የተሟላ ኑሮ

180/201

የእግዚአብሔር ዕቅድ ሲሟላ

አምላክ በፍቅሩና በጥንቃቄው ከራሳችን ይልቅ እኛነታችንን አብልጦ ስለሚያውቅ ራሳችንን ከፍ ለማድረግ ያለንን የጋለ ጉጉት ያጨነጉለዋል፡፡ ተራን ጉዳይ ከማሳደድ ይልቅ በፊታችን የተደቀነውን ቅዱስ ዓላማ እንድንመለከት ይፈልገናል፡፡ እነዚህ ተግባሮች ከፍተኛ ቁም ነገር እንዳንፈጽም ያሰለጥሉናል፡፡ አንዳንድ ጊዜ የእኛ ዕቅድ ይወድቅና የአምላክ ዕቅድ ይሟላል፡፡ CLAmh 192.4

ለእግዚአብሔር ከፍተኛ መሥዋዕት እንድናቀርብ አይጠበቅብንም፡፡ ብዙ ጊዜ አንዳንድ ነገሮችን እንድንተው ብንጠየቅም እነዚያ አጉል ነገሮች ወደ ሰማይ ከመግባት ስለሚከለክሉን ነው፡፡ መልካም የመሰሉትን ነገሮች እንኳ እንድንተው እግዚአብሔር ቢጠይቀን በምትኩ ከዚያ የበለጠ ሊሰጠን ማቀዱን ማወቅ አለብን፡፡ CLAmh 192.5

አሁን ቅር የተሰኘንባቸውን ነገሮች ቢኖሩም በሚመጣው አለም ግልጥ ይሆንልናል፡፡ ያላተመለሰ መስሎን የነበረ ጸሎትና ተስፋ ያስቆረጠን መስሎን የነበረውን ጉዳይ በረከት መሆኑን እንረዳለን፡፡ CLAmh 192.6

ዝቅተኛ መስሎ ይታየን የነበረ ስራ ሁሉ የእግዚአብሔር ስራ ሰለሆነ ቅዱስ መሆኑን እንረዳለን፡፡ በየቀኑ “የተቻለኝን ያህል እንድሰራ እርዳኝ፤ ጌታ ሆይ የተሻለ ሥራ መስራትን አስተምረኝ፤ ኃይልንና ፈቃደኛነትን አድለኝ፡፡ በተግባሬ ሀሉ ለመድኃኒቴ እንዳገለግል እርዳኝ” እያልን መጸለይ ይገባናል፡፡ CLAmh 192.7

የሙሴን የሕይወት ታሪክ አስታውሱ፤ የንጉስ የልጅ ልጅ ሆኖ በግብጽ የገበየው ትምህርትና ለወራሽነት የነበረው መብት የሚያጓጓ ነበረ፡፡ እንደ ግብጻውያን አስተሳሰብ ከጠቢባን መካከል ለመመደብ አንድም የሚያግደው ነገር አልነበረም፡፡ ከፍተኛ የጦር እና የሲቪል ትምህርት ነበረው፡፡ እስራኤሎችን ከባርነት ነፃ ለማውጣት የተዘጋጀ መስሎት ነበር፡፡ የእግዚአብሔር ግምት ግን የዚያ ተቃራኒ ነበረ፡፡ በምህረቱ ሙሴን በግ እያስጠበቀ ለ40 ዓመታት በምድረ በዳ አሠለጠነው፡፡ CLAmh 193.1