የተሟላ ኑሮ

15/201

ሰው ሰራሽ የከተማ ሕይወት

የከተማ ሕይወት ሰው ሠራሽ ነው፡፡ ገንዘብ ማሳደድ ደስታ ለማግኘት የሚደረግ ጥረት፣ የታይታ ምኞትና ምቾት ለማግኘት የሚደረገው የገንዘብ ማባከን፣ የብዙ ሰዎችን አንጎል ከእውነተኛው ሕይወት አርቆታል፡፡ በተጨማሪም እነዚህ ነገሮች በሺህ ለሚቆጠሩ የአመጽ ሥራዎች በር ከፍተውላቸዋል፡፡ እነዚህንም የአመጽ ሥራዎች ወጣቶች ሊከላከሏቸው አይችሉም፡፡ CLAmh 18.2

ለወጣቶችና ለሕፃናት በጣም አስጊና አልባሌ ከሆኑ ፈተናዎች አንዱ ደስታ የማግኘት ፍላጎት ነው፡፡ ዓመት በዓሎች እጅግ በዝተዋል፤ የጨዋታ ውድድር በሺህ የሚቆጠሩትን ይስባል፤ ደስታ ለማግኘት ያለው ዲልቃ ከትክክለኛዎቹ የሕይወት ተብባሮች አርቋቸዋል፡፡ ለተሻለ ጥቅም ሊውል የሚገባው ገንዘብ ለመደሰቻ ይባክናል፡፡ በዚህ አያያዝ ለወደፊቱ የከፋ ችግር ይጠብቀናል፤ ብዙ ቤተሰቦችም ከከተማ መውጣት ግድ ይሆንባቸዋል፡፡ CLAmh 18.3

የከተማ ኑሮ የጤና ፀር ነው፡፡ በከተማ ውስጥ ከሚገኙት መጥፎ ነገሮች ጥቂቶቹ የአየር መቆሸሽ፣ የውኃ መቆሸሽ፣ የምግብ መቆሸሽ፣ የቦታ ጥበትና የደዌ ብዛት ናቸው፡፡ CLAmh 18.4