የተሟላ ኑሮ

165/201

የእውቀታችን ወሰን

በጴንጤቆስጤ ቀን መንፈስ ቅዱስ በዘነበላቸው ጊዜ ደቀመዛሙርቱ የሱስ በምሳሌ ያስተማራቸውን በሚገባ አስተዋሉት ፡፡ ምሥጢር ሆኖባቸው የነበረው ትምህርት ሁሉ ተገለጠላቸው፡፡ ያን ጊዜም ቢሆን የክርስቶስ ተስፋ በሙሉ ሲፈጸም አላዩም፡፡ ዛሬም ቢሆን ያው ነው፡፡ ስለ እግዚአብሔር ያለን ዕውቀት ያልተሟላና ፍጹም ያልሆነ ነው፡፡ CLAmh 176.3

ውዝግቡ አብቅቶ ክርሰቶስ ታማኞችን ለአብ ሲያስረክብ ዛሬ ምሥጢር የሆነባቸውን በግልጥ ይመለከቱታል፡፡ CLAmh 176.4

ክርስቶስ የከበረውን ሰብአዊነቱን ወደ ሰማይ አደባባይ ይዞ ሄደ፡፡ ለሚቀበሉት ሁሉ የእግዚአብሔር ልጆች እንዲሆኑ ሥልጣን ይሰጣቸዋል፡፡ በመጨረሻም አብ ለልጆቹ እንዲሆኑ ለዘለዓለም ይቀበላቸዋል፡፡ CLAmh 176.5

ዛሬ ታማኝ የሆነ ሁሉ “ፊቱን ያዩታል፤ ስሙም በግምባራቸው ይሆናል ፡፡” (ራዕይ 20፡4) የእግዚአብሔርን ፊት ከማየት የበለጠ በሰማይ ምን ደስታ አለ? በክርስቶስ ጸጋ የዳነው ኃጢአተኛ የአግዚአብሔርን ፊት ተመልክቶ አባቱ መሆንኑ ከማወቅ ሌላ ምን ደስታ ይፈልጋል? CLAmh 176.6

መጽሐፍ ቅዱስ በአብና በወልድ መካከል ያለውን ግንኙነት ከማብራራቱም በላይ ልዩነታቸውንም በግልጥ ያስረዳል፡፡ “ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በብዙ ዓይነትና በብዙ ጎዳና ለአባቶቻችን በነቢያት ተናግሮ በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረ፡፡ እርሱም የክብሩ መንጸባረቅና የባሕርይው ምሳሌ ሆኖ ሁሉን በሥልጣኑ ቃል እየደገፈ ኃጢአታችንን በራሱ ካነፃ በኋላ በሰማያት በግርማ ቀኝ ተቀመጠ፤ ከመላእክት ይልቅ እጅግ የሚበልጥ ስምን በወረሰ መጠን እንዲሁ ከእነርሱ አብዝቶይበልጣል፡፡” CLAmh 176.7

“ከመላእክትስ-አንተ ልጄ ነህ እኔ ዛሬ ወልጄሃለሁ ደግሞም-እኔ አባት እሆናለሁ እርሱም ልጄ ይሆናል ያለው ከቶ ለማነው?” (ዕብራውያን 1፡1-5) ፡፡ CLAmh 176.8

የአብና ወልድ ልዩነት እንዲሁም አንድነታቸው ክርስቶስ ለደቀመዛሙርቱ በጸለየው ጸሎት በዮሐንስ ወንጌል ምራዕፍ 17 ተገልጧል፡፡ CLAmh 177.1

“ሁሉም አንድ ይሆኑ ዘንድ ከቃላቸው የተነሣ በእኔ ሰለሚያምኑ ደግሞ እንጅ ስለ እነዚህ ብቻ አልለምንም፡፡ አንተ እንደላክኸኝም ዓለም ያምን ዘንድ አንተ አባት ሆይ፤በእኔ እንዳለህ እኔም በአንተ እነርሱም ደግሞ በእኛ አንድ ይሆኑ ዘንድ እለምናለሁ ፡፡” (ዮሐንስ 17፡20-21) ፡፡ CLAmh 177.2

በክርስቶስና በደቀመዛሙርቱ መካከል ያለው አንድነት ማንነታቸውን አያጠፋባቸውም፡፡ በአሳብ፤ በጠባይ፤ በአስተሳስብ አንድ ይሁኑ እንጂ በአካል አንድ አይደሉም፡፡ የአብና የወልድ አንድነትም እንደዚሁ ነው፡፡ CLAmh 177.3

ክርስቶስ ሰናአዊነቱን ለብሶ ከሰዎች እንደ አንዱ ሆኖ ፤በተጨማሪም ለኀጢአተኛው ሰብአዊ ፍጡር አብን ገለጠለት፡፡ CLAmh 177.4

ለሰው ዘር መለኮትን ሊገልጥ የሚችል ከጥንት ጀምሮ ከአብ ጋር የነበረው የማይታየው አምላክ አምሳያ የሆነው እርሱ ብቻ ነበር፡፡ በሁሉም ነገር ወንድሞችን መሰለ፡፡ እንደኛ ሥጋ ለበሰ ፡፡ ተራበ፣ተጠማ፣ ደከመ፡፡ ሲርበው ይበላ፤ሲደክመው ያርፍ ነበር፡፡ የሰዎችን ዕድል ተካፈለ፤ ግን ነውር የሌለበት የእግዚአብሔር ልጅ ነበር፡፡ በምደር ላይ እንግዳና መፃተኛ ነበር፡፡ የዘመናችን ሰዎች እንደሚፈተኑት ቢፈተንም ከኃጢአት የራቀ ኑሮ ኖረ ፡፡ ርኀሩኀ፤ አፍቃሪ፤ አዛኝ ለሌሎች አሳቢ በመሆኑ የአግዚአብሔርን ባሕርይ ለሰዎች ገለጠ፡፡ CLAmh 177.5

ዘወትር አግዚአብሔርንና ሰውን ያገለግላል ነበር፡፡ “የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው ለድሆች የምስራች እሰብክ ዘንድ እግዚአብሔር ቀብቶኛል፤ልባቸው የተሰበረውን እንጠግን ዘንድ ለተማረኩትም ነፃነት፤ ለታስሩትም መፈታትን እናገር ዘንድ ልኮኛልና፡፡” ለዕውሮችም ማየትን እሰብክ ዘንድ “የተወደደችውን የእግዚአብሔርን ዓመት እናገር ዘንድ፤የሚያለቅሱትንም ሁሉ አጽናና ዘንድ፡፡” (ኢሳይያስ 61፡1 ፤ ሉቃስ 4፡18 ኢሳይያስ 61፡2) ፡፡ CLAmh 177.6

“በሰማይ ላለው አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ የሚረግሟችሁን መርቁ ፤ለሚጠሏችሁም መልካም አድረጉ ፤ለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤እርሱ በክፉዎችና በበጎች ላይ ዝናብን ያዘባልና፡፡” (ሉቃስ 6፡35 ፤ ማቴዎስ 5፡45) CLAmh 177.7

“አባታችሁ ርኀሩኀ እንደሆነ እናንተም ርኀሩኀ ሁኑ (ሉቃስ 6፡36) ፡፡ CLAmh 177.8