እግዚአብሄር ቃል ገብቷል

6/16

መከራችሁ ከኣቅማችሁ በላይ ሆኖባችኋል?

በውሃ ውስጥ በምታልፍበት ጊዜ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤
ወንዙን ስትሻገረው አያሰጥምህም፤ በእሳት ውስጥ ስትሄድ
አያቃጥልህም፤ ነበልባሉም አይፈጅህም፡፡
ኢሳ 43፡2

ጸጋዬ ይበቃሃል፤ ኃይሌ ፍጹም የሚሆነው
በድካም ጊዜ ነውና፡፡
2 ቆሮ 12፡9

መከራን እንድንታገስ መመረጣችን፣ ጌታ ኢየሱስ በእኛ ውስጥ እንዲያድግ የሚፈልገውን የከበረ ነገር ማየቱን ያስረዳናል፡፡ በእኛ ውስጥ ለስሙ ክብር የሚሆን ምንም ነገር ባያይ ኖሮ፣ እኛን ለማንጠር ጊዜ ባላጠፋ ነበር፡፡ እርሱ ዋጋቢስ ድንጋዮችን ወደ ማንጠሪያ እሳቱ ውስጥ አይጨምርም፡፡ እቃገ 23.1

እግዚአብሔር ወደ ልጆቹ መከራን ሲልክ ዓላማ አለው፡፡የመጨረሻውን ከመጀመሪያው ማየትና በመከራቸው ውስጥ የሚያከናውኑትን የዓላማ ክብር ማስተዋል ቢችሉ ኖሮ፣ እነርሱ ለራሳቸው ከሚመርጡት መንገድ በተቃራኒ እግዚአብሔር ፈጽሞ እንደማይመራቸው ይረዱ ነበር፡፡ እቃገ 23.2

እግዚአብሔር ልጆቹ በከባድ መከራ ውስጥ በሚያልፉበት ጊዜ የሚያሳያቸው ፍቅር፣ ድምቅ ባሉት የብልጽግና ቀናት መካከል እንደሚያሳያቸው ያለ ጠንካራ ፍቅር ነው፡፡ ሰማንኛውም ድንገተኛ ነገር ውስጥ የጌታን ጥበብ ፈልጉ፡፡ በእያንዳንዱ መከራም ውስጥ ከችግራችሁ የምትወጡበትን መንገድ እንዲያሳያችሁ ወደ ኢየሱስ ልመናችሁን አቅርቡ፤ በዚያን ጊዜዓይናችሁ ይከፈትና መፍትሔውን ታያላችሁ፤ በቅዱስ ቃሉ ውስጥ የተዘገበውን ፈዋሽ የተስፋ ቃል ላላችሁበት ሁኔታ ገጣሚ በሆነ መልኩ መጠቀም የሚያስችላችሁን ማስተዋል ታገኛላችሁ፡፡ በዚህ መንገድ ስትኖሩ ጠላት ወደ ልቅሶና ወደ አላማመን እናንተን ለመምራት መንገድ ያጣል፤ በአንጻሩ በጌታ ላይ እምነት፣ ተስፋና ድፍረትን ታገኛላችሁ፡፡ ... እያንዳንዱ የመራርነት ድርቅ ከኢየሱስ ፍቅር ጋር የተቀላቀላ ይሆናል፤ ስለ መራር ሁኔታው ከማማረር ይልቅ የኢየሱስ ፍቅር ከሰቆቃው ጋር ከመቀላቀሉ የተነሳ ወደ ቅዱስ ደስታ እንደለወጠውታስተውላላችሁ፡፡ እቃገ 23.3

የተወደደው አዳኝ ሰሚያስፈልገን ትክክለኛ ጊዜ ላይ እርዳታውን ይልክልናል፡፡ ወደ ሰማይ የሚወስደው መንገድ የእርሱ ዱካ ያረፈበት ነውና የተለየ ነው፡፡ በዚያ መንገድ ላይ የእኛን እግር የሚወጋ እሾህ ሁሉ እርሱንም ወገቶታል፡፡ እንድንሸከመው የተጠራነውን እያንዳንዱን መስቀል እርሱ አስቀድሞ ተሸክሞታል፡፡ ጌታ ነፍስን ለሰላም ለማዘጋጀት፣ ግጭቶችን ይፈቅዳል፡፡ እቃገ 24.1

በሰማይ ያለው አባታችን የሚያስፈልገንን ነገር ላመስጠት፣ እኛ ፈጽሞ የማናውቃቸው እልፍ መንገዶች አሉት፡፡ የእግዚአብሔርን አገልግሎትና ክብር ከሁሉም በላይ ማድረጎን የህይወት መመሪያቸው አድርገው የተቀበሉ ሁሉ፣ ጭንቀት ከእነርሱ ይርቃል፤ ለእግራቸውም መርገጫ ምቹ ስፍራን ያገኛሉ፡፡ እቃገ 24.2

በመጨረሻ ድል ነሺ የሚሆኑ ሁሉ በመንፈሳዊ ህይወታቸው እጅግ አስጨናቂና ፈታኝ የሆነን ጊዜ ያሳልፋሉ፡፡ ነገር ግን ተስፋ ሌቆርጡ አይገባም፡፡ ምክንያቱም ይህ በክርስቶስ ትምህርት ቤት ከሚሰልጥኑበት መንገድ አንዱ ነውና፤ ከተለወሱበት ቆሻሻ ለመጥራትም ወሳኝ ነው፡፡ እቃገ 25.1

በእምነት ከተቀበልነው፣ በጣም መራራና ከባድ የሚመስለው መከራ በረከት ይዞልን ይመጣል፡፡ በምድር ላይ ያለንን ደስታ ለማጥፋት የሚሰነዘርብን በጭካኔ የተሞላ ጡጫ፣ ዓይናችንን ወደ ሰማይ እንድናነሳ ቀና የሚያደርገን ይሆናል፡፡ መከራ በጌታ ወዳለው መጽናናት ባያመራቸው ኖሮ፣ ኢየሱስን ሊያውቁ የማይችሉ ስንቶች ነበሩ! እቃገ 25.2

መከራችንን፣ ምሬታችንንና ሰቆቃችንን ለማስፈር የባህር መዝገብ አያስፈልገንም፡፡ እነዚህ ሁሉ በመጽሐፍቱ ላይ ተጽፈዋል፤ ሰማይም የሚከታተላቸው ናቸው፡፡ አዳኙ በፈተናና በመከራ ውስጥ ካሉት ጎን ይገኛል፡፡ በእርሱም ዘንድ ውድቀት፣ ኪሳራ፣ የማይታሰብ ነገር ነው፡፡ ሽንፈትም የለም፡፡ እቃገ 25.3