የተሟላ ኑሮ

174/201

ስለእግዚአብሔር ግልጥ ማስረጃዎች

ስለእግዚአብሔር ባህርይ የተብራራ ማስረጃ ለማግኘት ከፍተኛ ጥረት የማድረግ መብት አለን፡፡ “ሙሴ እግዚአብሔርን “ክብርህን አሳየኝ “ባለው ጊዜ አልተቆጣውም፡፡ ግን ፀሎቱን ተቀበለለት፡፡ CLAmh 187.4

“እኔ መልካምነቴን በፊትህ አሳልፋለሁ፤ የእግዚአብሔርንም ስም በፊትህ አውጃለሁ” አለው፡፡ (ዘፀአት 33፡18-19) አስተሳባችንን የሚያጨልም ኀሊናችንን የሚያሳውር ኃጢአት ነው፡፡ ኃጢአት ነው፡፡ ኃጢአት ከልቦናችን ተጠርጎ ሲወጣ የእግዚአብሔርን ክብር በሚያበራው በክርስቶስ ገጽ አማካይነት ልናይ እንችላለን፡፡ ድምጹንም “መሐሪ፤ ሞገስ ያለው ታጋሽም ፤ ባለብዙ ቸርነትና እውነት ሲል እንሰማዋለን፡፡ “በብርሃኑ አማካይነት አእምሮአችን፤ ልባችንና ነፍሳችን፤ ይበራልንና ወደ ቅድስናው እንለወጣለን፡፡ CLAmh 187.5

በእግዚአብሔር መለኮታዊ ቃል ለሚያምኑ ሰዎች ሁሉ ግሩም ድርሻ ተመድቦላቸዋል፡፡ የእውነት መደብር የኃይል ምንጭ አለላቸው፡፡ የተከበሩ ነገሮች ይገለጡላቸዋል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አሉ ተብለው ያልታሰቡ መብትና ግዴታዎች መኖራቸውን ያውቃሉ፡፡የትህትናን ፈለግ በመከተል በታዛዥነት የሚኖሩ ሰዎች ስለእግዚአብሔር ቅዱስ ህግ በበለጠ ያውቃሉ፡፡ CLAmh 187.6

ተማሪው መጽሐፍ ቅዱስን ዋና መሪው አድርጎ በህግና በሥርዓት ከቆመ ሌላውን የዕውቀት ዘርፍ ሁሉ ይደርስበታል፡፡ የሰዎች ፍልስፍናዎች ከእግዚአብሔር ስለሚያርቁ በመጨረሻ ከጸጸትና ከውርደት ላይ ይጥላሉ፡፡ CLAmh 187.7

ግን በአግዚአብሔር ላይ የተመሠረተ ጽኑ እምነት ብርታትንና የጠባይ ጥራትን ያበረክታል፡፡ በደግነቱ ፤ በምህረቱና በፍቅሩ ስንጸና እውነት እየጎላች ትሄዳለች፡፡ ለአሳባችን ጥራት፤ ለልባችን ንጽህና የሚኖረን ጉጉት ከፍተኛ ይሆናል፡፡ ሕይወታችን በተቀደሰ አካባቢ ሊገኝ የሚችል በቃሉ አማካይነት ከእግዚአብሔር ጋር ቅርብ ግንኙነት ሲኖረን ነው ፡፡ እውነት ከግዝፈቱ ፤ ከርቀቱ ፤ ከጥልቀቱና ፤ ከስፋቱ የተነሣ ራሳችን ከማየት ይከልለናል፡፡ ልባችን በትህትና ፤ በገርነትና በፍቅር ይደቆሳል፡፡ CLAmh 187.8