የተሟላ ኑሮ
የጓደኛ አርኣያ
የእግዚአብሔር ቃል በአዋቂዎች ላይ ሳይቀር የጓደኛ አርአያ እንደሚመጣ ደህና አድርጎ ይናገራል፡፡ በሕፃናትና በወጣቶች አእምሮና ጠባይ ላይ ምን ያህል የበለጠ ኃይል ይኖረው ይሆን፡፡ የጓደኞቻቸው ዓይነት፤ በምን ዓይነት የሕይወት ደንብ እንደሚኖሩና የኑሮ ልምዳቸው በዚህ ዓለምም ሆነ በሚመጣው ያላቸውን ጠቃሚነት ይወስናል፡፡ CLAmh 41.3
በጣም የሚያሳዝነውና የወላጆችንም ልብ የሚያንቀጠቅጠው አሰቃቂ እውነት ወጣቶች ለመሰልጠን የሚሔዱባቸው ብዙ ትምህርት ቤቶችና ኮሌጆች ጠባይን በሚያበላሽ፤ አእምሮን ከእውነተኛው የሕይወት ዓላማ በሚመልስና ሞራልን በሚያረክስ አርኣያ መሞላታቸው ነው፡፡ ከከሐዲዎች ከደስታ አፍቃሪዎችና ከረከሱት ጋር ግንኙነት በማድረግ ብዙ ወጣቶች ክርስቲያን ወላጆቻቸው በጥንቃቄ በማስተማርና በእምነት በመጸለይ ጠብቀው ያቆዩትን ንጽሕናቸውን፤ በእግዚአብሔር የነበራቸውን እምነትና የመሥዋዕትነት መንፈስ ያጠፋሉ፡፡ CLAmh 41.4
ለመሥዋዕትነት አገልግሎት በበለጠ ለመዘጋጀት ትምህረት ቤት ከሚገቡት ብዙዎቹ በዓለማዊ ትምህርት ተውጠው ይቀራሉ፡፡ በትምህርት ታዋቂ የመሆንና በዓለም የክብር ቦታ የመያዝ ምኞት ይነሳሳባቸዋል፡፡ ትምህርት ቤት የገቡበት ዓላማ ይረሳና ሕይወታቸውን ራስን ለማገልገልና ዓለማዊውን ነገር ለማሳደድ ብቻ ይጠቀሙበታል፡፡ ብዙውን ጊዜ ሕይወትን ለዚህ ዓለምና ለሚቀጥለውም የማይገጥም የሚያደርጉ ጠባዮች ይመሠርታሉ፡፡ CLAmh 42.1
አብዛኛውን ጊዜ ሰፊ አስተያየቶች ያላቸው፤ ራሳቸውን ብቻ ወዳጅ የልሆኑና የተቀደሰ ዓላማ ያላቸው ሰዎች የዚህን ዓይነት ጠባይ የሚመሰርቱት ከልጅነት ጓደኞቻቸው ነው፡፡ እግዚአብሔር ከእሥራኤል ልጆች ጋር በነበረው ግንኙነት ልጆቻቸው ምን ዓይነት ጓደኛ ሊኖራቸው እንደሚገባ አስጠነቀቃቸው፡፡ የመንግስት፣ የሃይማኖትና የኅብረተሰብ ድርጅት ሁሉ የተቋቋመው ልጆችን ከሚጎዳ ጓደኝነት ለማዳንና ከሕፃንነታቸው ጀምረው የእግዚአብሔርን ሕግና ሥርዓት እንዲያውቁ ለማድረግ ነበር፡፡ የእሥራኤል መንግስት በተመሠረተ ጊዜ የተሰጠው ትምህርት ዓላማ የሁሉን ሰው ልብ ለመንካት ነበር፡፡ የበኵርን ልጅ የሚያጠፋው የመጨረሻው መቅሰፍት በግብጽ ላይ ከመውረዱ በፊት እግዚአብሔር የእርሱ ወገን የሆኑትን ልጆቸውን ወደየቤታቸው እንዲያስገቡ አዘዛቸው፡፡ የእያንዳንዱ ቤት መድረክ ደም ተቀበቶ ነበር፤ ሁሉም በዚህ ምሳሌያዊ ጥበቃ ሥር መኖር ነበረባቸው፡፡ ዛሬም እግዚአብሔርን የሚወዱና የሚፈሩ ወላጆች ሁሉ ልጆቻቸውን በቃል ኪዳኑ ጥበቃ ሥር፤ ማለት በክርስቶስ ደም በተዘጋጀው ጥበቃ ሥር ማድረግ አለባቸው፡፡ CLAmh 42.2
የእግዚአብሔርን የትምህርት ሥነ ሥርዓት ለመከተል ለሚፈቅዱ ሁሉ የሚያጠነክረውን ጸጋውንና ኃይሉን ይሰጣቸዋል፤ እርሱ ራሱም አብሯቸው ይሆናል፤ ለሁሉም “እግዚአብሔር አምላክህ ከአንተ ጋር ነውና ጽና፣ አይዞህ፣ አትፍራ፣ አትደንግጥ፡፡ አልጥልህም አልተውህም” ይላል፡፡ ኢያሱ 1፡9፣5 CLAmh 42.3