የተሟላ ኑሮ

17/201

በሕይወት ውስጥ የተሻሉት ነገሮች

ሰው ለልጆቹ ሊያወርሳቸው ከሚችለው ቅርስ ሁሉ ብልጫ ያለው የአካልና የአዕምሮ ጤናና ጥሩ ጠባይ ናቸው፡፡ የሕይወትን እውነተኛ ክንውን የሚያስገኙትን ነገሮች የሚያውቁ ሰዎች በቶሎው አስተዋይ ይሆናሉ፡፡ ትዳር በሚያቋቁሙበት ጊዜ ዋና አሳባቸው ስለ ሕይወት ምርጥ ነገሮች (የተሻሉ) ነገሮች ነው፡፡ CLAmh 19.3

ሰው ሠራሽ ነገር ብቻ ከሚታይበት የሚታየውና የሚሰማው ሁሉ ወደ መጠፎ ሐሳብ ከሚመራበት ቦታና ብጥብጥና ትርምስ ሰላም ከሚነሣበት ቦታ ላይ ከመኖር የእግዚአብሔርን ሥራ ልታይበት ወደምትችልበት ቦታ ሒድ፡፡ የስነ ፍጥረት ውበት፣ ጸጥታና ሰላም በሚገኝበት ቦታ መንፈስህ ይረፍ፡፡ ዓይኖችህ በበልግ በተሸፈኑት መስኮች፣ በለምለም ዛፎችና በተራራዎች ላይ ይረፉ፡፡ በከተማ አብዋራና ጭስ ወዳልተበከለው ጥቁር ሰማይ እየተመለከትህ ኃይል የሚሰጠውን የሰማይን አየር ሳብ፡፡ ከከተማ ጋጋታና ጩኸት ውጣና ልጆችህ ጓደኝነትህን ወደሚያገኙበት፣ በስነፍጥረት አማካይነትም ስለእግዚአብሔር ልታስተምራቸው ወደምትችልበትና የተሟላና ጠቃሚ የሆነ ሕይወት እንዲኖሩ ልታሰለጥናቸው ወደምትችልበት ቦታ ሒድ፡፡ CLAmh 20.1

ሰው ሠራሽ የኑሮ ጠባያችን ብዙ በረከትና ደስታ ያስቀርብናል፤ በዚህም ምክንያት በጣም ጠቃ የሆነ ሕይወት ለመኖር የማንገጥም እንሆናለን፡፡ በጣም ውድ የሆኑ ብዙ የቤት ዕቃዎች መግዛት ገንዘብ ማባከን ከመሆኑም በላይ በቤት ውስጥ ሥራና ጣጣ ያበዛሉ፡፡ CLAmh 20.2

በብዙ ቤተሰብ ባለቤቲቱ ለማንበብ፤ የጊዜውን መሻሻል ለመከታተል፤ የባልዋ ጓደኛ ለመሆንና የልጆችዋንም የአእምሮ እድገት ለመከታተል ጊዜ የላትም፡፡ የተከበረው መድኃኒታችን የቅርብ ጓደኛዋ እንዲሆን ጊዜና ቦታ አትሰጠውም፡፡ የቤትዋ እመቤት ትንሽ በትንሽ የቤት አገልጋይ በመሆንዋ ኃይልዋ፣ ጊዜዋና ምኞትዋ ሁሉ ከምትጠቀምባቸው ነገሮች ጋር አብረው ይጠፋሉ፡፡ ልጆችዋን ለተሻለ ሕይወት ለማዘጋጀት የነበራት የተከበረ ዕድልም ሳትጠቀምበት ያልፋል፡፡ CLAmh 20.3