የተሟላ ኑሮ

171/201

32—አቻ የሌለው መጽሐፍ

መጽሐፍ ቅዱስ በክርስቶስ አማካይነት የአብን ክብር ይገልጣል፡፡ ከተቀበልነው ፤ ካመንንበትና የሚያዝዘውን ከፈጸምን ጠባይን ለመለወጥ ፍቱን መድኃኒት ነው፡፡ የአካልን ፤ የመንፈስንና የአእምሮን ኃይል የሚያጎለምስ ብርቱ ኃይል ነው፡፡ CLAmh 183.6

ወጣቶች ፤ አዋቂዎች ሳይቀሩ ፈተና የሚደርስባቸው መጽሐፍ ቅዱስን በሚገባ ስለማይከታተሉ ነው፡፡ የጸናና የጠበቀ ቆራጥነት የሚጠፋው የቃለ - እግዚአብሔር ጠቃሚነት ችላ ሲባል ነው፡፡ CLAmh 183.7

በመጽሐፍ ቅዱስ አማካይነት የተገለጠውን እውነት ተቀባይነት ካገኘ መንፈስንና አእምሮን ያፋፋል፡፡ የእግዚአብሔር ቃል ተገቢውን ግምት ቢሰጠው ኑሮ ወጣቶችም ሆኑ ሽማግሌዎች ፈተናን ሊቋቋሙበት የሚችሉ ጽኑ መመሪያ ባገኙ ነበር፡፡ CLAmh 184.1

ሰዎች ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ክቡርነት ይጻፉ፤ ያስተምሩም፡፡ የአእምሮአችን ችሎታ እስከፈቀደልን ድረስ ያን ቅዱስ መልእክት እናጥናው፡፡ የሰዎችን አጉል ፍልስፍና ከመመራመር ይልቅ እውነት የሆነውን የእግዚአብሔርን ቃል መከታተሉ ይበልጣል፡፡ CLAmh 184.2

በተጠቃሚነት በኩል የትኛውም ሥነ-ጽሑፍ ቢሆን ከእግዚአብሔር ቅዱስ መጽሐፍ ጋር እኩል አይሆንም፡፡ CLAmh 184.3

ምድራዊ አስተሳሰብ ያለው ሰው የእግዚአብሔርን ቃል ማጥናት ደስ አይለውም፡፡ ግን አእምሮው በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት የበራለት ሰው ከተቀደሱት ገጾች ዘንድ መለኮታዊ ውበትና መንፈሳዊ ብርሃን ያገኛል፡፡ በዓለማዊ አስተሳሰብ ባዶ በረሃ ሆኖ የሚገመተው በመንፈሳዊ አስተሳሰብ ግን ምንጭ የሚፈለፈልበት ለምለም መስክ ነው፡፡ CLAmh 184.4