የተሟላ ኑሮ
6—ሕጻኑን ማስተዋል
ለእሥራኤል ወላጆች በተሰጠው የመልአክ መሪ ቃል የናቲቱ ልምድ ብቻ ሳይሆ ሕፃኑንም እንዴት ማስተማር እደሚገባ በተጨማሪ ተጠቅሷል፡፡ እሥራኤልን እንዲመራ የተመረጠው ሳምሶን በልደቱ ጊዜ የነበረው ጥሩ ነገር በቂው አልነበረም፡፡ በተጨማሪም በጥንቃቄ መመራት ነበረበት፡፡ ከሕፃንነቱ ጀምሮ የመጠነኛነት ልምድ እንዲኖረው የሚያደርገው ትምህርት ማግኘት ነበረበት፡፡ CLAmh 26.2
ስለ ዮሐንስ መጥምቁም የዚህ ዓይነት መመሪያ ቃል ተሰጥቶ ነበር፡፡ ልጁ ከመወለዱ በፊት ለአባትዮው ከሰማይ የመጣለት መልእክት እንደዚህ የሚል ነበር፡፡ CLAmh 26.3
“ደስታና ተድላ ይሆንልሃል፤ በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል፡፡ በጌታ ፊት ታላቅ ይሆናልና፤ የወይን ጠጅና የሚያሰክር መጠጥ አይጠጣም፡፡ ገናም በናቱ ማኅፀን ሳለ መንፈስ ቅዱስ ይሞላበታል፡፡” ሉቃስ 1፡14-15 CLAmh 26.4
በሰማይ ከተመዘገቡት ትልልቅ ሰዎች መካከል ዮሐንስ መጥምቁን የሚያህል እንደሌለ መድኃኒታችን መስክሮለታል፡፡ የተሰጠው ሥራ የአካልን ጥንካሬና ብርታት ለሥራው ዝግጅት ትክክለኛ የጤና ትምህርት ዋና ከመሆኑ የተነሳ የመላእክት አለቃ የሆነው መልአክ ስለ ልጁ ከሰማይ ለወላጆቹ መመሪያ ቃል ይዞ መጣ፡፡ CLAmh 26.5
ስለ እሥራኤል ሕፃናት አስተዳደግ የተሰጠውን መመሪያ ቃል ስናነብ የሕፃናትን ጤንነት የሚመለከት ነገር ሁሉ ሊናቅ እደማይገባው ማስተዋል አለብን፡፡ ሊናቅ የሚነገው ነገር የለም፡፡ የልጁን ጤንነት የሚመለከት ነገር ሁሉ አእምሮውንና ጠባዩንም ይመለከታል፡፡ CLAmh 27.1