሳይ ሊባሉ የሚቻሉ ጥቂቶች ናቸው፡፡ ብዙ ልጃገረዶች ምግብ ማብሰልና ሌላም የቤት ሥራ ውርደት ይመስላቸዋል፤ ስለዚህ ባል ባገቡና ትዳር በያዙ ጊዜ የሚገባቸውን ተግባር ለመፈጸም አይችሉም፡፡ CLAmh 56.3

ምግብ ማብሰል ቀላል ሳይንስ አይደለም፡፡ እንዲያውም ለየዕለቱ ኑሮ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ ሴቶች ሁሉ ሊማሩት የሚገባ ሳይንስ ነው፡፡ ድኆችን እንዲጠቅም አድርጎ ማስተማር ይገባል፡፡ ምግብን የሚጣፍጥና ለአካል የሚጠቅም አድርጎ ለመሥራት ብልሃት ይጠይቃል፤ ይህንም ለማድረግ የሚቻል ነው፡፡ ምግብ አብሳዮች ሁሉ ጣፋጭና ጤና የሚሰጥ ምግብ በቀላሉ ለማዘጋጀት መቻል አለባቸው፡፡ CLAmh 56.4

ለጤና የሚስማማ ምግብ ለማግኘት የሚያስፈልገውን ብልሃት የማታውቅ ባለትዳር ሴት ለቤተሰብዋ የሚያስፈልገውን መማር አለባት፡፡ በብዙ ቦታ የባልትና ትምህርት ቤቶች ስለምግብ አበሳሰል ያስተምራሉ፡፡ CLAmh 56.5

የባልትና ትምህርት ሳትማር ያደገች የቤት እመቤት ከጎረቤት ለመማር አትፈር፡፡ የዚህ የባልትና ሥራ አዋቂ እስክትሆን ድረስ ጥረት ከማድረግ አትቆጠብ፡፡ CLAmh 57.1

የምግብን ጊዜ መወሰን በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ ለእያንዳንዱ የምግብ ጊዜ የተወሰነ ሰዓት ይኑር ፡፡ በተወሰነው ሰዓት የተፈለገውን ያህል ምግብ በልቶ እስከሚቀጥለው የምግብ ጊዜ ምንም አለመቅመስ ነው፡፡ ፍላጎታቸውን መግታት ስለማይችሉ ብቻ ሳያስፈልጋቸው በየጊዜው የሚበሉ አሉ፡፡ አንዳንድ ሰዎች በመንገድ ላይ እንኳ ሆነው የሚቀመስ ካገኙ እግረ መንገዳቸውን ያግበሰብሱታል፡፡ ይህ ልማድ በጣም ይጎዳል፡፡ መንገደኞች በተወሰነ ጊዜ የተወሰነ ምግብ ቢበሉ ድካም አይሰማቸውም፤ በሽታም አይዞራቸውም፡፡ CLAmh 57.2