የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡

32/126

እግዚአብሔር የመንፈስ ቅዱስን ሥጦታ ሊሰጥ ይፈልጋል፡፡

ሰዎቻችን በሚኖሩበተ በማኀበር ውስጥ ልምምድ ያላቸው ሰራተኞች የተለየ ጥረት ሊያደርጉ ጌታ እንዲሠራ መንገድ እንዲከፍቱለት በተቻላቸው ኃይል ሁሉ ይሰሩ ዘንድ በዚያ ጣቢያ ባሉት ምዕመናን ላይ እጅግ የጠበቀ ግዳጅነት ያርፍባቸዋል፡፡ ልባቸውን በጸሎት መመርመርና ከእግዚአብሔርና ከወንድሞቻቸው ጋር ተባብረው እንዳይሠሩ የሚከለከላቸውን ኃጢአት ሁሉ በማስወገድ የንጉሡን አውራ ጐዳና ማጥዳት አለባቸው፡፡ CCh 63.5

በሌሊቱ ራእዮች በእግዚአብሔር ሕዝብ መኻከል ታላቅ የመታስ (የሪፎርመቶሪ) እንቅስቃሴ ምሥሎች በቶ አለፉ፡፡ ብዙዎች እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበር፡፡ በሽተኞች ተፈወሱ ሌሎችም ተዓምራተ ተደረጉ፡፡ ከጴንጤቆስጤ ቀን በፊት እንደ ተገለጸው የጸሎት መንፈስ ታየ በብዙ መቶና በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ቤተሰቦችን እየጐበኙ በፊታቸው የእግዚአብሔርን ቃል ሲገልጡ ታዩ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ልቦች ተረዱ ዓይነተኛ የሆነ መመለስ የተገለጸ ሆነ፡፡ በሁሉ በኩል ለእውነት አዋጅ በሮች ወለል ብለው ተከፈቱ፡፡ ዓለም በሰማያዊ አነቃቂነት የበራ መሰለ፡፡ እውነተኞችና ትሁታን የሆኑ ያምላክ ሰዎች ታላ በረከቶች ተቀበሉ፡፡ የምሥጋናና የውዳሴ ድምፆች ሰማሁ፤ በ ፲፰፻፵፬ ዓ.ም.እ.ኤ.አ. እንደ ታየው ሪፎርሜሺን (መታደስ) የሆነ መሰለ፡፡ ፮6 CCh 64.1

እግዚአብሔር ሕዝቡን በፍቅሩ እንደና እያጠመቃቸው ነው፤ በመንፈሱ ሥጦታ ሊያለመልማቸው (ሊያበለጽጋቸው) ይፈልጋል፡፡ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ መንፈስ ቅዱስ የጐደላት መሆን አያስፈልግም፡፡ ከክርስቶሰ ዕርገት በኋላ መንፈስ ቅዱስ በሚጠባበቁት በሚጸልዩ አማኞች ደቀ መዛሙርት ላይ ወደ ልብ ሁሉ በደረሰው ምላትና ኃይል ወረደባቸው ምላትና ኃይል ወረደባቸው፡፡ ወደፊትም ምድረዋ በእግዚአብሔር ክብር ልትበራ ነው፡፡ በእውነት አማካይነት ከተቀደሱት የተቀደሰው አርአያነት /ንቃት/ ለዓለም ሊገለጽ ነው፡፡ ምድርም በጸጋ አካባቢነት ልትከበብ ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ ያምላክን ነገሮች ወስዶ ለሰዎችም በማሳየት በሰብአዊ ልቦች ይሠራል፡፡ ፯7 CCh 64.2

ጌታ በርሱ በእውነት ለሚያምኑ ሁሉ ታላቅ ሥራ ያደርግ ዘንድ ፈቃደኛ ነው፡፡ ፈቃደኞች ወንጌላውያን የቤተ ክርስቲያን አባሎች ሊያደርጉ የሚቻላቸውን ሥራ ይሰሩ ዘንድ ቡነቁ በኃላፊነታቸውም በሚያደርጉት ተጋድሎ እንደሚቻላቸው ቢያዩ ብዙዎች በክርስቶስ ሰንደቅ ዓላማ በታች ይቆሙ ዘንድ የሰይጣንን ረድፎች ሲተው እናይ ነበር፡፡ ሰዎቻችን በነዚህ ጥቂቶች የምክር ቃላት (ዮሐንስ ፲፭፡፰)፤ ውስጥ የተሰጠውን ብርሃን ቢሠሩበት ያምላክን ደህንነት በእርግጥ እናይ ነበር፡፡ ግሩም የሆኑት መነቃቂያዎች (ሪቫይቫል) ይከተላሉ ኃጢአተኞች ይመለሳሉ ብዙዎችም ነፍሳት ወደ ቤተ ክርስቲያን ይጭመራሉ፡፡ ከክርስቶስ ጋር ልባችንን ስናስተባብር፤ ሕይወታችንን ከሥራው ጋር ስናስማ በጴንጢቆስጤ ቀን በደቀ መዛሙርት ላይ የወረደው መንፈስ ቅዱስ በኛም ላይ ይወርዳል፡፡ ፰8 CCh 64.3