የተሟላ ኑሮ

43/201

9—ልጆች ምን ያንብቡ?

የክፉው ሁሉ መሪ ሰይጣን የእግዚአብሔርን ቃል ለማሳትና የሰውን ትምህርት ቀዳሚ ለማድረግ በመጣር ላይ ነው፡፡ ይህም ማለት “መንገዴ ይህቺ ናት፤ በእርሷም ሂድ” (ኢሣ 30፡21) የሚለው የእግዚአብሔርን ድምፅ እንዳንሰማ ያደርገናል ማለት ነው፡፡ በተቃወሰ የትምህርት አሰጣጥ ኣማካይነት ከሰማይ የሚመጣውን ብርሃን አደብዝዞታል፡፡ CLAmh 43.1

እግዚአብሔር ያልተጨመረበት ፍልስፍና የሳይንስ ምርምር በሺህ የሚቆጠሩትን ሰዎች ከሐዲ አድርጓል፡፡ ዛሬ በየትምህርት ቤቱ ሊቃውንት በሳይንስ ምርምር ያገኙት ሐሳብ በትምህርት መልክ ይቀርባል፤ ይህም በሚደረግበት ጊዜ ሊቃውንቱ የሚሉት ልክ ከሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ልክ ሊሆን አይችልም የሚል ስሜት ይሰጣል፡፡ መናፍቅነት ለሰብአዊ አእምሮ አስጎምጂ ነው፡፡ ወጣቶችም ነጻነት ያገኙ እየመሰላቸው ይታለላሉ፡፡ ሰይጣን ድል ይነሳል፡፡ በወጣቶች ልብ የሚዘራውን የጥርጣሬ ዘር ይንከባከበዋል፡፡ እንዲያደግና ፍሬ እንዲያፈራ ስለሚያደርገው በአጭር ጊዜ ውስጥ የመናፍቅነት መከር ይሰበስባል፡፡ CLAmh 43.2

በወጣቶች አእምሮ የመናፍቅነት ዘር መዝራት አስጊ የሚሆንበት ምክንያት የሰብአዊ ተፈጥሮ ልብ ወደ ክፉ ነገር ዝንባሌ ስላለው ነው፡፡ ሰው በእግዚአብሔር ያለውን እምነት የሚያጓድል ነገር ሁሉ ፈተናን ለመከላከል አቅመቢስ ያደርጋል፡፡ የኃጢአትን መከላከያ ያስወግዳል፡፡ ትልቅነት ማለት እግዚአብሔርን ማክበርና በየቀኑ ሕይወት ጠባዩን መግለጽ መሆኑን ለወጣቶች የሚያስተምር ትምህርት ቤት እንፈልጋለን፡፡ እግዚአብሔር ለሕይወታችን ያሰበውን ለመፈጸም እንድንችል ከቃሉና ከፈጠራቸው ነገሮች ስለ እርሱ መማር ያሻናል፡፡ CLAmh 43.3