የተሟላ ኑሮ
የልጆች የመጀመሪያ ትምህርት ቤት
የልጅ የመጀመሪያ ትምህርት ቤት ቤቱ ነው፡፡ የአገልግሎት ሕይወቱ መሠረቱ የሚጣለው እዚህ ነው፡፡ የሕይወት ደንቦች በቃል ብቻ አይጠኑም፡፡ መላውን ሕይወት ማነጽ አለባቸው፡፡ CLAmh 40.2
ልጅ ገና በሕጻንነቱ የረዳትነት ትምህርት መማር አለበት፡፡ ጉልበቱና የማሰብ ኃይሉ በመጠኑ እንደደረጀ በቤት ውስጥ የሚሠራው ሥራ ሊሰጠው ይገባል፡፡ እናትና አባቱን እንዲረዳ ራሱን ብቻ እንዳይወድና ራሱን እንዲገታ፤ ከራሱ በፊት ሌሎቹን ለማስደሰት እንዲሞክር፤ እህቶቹን፣ ወንድሞቹንና ጓደኞችን የሚያስደስትበትን መንገድ እንዲሻና ለሽማግሌዎች፣ ለታመሙና ለዕድለቢሶች እንዲራራ መደፋፈር አለበት፡፡ እውነተኛ የአገልግሎት መንፈስ በቤት ውስጥ ከታየ በልጆቹ ሕይወት ይመሠረታል፡፡ በአገልግሎትና ለራስ ይቅርብኝ ብሎ ሌሎችን በመጥቀም መደሰትን ይማራል፡፡ CLAmh 40.3
ከቤት የሚሰጠው ትምህርት ከትምህርት ቤት በሚሰጠው ትምህርት መደገፍ አለበት፡፡ የአካል፣ የአእምሮና የመንፈሳዊ ዕድገት፤ የአገልግሎና የመሥዋዕትነት ትምህርት ዘወትር መታወስ አለበት፡፡ CLAmh 40.4
ከማንኛውም ነገር ይልቅ በየዕለት ኑሮ በትንንሽ ነገሮች ክርስቶስን ማገልገል ጠባይን ለመገንባትና ሕይወትንም ራስን ብቻ ወዳለመውደድ አገልግሎት ለመምራት የበለጠ ኃይል አለው፡፡ ይህን ዓይነት ስሜት ማነቃቃት፣ ማደፋፈረርና በትክክል መምራት የወላጆችና የመምህራን ሥራ ነው፡፡ ከዚህ የበለጠ ዋና ሥራ ሊሰጣቸው አይቻልም፡፡ የአገልግሎት መንፈስ ሰማያዊ መንፈስ ነው፡፡ ይህን ዓይነት መንፈስ ለማነሳሳት በሚደረገው ጥረት ሁሉ መላዕክት ይተባበራሉ፡፡ CLAmh 40.5
የዚህ ዓይነት ትምህርት በእግዚአብሔር ቃል ላይ ሊመሠረት ይገባል፡፡ ደንቦቹ በሙሉ የሚገኙት ከእግዚአብሔር ቃል ብቻ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የመማርና የማስተማር መሠረት ሊሆን ይገባል፡፡ አስፈላጊውን እውቀት እግዚብሔርንና እርሱ የላከውን (ክርስቶስን) ማወቅ ነው፡፡ CLAmh 40.6