የተሟላ ኑሮ

175/201

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚያስደስት ውጤት አለው

የተፈጥሮ ኃይሎች የሚጎለምሱ በቅዱስ መታዘዝ አማካይነት ነው፡፡ የሕይወትን ቃል በመማር ተማሪዎች አእምሮአቸው ይዳብራል፤ ጠባያቸው ጨዋ ይሆናል፡፡ እንደ ዳንኤል ቃልን ሰሚዎችና አድራጊዎች ከሆኑ እንደእርሱ በማንኛውም የትምህርት ዓይነት የላቁ ይሆናሉ፡፡ አእምሮአቸው ንጹህ ስለሚሆን በአሰባቸው የጸኑ ይሆናሉ፡፡ የማስተዋል ችሎታቸው ፈጣን ይሆናል፡፡ CLAmh 188.1

ከእግዚአብሔር ከጥበብ ሁሉ ምንጭ ጋር ግንኙነት ሲያደርግ ሰው ከምን ደረጃ እንደሚደርስና ምን ማድረግ እንደሚችል ሌሎች እስኪገነዘቡ ድረስ ራሳቸውን መቆጣጠርና ማሰልጠን ይችላሉ፡፡ CLAmh 188.2

የዚህ ዓለም ኑሮአችን ለሰማይ ኑሮ የምንዘጋጅበት ጊዜ ነው፡፡ ዛሬ የጀመርነው ትምህርት በአሁኑ ጊዜ ወይም በዚህ ምድር አያልቅም፡፡ ለዘለዓለም ይቀጥላል፡፡ ማለቂያ የለውም፡፡ በመዳን ዕቅድ አማካይነት የእግዚአብሔር ጥበብና ፍቅር ይገለጣል፡፡ CLAmh 188.3

አዳኛችን ልጆቹን ወደ ሕይወት ምንጭ ሲመራን በእውቀት ያበለጽገናል፡፡ የእግዚአብሔር ግሩም ሥራ፤ ዓለምን ለመፍጠርና ለማስተዳደር ያለው ኃያልነት በየዕለቱ ይገለጣል፡፡ ከዙፋኑ ዘንድ በሚበራው ብርሃን አማካይነት ምስጢር ሁሉ ይገለጣል፡፡ በፊት ከብደው የታዩት ነገሮች ግልጥና ቀላል ሆነው ሲያገኛቸው ሰውየው ይደነቃል፡፡ CLAmh 188.4

አሁን በመስተዋት እንደምናይ በከፊል እናያለን፤ ያን ጊዜ ግን ፊት ለፊት እናያለን፡፡ አሁንም ከፍለን እናውቃለን፡፡ በኋላ ግን እኛ እንደታወቅን እናውቃለን፡፡ CLAmh 188.5