የተሟላ ኑሮ
መስቀሉ ፍቅርን ይገልጣል
የእግዚአብሔር ፍቅር ለሰው የተገለጠው በመስቀሉ አማካይነት ነው፡፡ ሙሉ ትርጉሙ በአፍ ቢነገር፤በእጅ ቢጻፍ ተነግሮ አያልቅም፤ የሰው አእምሮም ሊያስተውለው አይችልም፡፡ CLAmh 178.1
ወደ ቀራንዮ መስቀል በመመልከት “እግኢአብሔር እንዲሁ ዓለሙን ወዷልና አንድ ልጁን እስኪለውጥ ድረሰ በእርሱ ያመነ ሁሉ እንዳይጠፋ የዘለዓለም ሕይወት ትሆንለት ዘንድ እንጂ” ማለት ብቻ እንችላለን፡፡ (ዮሀንስ 3፡16) CLAmh 178.2
ሰለ ኃጢአታችን የተሰቀለው፤የሞተው፤የተነሳውና ያረገው ክርስቶስ የመዳናችን ኃይል ነው፡፡ ሰለርሱ ተምረን ሌሎችንም ማሰተማር አለብን፡፡ CLAmh 178.3
በረከትን ሁሉ የምንቀበለው በክርስቶስ አማካይነት ነው፡፡ በእርሱ አማካይነት የልዑል አምላክ የማያልቀው በረከት በየቀኑ ይዘብልናል፡፡ የአበባዎች ውበትና መዓዛ እንድንደሰትበት የተሰጠን በእርሱ አማካይነት ነው፡፡ ፀሐይንና ጨረቃን የፈጠረ እርሱ ነው፡፡ ሰማያትን ከዋክብት ሁሉ የፈጠራቸው እርሱ ራሱ ነው፤ CLAmh 178.4
ለማያመሰግነው ዓለም የሚወርደው ጠል፤ የሚያበራው ብርሃን ሁሉ በክርስቶስ አማካይነት እግዚአብሔር በፍቅሩ የገለጠልን ነው፡፡ CLAmh 178.5
ሁሉም የተሰጠን አቻ በሌለው ስጦታ በክርስቶስ አማካይነት ነው፡፡ CLAmh 178.6
ይህ ሁሉ በረከት ለእግዚአብሔር ልጆች እንዲወርድ በመስቀል ላይ ተቸነከረ፡፡ CLAmh 178.7
” የእግዚአብሔር ልጆች “ተብለን እንጠራ ዘንድ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደሰጠን እዩ፡፡” (ዮሐንስ 3፡1) CLAmh 178.8
” ሰዎች ከጥንት ጀምሮ ለሚጠብዙህ ከምትሠራላቸው ከአንተ በቀር ሌላ አምላክን አልሰሙም፤ በጆሮአቸውም አልሰሙም ፤ሌላ አምላክም ዓይን አላየችም (ኢሳያስ 64፡4) CLAmh 178.9
የዳኑት ሁሉ እግዚአብሔርን በክርስቶስ አማካይነት ማወቅ አለባቸው፡፡ እርሱን ካወቅን ህይወታችን ይለወጣል፡፡ ይህን ዕውቀት ካወቅን ሰውነታችን የክርስቶስን አርኣያነት ይከተላል፡፡ ሙሉ ሰውነታችን መለኮታዊ በረከት ያገኛል፡፡ CLAmh 178.10
ይህንን ዕውቀት እንድንገበይ እግዚአብሔር ይጠይቀናል፡፡ ከዚህ በተረፈ ሁሉም ከንቱ እና ባዶ ነው፡፡ CLAmh 178.11