የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡

33/126

የመዘግየት አሥጊነት፡፡

በሌሊት ራእይ እጅግ ልብ የሚነካ ትርኢት (ሁኔታ) በፊቴ አለፈ፡፡ ታላቅ የእሳት ኳስ በአንዳንዶቹ ያማሩ ቤቶች ላይ ወድቆ ድራሻቸውን ሲያጠፋ አየሁ፡፡ አንዱም ‹‹የእግዚአብሔር ፍርዶች በምድር ላይ መውረዳቸውን እናውቅ ነበር፤ ግን እንዲህ በተሎ እንደሚመጡ አላወቅንም›› ሲል ሰማሁ፡፡ ሌሎችም በተጨነቁት ድምጾች፤ ‹‹ለካ አውቀሃል እንግዲያውስ ለምን አልነገርህንምአ እኛ አላወቅንም›› አሉ፡፡ በሁሉም በኩል ይህን የመሰሉ የወቀሳ ቃላት ሲነገሩ ሰማሁ፡፡ CCh 64.4

በታላቅ ጭንቀት ነቃሁ፡፡ እንደገና ልተኛ ሔድሁ በታላቅ ስብሰባ ውስጥ ያለሁ ይምስለኝ ነበር፡፡ የዓለም ካርታ ተዘርግቶ ለነበረው ጉባዔ (ኮምፓኒ) አንደኛው ባለ ሥልጣን ሲናገር ነበር፡፡ ካርታው ሊታረስ ስለሚገባው የእግዚአብሔር ወይን ቦታ የሚያመለክት እንደሆነ ተናገረ፡፡ ከሰማይ ብርሃን በማናቸውም ላይ ሲበራ ያይኛው ብርሃኑን ለሌሎች ማብራት አለበት፡፡ ብርሃናት (መብራቶች) በብዙዎች ሥፍራዎች እንዲነዱ ነበር፤ ከነዚህም መብራቶች ሌሎች መብራቶች ደግሞ እንዲቀጣጠሉ ነው፡፡ CCh 65.1

‹‹እላንት የምድር ጨው ናችሁ ጨው ግን አልጫ ከሆነ በምን ይጣፍጣል የሚረባው የለም፡፡ ሜዳ ይጣላል እንጅ ሰውም ይረግጠዋል፡፡ እላንት የዓለም ብርሃን ናችሁ አገር በተራራ ላይ ተሰርታ መሠወር አይቻላትም፡፡ መብራትም አያበሩም በንቅብ ውስጥ ሊያኖሩት በመቅረዙ ላይ እንጅ በቤት ላሉት ሁሉ እንዲያበራ፡፡ እንዲሁ በርሃናችሁ በሰው ፊት ይብራ መልካሙን ስራችሁን አይተው የሰማዩን አባታችሁን ያመሰግኑት ዘንድ›› የሚሉ ቃላት ተደጋግመው ተነግረዋል፡፡ ማቴ ፭ ፲፫ ፲፮ CCh 65.2

የሚያልፈው ቀን ሁሉ ወደ ፍጻሜ ያቀርበናል፡፡ ወደ እግዚአብሔር ደግሞ የሚያቀርበን ነውንነ በጸሎት እንተጋለንንእ ዕለት ዕለት አብረናቸው የምንሆን (የምንገናኛቸው) እርዳታችንና መሪነታችንን ይፈልጋሉ፡፡ በእንዲህ ያለ የአሳብ ሁኔታ ይኸውም በጊዜው የሚነገረው ቃል በተረጋገጠው ሥፍራ ውስጥ እንደተቸነከረው ምሥማር በመንፈስ ቅዱስ እቤት ይላክላቸው ይሆናል፡፡ ነገ ከእነዚህ ነፍሳት አንዳንዶቹ እነደገና ከቶ ልንደርስባቸው ከማንችልበት ሥፍራ ይሆኑ ይሆናል፡፡ ለነዚህ ጓድ ጉዘኞች የምናሳያቸው አርአያነታችን ምንድን ነውነ ወደ ክርስቶስ ልንመልሳቸው ምን ጥረት እናደርጋለንእ ፱9 CCh 65.3

መላእክት አራቱን ነፋሳት ሲይዙ ሳለ ባለን ችሎታዎች ሁሉ መሥራት አለብን፡፡ ከቶውን ሳንዘገይ መልእክታችንን ማድረስ አለብን፡፡ ሃይማኖታችን ከርስቶስ ዋናው (ደራሲው) የሆነና ቃሉም መለኮታዊ መግለጫ የሆነ እምነትና ኃይል መሆኑን ለሰማያዊ ዓለማትና (ዩኒቨርስና) በዚህ የከፋ ዘመን ላሉት ሰዎች አስረጅ መስጠት ይገባናል፡፡ ሰብዓዊ ነፍሳት በሚዛን ውስጥ ተሰቅለዋል፡፡ ለእግዚአብሔር መንግሥት ዜጋዎች ይሆናሉ፤ ወይም ለሰይጣን የግፍ አገዛዝ ባሮች ይሆናሉ፡፡ ሁሉም በወንጌል እፊታቸው የቀረበላቸውን ተስፋ ይጨብጡ ዘንድ መብት ሊኖራቸው አለባቸው እንግዲህ የለ ሰባኩ እንዴት ሊሰሙ ይችላሉይ ሰብዓዊ ቤተሰብ በአምላክ ፊት እንዲቆሙ የግብረገብ (የሞራል) እንደገና መታደስ የጠባይ ዝግጅት ያስፈልጋቸዋል፡፡ ከሚያዩሉባቸው ስህተቶች የተነሣና የወንጌልን መልእክት መቃወማቸው እንደሆነ ስለሚቆጠርባቸው ለመጥፋት ዘግጁዎች የሆኑ ነፍሳት አሉ፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር ባንድነት የሚሠሩ ሰራተኞች ይሆኑ ዘንድ አሁን በምሉ ለእግዚአብሔር ራሳቸውን ቀድሰው የሚሰጡ እነማን ናቸውና ፲10 CCh 65.4

ዛሬ አብዛኞቹ ከጉባዔዎቻችን ውስጥ ያሉት በግፍና በኃጢአት የሞቱ ናቸው፡፡ እነሱ በማጠፊያዎቹ ላይ እንዳለው በር ይመጣሉ፤ ይሔዳሉም፡፡ ለብዙ ዓመታት እጅግ ጥብቅ ስለ ሆነው ነፍስን የሚያነቃቃ እውነት በደስታ ሰምተዋል፤ ግን ሥራ ላይ አላዋሉትም፡፡ ስለዚህ ስለ እውነቱ ክቡርነት (ተወዳጅ ነት) ስማታቸው እያነሰና እየተቀነሰ ሔደ፡፡ የሚያነቃቁ የግሣጼና የማስጠንቀቂያ ምሥክሮች ወደ ንስሐ አያነቋቋቸውም፡፡ በስብዓዊ ከንፈሮች አማካይነት ከአምላክ የሚመጡላቸው እጅግ ጣፋጭ የሆኑ ዜማዎች ማለት በኃይማኖት መጽደቅና የክርስቶስ ጽድቅ የፍቅርና የምሥጋና መልስ ከነሱ የሚያስገኝ አይደለም፡፡ ሰማያዊው ነጋዴ የኃይማኖትንና የፍቅርን የበለጸጉትን ዕንቁዎች እፊታቸው ቢያደርግላቸውም እንኳ፤ ‹‹የዓይንም ኩል› እንዲያዩ ከርሱ ይገዙ ዘንድ ቢያድማቸውም በርሱ ላይ ልባቸውን ያደነድናሉ፤ ለብነታቸውን ለፍቅርና ለመንፈሳዊ ቅናት አይለውጡም በስም ክርስቲያደንነታቸው ሱገልጹ የመለኮታዊ አምልኮን ኃይል ይክዳሉ፤ በዚህ ሁናቴ ቢቀጥሉ እግዚአብሔር ችላ ይላቸዋል፡፡ የቤተሰቡ አባሎች እንዳይሆኑ ራሳቸውን ያልተገቡ ማድረጋቸው ነው›› ፲፩11 CCh 65.5

ስሞቻቸው በቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት ውስጥ መጻፋቸው የማያድናቸው እንደሆነ የቤተ ክርስቲያን አባሎች ይገንዘቡ፡፡ እነሱ እግዚአብሔር የተደሰተባቸው ሊያፍሩ የማያስፈልጋቸው ሰራተኞች እንደሆኑ ራሳቸውን ማሳየት አለባቸው፡፡ ዕለት ዕለት በክርስቶስ አመራር መሠረት ጠባያቸውን መገንባት አለባቸው ዘወትር በርሱ እያመኑ በርሱ መጽናት አለባቸው፡፡ በእንዲህ በክርስቶስ ለዓቅመ አዳምና ሔዋን ሙሉ እድገት ያገኛሉ ይኸውም ባለጤናዎች ደስተኞች አመሰጋኞች ክርስቲያኖች እይተገለጸላቸውና እይተብራራላቸው ወደሚሔደው ብርሃን በእግዚአብሔር የተመሩ ይሆናሉ፡፡ ይህ ልምዳቸው ካልሆነ አንድ ቀን ድምጻቸውን በመሪር ልቅሶ አንስተው፤ ‹መከሩ አለፈ፤ በጋውም ሔደ ነፍሴም አልዳነችም ለመጠጊያ ወደ ታላቁ አምባ ለምን አልሸሸሁም በነፍሴ ይህንነት ለምን ቆለድሁ፤ የጸጋንም መንፈስ ለምን ናቅሁ /ችላ አልሁ/ ከሚሉት መኻከል ይሆናሉ፡፡ ፲፪12 CCh 66.1

ወንድሞቼና እህቶቼ እውነትን እሃምናለን ስትሉ የቆያችሁ እያንዳንዳችሁን እጠይቃለ፤ ምግባራችሁ ከሰማይ ከተሰጣችሁ ብርሃን፤መብቶችና ምቹ ጊዜያቶች ጋር የሚስማማ ኑርዋልንኑ ይህ ጥብቅ ጥያቄ ነው፡፡ የጽድቅ ፀሐይ በቤተ ክርስቲያን ላይ ወጥቷል፤ ለማብራትም የቤተ ክርስቲያኒቱ ተግባር ነው፡ ግሥጋሤ ለማድረግ የነፍስ ሁሉ መብት ነው፡፡ ከክርስቶስ ጋር ግንኙነት ያደረጉት በጸጋና በእግዚአብሔር ልጅ እውቀት ለዓቅመ አዳምና ሔዋን ሙሉ እድገት ያገኛሉ፡፡እውነትን እናምናለን የሚሉ ሁሉ ለመማርና ለማድረግ በችሎታቸውና በሞቹ ጊዜያቸው እጅግ የጠነከሩ ቢሆኑ፤ በክርስቶሰ ጠንካሮች ይሆኑ ነበር፡፡ ሥራቸው ምንም ይሁን ገበሬዎች ሜካኒክ፤ አስተማሮች ወይም ቄሶች ቢሆኑ ለእግዚአብሔር ፈጽመው ራሳቸውን ቀድሰው የሰጡ ብሆን ኑሮ ለሰማያዊ ጌታ ችሎት ያላቸው ሰራተኞች ይሆኑ ነበር፡፡13 CCh 66.2