የተሟላ ኑሮ
የኑሮን መዝሙር መማር
በግርግር (በሳጥን) የተያዘች ወፍ ቀኑን ሁሉ የሌሎችን ሰዎች መዝሙር ስትሰማ ከዋለች ጌታዋ እንድትማር የሚፈልገውን መዝሙር መማር አትችልም፡፡ በጥራዝ ነጠቅነት ከዚያ አንድ ስንኝ፤ ከዚያም አንድ ቃል ትቀስማለች እንጂ ሙሉ በሙሉ ልታውቅ አትችልም፡፡ የወፏ ጌታ ግን ሳጥኑን በማጠር ወፏን በደንብ መዘመር እስከምትችልበት ድረስ እየደጋገመ ሳይሰለች ይዘምርላታል፡፡ ከዚያ በኃላ ወፏ ወደ ብርሃን ብትውጣም መዝሙሩን በደንብ መዘመር ትችላለች፡፡ እግዚአብሔርም ልጆቹን በዚህ መንገድ ያሰለጥናቸዋል ፡፡ የሚያስተምረን መዝሙር አለው፡፡ በፈተና ጨለማ ውስጥ የተማርነው መዝሙር የትም ልንዘምረው እንችላለን፡፡ CLAmh 191.3
ብዙዎች በእድሜ ልክ ስራቸው አይደሰቱም፡፡ ምናልባት አከባቢያቸው አያስደስታቸውም ይሆናል፡፡ ሁል ጊዜ የሚሠሩት ተራ ይሆናል፡፡ ራሳቸውን ለበለጠ ሥራ ብቁ አድርገው ይገምታሉ፡፡ በስራቸው ያልተመሰገኑና አመድ አፋሽ ሆነው ይሰማቸዋል፡፡ የወደፊት ሁኔታቸውም ያጠራጥራቸዋል፡፡ CLAmh 191.4
የምንሰራውን ሥራ እኛ ባንመርጠውም እግዚአብሔር የመረጠልን ተግባር መሆኑን አንርሳ፡፡ ቢያስደስተንም ባያስደስተንም ያገኘነውን ሥራ መስራት አለብን፡፡ “አንተ በምትሄድበት በሲኦል ሥራን አሳብ እውቀትና ጥበብ አይገኙምና እጅህ ለማድረግ የምታገኘውን ሁሉ እንደ ኃይልህ አድርግ፡፡” (መክብብ 9፡10) ፡፡ CLAmh 191.5
አምላክ ወደ ነነዌ ልንሄድ ቢፈልገን በዚያ ፋንታ ወደ እዮጴ ወይም ወደ ቅፍርናሆም ብንሄድ አያስደስተውም፡፡ ወዳመለከተን ቦታ የምንሄድበት ምክንያት አለው፡፡ በዚያ በተወሰነው ቦታ እርዳታችን የሚያስፈልገው ሰው ይኖራል፡፡ CLAmh 192.1
ፊልጶስን ወደ ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ፤ ጴጥሮስን ወደ ሮማዊው የመቶ አለቃ፤ ትንሿ እስራኤሊያዊት ወደ ሦሪያዊው የጦር አዛዥ ወደ ንእማን የላከ አምላክ ዛሬም ቢሆን ወጣቶችን፤ ሴቶችንና ውንዶችን የእርሱ ወኪል እንዲሆኑ መለኮታዊ አርዳታና መመሪያ ወደ ሚያስፈልጋቸው ዘንድ ይልካቸዋል፡፡ CLAmh 192.2
የእኛ አሳብ ብዙ ጊዜ ከእግዚአብሔር አሳብ ጋር አይገጥምም፡፡ አንዳንድ ጊዜ ለእኛም ለእርሱም ስለሚበጅ እግዚአብሔር እንደ ፍላጎታችን እንዳንሠራ ይከለክለናል፡፡ ዳዊትንም ከልክሎት ነበር፡፡ አንድ እርግጠኛ ነገር መኖርን እናውቃለን ያልናቸውንና ራሳቸውም ሳይቀር ለክብሩ የሚያስከብሩትን ሰዎች ለአገልግሎቱ ያውላቸዋል፡፡ ሊሠሩት የፈለጉትን መከልክል መልካም መስሎ ከታየው ሌላ የስራ መስክ ይከፍትላቸዋል፡፡ ይህንንም ሲያደርግ ፍቅሩን ይገልጥላቸዋል፡፡ CLAmh 192.3