የተሟላ ኑሮ
እግዚአብሔር የሚታወቀው በቃሉ አማካይነት ነው
እግዚአብሔር በቃሉ አማካይነት ስላውቅነው ይህን ቁም ነገር ለልጅ ልጅ ማስተላለፍ አለብን፡፡ ልጆች ማስተዋል ከጀመሩበት አንስቶ ከየሱስ ሥራና ስም ጋር መተዋወቅ አለባቸው፡፡ CLAmh 184.5
መጀመሪያ በሚማሩበት ትምህርት አማካይነት አግዚአብሔር አባታቸው መሆኑን ይወቁ፡፡ ተቀዳሚ የትምህርታቸው ዓላማ መታዘዝን እንዲወዱ መሆን አለበት፡፡ የእግዚአብሔር ቃል በአክብሮትና በትህትና ተደጋግሞ ይነበብላቸው፡፡ CLAmh 184.6
በመንፈስ ለታደለው አእምሮ መለኮታዊ ውበትና ሰማያዊ ብርሃን ከቅዱስ መጽሐፍ ዘንድ ይገልጥለታል፡፡ CLAmh 184.7
አቀራረቡም በሚያስተውሉት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ተጀምሮ የመታዘዝ ፍላገታቸውን የሚያነቃቃ ይሁን፡፡ ከሁሉም በላይ” እግዚአብሔር እንዲህ አድርጎ ከወደደን እኛ ደግሞ እርስ በእርሳችን ልንዋደድ ይገባናል፡፡ “የሚለውን በክርስቶስ አማካይነት የተገለጠውን ፍቅሩን ያስተውሉ፡፡ (1ኛ ዩሐንስ 4፡11) ፡፡ CLAmh 184.8
ለወጣቱ የእግዚአብሔር ቃል የመንፈሱና የአእምሮው ምግብ ይሁንለት፡፡ የትምህርቱ አርእስትና የምርምሩ እንብርት የክርስቶስ መስቀል ይሁን፡፡ በየዕለት ተግባሩ የተማረውን በሥራ ላይ ያውለው እንዲህ ከሆነ ክርስቶስ ለወጣቱ የቅርብ ወዳጁና የዕለት ባልደረባው ይሆናል ፡፡ አሳቡን በሙሉ ለክርስቶስ ያስገዛል፡፡ ታዲያ ወጣቱ ከጳውሎስ ጋር “ነገር ግን ዓለም ለእኔ የተሰቀለበትን ፤ እኔም ለዓለም የተሰቀልሁበትን ፤ ከጌታችን ከየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምህርት ከእኔ ይራቅ” ማለት ይችላል፡፡ (ገላቲያ 6፡14) ስለዚህ ወጣቶች በሃይማኖት ከክርስቶስ ጋር ይተዋወቃሉ፡፡ CLAmh 184.9
የቃሉን እርግጠኛነትና የተስፋውን እውነተኛነት ራሳቸው ተረድተዋል፡፡ እግዚአብሔር መልካም መሆኑን ቀምሰዋል፡፡ የተወደደው ዮሐንስ በህይወቱ የተረዳውን እውነት እንዲህ ብሎ ይመሰክራል፡፡ CLAmh 185.1
“ስለህይወት ቃል ከመጀመሪያው የነበረውንና የሰማነውን በዓይኖቻችንም ያየነውንም የተመለከትነውንም” እጆቻችንም የዳሰሱትን እናወራለን፡፡ ህይወትም ተገለጠ፤ አይተንማል፡፡ እንመሰክርማለን፤ከአብ ዘንድ የነበረውንም ለእኛም የተገለጠውን የዘለዓለምን ህይወት እናወራላችኋለን፡፡ እናንተ ደግሞ ከእኛ ጋር ኀብረት እንዲኖራቸሁ ያየነውንና የሰማነውን ለእናንተ ደግሞ እናወራለን፡፡” (1ኛ ዮሐንስ 1፡1‐‐3) CLAmh 185.2
ስለዚህ እያንዳንዱ ሰው ክርስቶስን ለግል በማወቅ “እግዚአብሔር እውነተኛ መሆኑን ይተም፡፡” የክርስቶስ ኃይል ራሱ በማየቱና በመስማቱ እንዲህ ብሎ ሊመሰክር ይችላል፡፡” የምፈልገውን ርዳታ ከክርስቶስ ዘንድ አገኛለሁ፡፡” ፍላጎቱ ሁሉ ተሟልቶልኛል፡፡ ነፍሴ ረክታለች፡ ፡መጽሐፍ ቅዱስ ለእኔ ከየሱስ ዘንድ የተላከልኝ ራዕይ ነው፡፡ መለኮታዊ አዳኜ ስለሆነ በየሱስ አምንበታለሁ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የክርስቶስ ድምጽ መሆኑን አምንበታለሁ፡፡ CLAmh 185.3
የእግዚአብሔርን ቃልና እግዚአብሔርን ለግሉ ያመነ ሰው ሁሉ የተፈጥሮ ሳይንስን ለመመራመር ይዘጋጃል፡፡ ስለክርስቶስ “በእርሱ ህይወት ነበረች ፤ ህይወትም የሰው ብርሃን ነበረች” ተብሎለታል፡፡ (ዮሐንስ 1፡4) ፡፡ ኃጢአት ወደ ኤዴን ገነት ሳትገባ በፊት አዳምና ሔዋን በእግዚአብሔር ብሩህ ብርሃን ተከበው ነበር፡፡ ያ ብርሃን ሁሉን ያበራራላቸው ነበር፡፡ CLAmh 185.4
የእግዚአብሔርን ባህርይና ሥራውን እንዳያስተውሉ የሚያደርጋቸው አንድም ነገር አልነበረም፡፡ ግን ለፈታኙ ሲጋለጡ ብርሃኑ ጨለመባቸው፡፡ የቅዱሳንን መጎናፀፊያ ካወለቁ በኃላ ተፈጥሮን የሚያበራው ብርሃን ጠፋባቸው፡፡ ከዚያ በኋላ በትክክል ሊያነቡ (ሊመለከቱት) አልቻሉም፡፡ የእግዚአብሔርን ማንነት በሥራው አማካይነት ለይቶ ማወቅ አቃታቸው፡፡ CLAmh 185.5
ዛሬም ሰው በራሱ ጥበብ ብቻ የተፈጥሮን ትክክለኛ ትርጉም ሊረዳ አይችልም፡፡ በመለኮታዊ ጥበብ ካልተመራ በቀር ተፈጥሮንና የተፈጥሮን ህግ ከእግዚአብሔር በላይ አልቆ ይመለከታል፡፡ ሰብአዊ የሳይንስ ፍልስፍና ከእግዚአብሔር ቃል ጋር የማይስማማው ስለዚህ ነው፡፡ CLAmh 186.1
ግን የክርስቶስን ህይወት ብርሃን ለሚቀበሉ ሁሉ ተፈጥሮ በግልጥ ይብራራላቸዋል፡፡ ከመስቀሉ በቀጥታ በሚበራው ብርሃን አማካይነት የተፈጥሮን ሚስጢር ይገልጥልናል፡፡ CLAmh 186.2