እግዚአብሄር ቃል ገብቷል
ተስፋ ቆርጣችኋል?
አንተን ተስፋ የሚያደርጉ፣ ከቶ አያፍሩም
መዝ 25፡3
እርሱን ተስፋ ለሚያደርጉት፣ ለሚፈልገውም ሰው
እግዚአብሔር መልካም ነው፡፡ ሰው የእግዚአብሔርን ማዳን
ዝም ብሎ ተስፋ ቢያደርግ መልካም ነው፡፡
ለቆ ኤር 3፡25-26
ነፍስን ተስፋ ማስቆረጥ የሰይጣን ስራ ነው ፤ በተስፋና በእምነት መሙላት ደግሞ የክርስቶስ ተግባር ነው፡፡ እቃገ 20.1
ሰይጣን ከእግዚአብሔር የተቀበልነውን የተባረከ ዋስትና ሊዘርፈን ሁልጊዜ ዝግጁ ነው፡፡ ማንኛውንም የተስፋ ጭላንጭል ሊያጠፋ ይሻል፤ ነገር ግን ይህንን እንዲያደርግ ልትፈቅዱላት አይገባም፡፡ እምነትን ተለማመዱ ፤ የእምነትንም መልካሙን ገድል ተጋደሉ፤ ከእነዚህ ጥርጣሬዎች ጋር ተፋለሙ ፤ ከጌታ የተስፋ ቃሎች ጋር ራሳችሁን አስተዋውቁ፡፡ እቃገ 20.2
የክርስትና ሕይወት ብዙዎች ከሚያስቡት በላይ ነው፡፡ ገርነት፣ ትዕግስት፣ የዋህነትና ቸርነትን ብቻ የያዘ አይደለም፡፡ እነዚህ ባህሪዎች አስፈላጊ ናቸው፤ ነገር ግን ድፍረት፣ ኃይል፣ ጉልበትና እቃገ 20.3
ጽናትም ያስፈልጋሉ፡፡ ክርስቶስ ያዘጋጀልን መንገድ ጠባብና ራስን የመካድ መንገድ ነው፡፡ በዚያ መንገድ ለመጓዝ እንዲሁም ከአስቸጋሪና ተስፋ አስቆራጭ ሁኔታዎች ጋር ለመፋለም እቃገ 20.4
ልፍስፍስነትን ማስወገድ ይጠይቃል፡፡ እቃገ 20.5
ስለ ተስፋ መቁረጣችሁ ከማሰብ ይልቅ፣ በክርስቶስ ስም ልትቀዳጁ ስለምትችሉት ኃይል አስቡ፡፡ ... እግዚአብሔር ለእናንተ ያለውን ታላቅ ፍቅር ያሳየባቸውን ማረጋገጫዎች አሰላስሉ፡፡ እምነት በመከራ መጽናትን፣ ፈተና መቋቋምንና ሰተስፋ አስቆራጭ ሁኔታዎች ውስጥ መሻገርን ያስችላል፡፡ ኢየሱስ የእኛ ጠበቃ ሆኖ ይኖራል፤ በእርሱ አማካይነት የሚገኘው ነገር ሁሉ የእኛ ነው፡፡ ... የምናልፍባቸው ሁኔታዎችና የምናካብታቸው ልምዶች ሁሉ፣ እግዚአብሔር ለእኛ መልካምን ነገር የሚያቀዳጅባቸው መሳሪያዎቹ ናቸው፡፡ እቃገ 21.1
በእምነት የእርሱን ብርታት ስንጠማጠም፣ ተስፋቢስና እጅግ አሳዛኝ የሚመስለውን በአስገራሚ ሁኔታ ይለውጠዋል፡፡ ሰምሬት በተሞሉ ቃላተ የእግዚአብሔርን ክብር አታሳንሱ፤ ይልቁንም በልባችሁ፣ በነፍሳችሁና በድምጻችሁ እርሱን አወድሱ፡፡ ... ይህንን በማድረግ፣ ነገሮች እንዴት ወደ ጥሩ ሁኔታ እንደሚላወጡ ተመልከቱ፡፡ እቃገ 21.2
አንዳንዶች ሁልጊዜ የሚመለከቱት ተስፋ አስቆራጭ ሁኔታዎችን ነው፡፡ ሰውጤቱም ተስፋ መቁረጥ ሰህይወታቸው ይነግስባቸዋል፡፡ ሰማይ ላዓለም የበረከት ወኪሎች ሊያደርጋቸው እንደሚጠባበቅና ሰብአዊ ፍጥረት ብርታትና ድፍረትን ሊያገኝ የሚችልበት ፈጽሞ የማይነጥፍ ምንጭ ኢየሱስ እንደ ሆነ ይዘነጋሉ፡፡ በሃዘን መቆዘም ፈጽሞ አያስፈልግም፡፡ በዚህ ምድር የሰይጥን ጥላ በመንገዳችን ላይ የማይኖርበት ጊዜ ፈጽሞ አይመጣም፡፡ ... ነገር ግን እምነታችን ይህንን ጥላ ሰንጥቆ ሊያልፍ ይገባል፡፡ እግዚአብሔር ሰተቃዋሚ ኃይላት ተስፋ ላለመቁረጥ እምቢ ያሉ ደስተኛ የስራ አጋሮችን ይጣራል፡፡ ጌታ እየመራን ነው ፤ ባለፉት ዓመታት ከእኛ ጋር እንደነበረ ለወደፊትም ከእኛ ጋር እንደሚሆን በመተማመን፣ በድፍረትም ወደ ፊት መሄድ እንችላለን፧ ጌታ እየመራን። እቃገ 21.3
ቶሎ ብለን ተስፋ ባለመቁረጥ መጽናት እንችል ዘንድ ትዕግስትን እንዲሁም ድል እንድንነሳ ጸጋን መጠየቅ ሲገባን መከራችን ከእኛ እንዲወገድ አጥብቀን እንጮሃለን፡፡ እቃገ 22.1
እግዚአብሔር ለሕዝቡ ያለውን ፍቅር አይቻለሁ፥ እጅግ ታላቅ ነው፡፡ ተወሳእክተ ሰቅዱሳን ላይ ክንፋቸውን ዘርግተው አየሁ፡፡እያንዳንዱ አማኝ የሚጠነቀቅለት መልአክ ኣለው። ቅዱሳን በተስፋ መቁረጥ ሲያነሱ፤ ወይም በአደጋ ውስጥ ሲወድቁ፡ የሚጠብቁዋቸው መላእክት ዜናውን ለማሰማት በፍጥነት ወደ ሰማይ ይሰራሉ፤ በሰማያዊው ከተማ ያሉ መላዕክትም መዘበራቸውን ያቆማሉ፡፡ ... በከተማይቱ ያሉት መላዕክትም ሁሉ ያለቅሳሉ። ... ነገር ግን ቅዱሳን በፊት ለፈታቸው ሽልማታቸው ላይ ዓይናቸውን ሲተክሉ፡ እግዚአብሔርንም በማመስገን ሲያከብሩት፡ መላእክቱ መልካሙን ዜና ይዘው ወደ ሰማይ ይበራሉ፤በከተማይቱ ውስጥ ያሉት መላእክትም ወርቃማውን በገናቸውን በመደርደር ከፍ ባለ ድምጽ ይዘምራሉ፡፡... ከዚያም የሰማይ ሰራዊት በጣፋጭ ዝማሬ ድምጻቸውን ያስተጋባሉ። እቃገ 22.2