የተሟላ ኑሮ

128/201

“የሚበሉት ስጧቸው”

ቀኑን ሙሉ ሕዝቡን የሱስ ሲስተምራቸው ስለዋለ ከእርሱና ከደቀመዛሙቱ አልተለዩም ነበር፡፤ ትምህርቱ ግልጥና የሚስተዋል ስለነበር ለነፍሳቸው ፈውስ ሆነላቸው፡፡ ፈዋሽ የሆነው መለኮታዊ እጁ ለድውያን ጤና፤ ሊሞቱ ለተቃረቡት ሕይወት ሰጣቸው፡፡ ያ ዕለት ገነት በምድር ሆኖ ዋለላቸው፡፡ ያለምግብ መዋላቸውንም እረስተውት ነበር፡፡ CLAmh 138.3

ፀሐይ ልትጠልቅ ብትቃረብም ሕዝቡ አልተበተነም፡፡ ደቀመዛሙርቱ ወደ የሱስ ቀረቡና ሰዎቹ ቢሰናበቱ መሻሉን ነገሩት፡፡ ብዙዎቹ ራቅ ካለ ቦታ ተነሥተው ከመምጣታቸው በላይ ከጥዋት ጀምረው ምንም አልቀመሱም ነበር፡፡ በአካባቢው ባሉት ከተሞች ምግብ ቢፈልጉ እንደማያጡ አስገነዘቡት፡፡ የሱስ ግን “የሚበሉት አቅርቡላቸው” አለ፡፡ (ማቴዎስ 14፡16) ፡፡ ወደ ፊሊጶስ ዘወር አለና “የሚበሉት ምግብ ከየት እንገዛለን?” ብሎ ጠየቀው፡፡ CLAmh 138.4

ፊሊጶስ ወደ ሕዝቡ ተመለከተና ለዚያ ሁሉ ሕዝብ ምግብ መግዛት የማይቻል መሰለው፡፡ CLAmh 138.5

ለቅምሻ ያህል እንኳን የሁለት መቶ ሳንቲም ምግብ አለመብቃቱን ተናገረ፡፡ የሱስም ምን ያህል ምግብ እንዳለ ጠየቀ፡፡ እንድርያስም “አምስት የገብስ እንጀራና ሁለት አሣዎች የያዘ አንድ ልጅ አለ፤ ግን ይች ለዚህ ያህል ሕዝብ ከምን ትደርሳለች?” አለ፡፡ (ማቴዎስ 15፡9) ፡፡ የሱስ ምግቡን እንዲያቀርቡለት አዘዘ፡፡ ባቀረቡለት ጊዜ “ወደ ሰማይ ተመልክቶ አመሰገነና ምግቡን ቆረሰው፤ ለደቀመዛሙርቱ ሰጣቸው እነርሱም ለሕዝቡ አሳለፉ፡፡ ሁሉም በልተው ጠገቡ፡፡ የተረፈውም ሲሰበሰብ አስራ ሁለት ሞሰብ ሞላ፡፡ (ማቴዎስ 14፡19፣20) CLAmh 138.6