የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡
ዓይነተኛ የሆነ የኃይማኖት ገለጻ፡፡
ለጌታ በትጋትና ከልብ ባልሆነው አኳሆን የምናደርገው አገልግሎት ለኃይማኖት ስም ሐሰትን ይላክክበታል፡፡ ከልብና በይነተኛ ሥራ የተገለጸው ክርስቲያንነት ብቻ ሕግን በመተላለፍና በኃጢአት በሞቱት ልብ ውስጥ ይሳተፍላቸዋል፡፡ የሚጸልዩ፤ ትሁታን የሚያምኑ ክርስቲያኖች ሰዎችን ሁሉ የሚፈትነው የሚያድነውን እውነት ያስታውቁ ዘንድ ታላቅ ምኞታቸው መሆኑን በሥራቸው የሚያሳዩ ለጌታ የበለጸገ የነፍሳት መከር ይሰበስባሉ፡፡ CCh 60.2
እንዲህ የዛለና የደከመ ለመሆኑ ለቤተ ክርስቲያኖቻችን ኃይማኖት ምንም ምክንያት የለም፡፡ «እላንት በተስፋ የታሠራችሁ ወደ ጽኑ አምባ ተመለሱ» ዘካርያስ ፱፡፲፪፡፡ በክርስቶስ ኃይል አለልን፤ እርሱ በአብ ፊት አማላጃችን ነው፡፡ ለሕዝቡ ፈቃዱን ይናገር ዘንድ መልእክተኞቹን ወደ ግዛቱ ክፍል ሁሉ ይልካል፡፡ በቤተ ክርስቲያኒቱ መኻከል ይሔዳል፡፡ ተከታዮቹን ለመቀደስ ከፍ ሊያደርግና ሊያስከብር ይፈልጎል፡፡ በውነቱ በርሱ የሚያምኑ አርአያቸው በዓለም ውስጥ የሕይወት ጣዕም ይሆናል፡፡ እርሱ ክዋክብትን በቀኝ እጁ ይይዛል፤ በነዚህም አማካይነት ለዓለም ብርሃኑ እንዲበራ ለማድረግ ሐሳቡ ነው፡፡ እንደዚሁም በላይ ባለችው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከፍ ባለው አገልግሎት ሕዝቡን ያዘጋጅ ዘንድ ይፈልጋል፡፡ እንድናደርግ ታላቅ ሥራ ሰጥቶናል፡፡ በቀናና በቁርጥ ሐሳብ እንድናደርገው፤ እውነት ያደረገልንንም በሕይወታችን እናሳይ፡፡ CCh 60.3
ልዩ ልዩ ወንጌላዊ ተግባሮችን አሁን ካሉበት አቋም ለማድረስ ራስን መካድ፤ ራስን መሠዋት ፣ የማይበገር ኃይል ፤ ብዙም ጸሎት አስፈልጎናል (ፈጅቶብናል) በዚህ መልእክት ጊዜ የነበሩ መሪዎች በደረሰባቸው ሁኔታ ይህን ያህል ታላቅ የሆነ ራስን መካድና ትጋት ያሳዩትን የገጠማቸውንም አስቸጋሪና ምቹነት የሌለው ሥራ መሥራት ጊዜውም ስለ ተለወጠ ለእግዚአብሔር ጉዳይ ብዙ ገንዘብ /መረዳጃ/ አሁን ስላለ መልእክቱ ሲጀመር ብዙዎች ይጋጠሙት ዘንድ እንደ ተጠሩት በእንዲህ ያለ ፈታኝ ሁኔታ ውስጥ ራሳቸውን ማኖር የማያስፈልጋቸው እንደሆነ እየሰማቸው አንዳንዶች አሁን በሥራ ደረጃ ላይ ያሉ ዓቅመቢሶች በመሆን የሚደሰቱ መሆናቸው የሚሠራ ነው፡፡ CCh 60.4
ዳሩ ግን በመጀመሪያ እንደነበረው ያው ትጋትና ራስን መካድ ባሁኑ የሥራ ደረጃ ውስጥ ቡገለጽ ኑሮ፤አሁን ከሚፈጸመው መቶ ጊዜያት በልጦ ባየነው ነበር፡፡፳20 CCh 61.1
ኃይማኖታችን ከፍ ያለ ነው፡፡ ሰንበት ጠባቂ አድቬንቲስቶች በመሆናችን የእግዚአብሔር ትእዛዛት ሁሉ የምንተዘዝና ስለሚመጣው አዳኛችን የምንጠባበቅ መሆናችንን እንናገራለን፡፡ እጅግ የተከበረ የማስጠንቀቂያ መልእክት ለጥቂቶቹ የአምላክ ታማኞች ሰዎች አደራ ተሰጥቷል፡፡ ስለዚህ ያረፈብንን ታላቁን ኃላፊነት በቃሎቻችንና በምግባራችን ማሳየት አለብን፡፡ በዕለት ኑሮዋችን አብን የምናከብር፤ ከሰማይ ጋር ግንኙነት እንዳደረግንና ከየሱስ ክርስቶስ ጋር አብሮ ወራሾች እንደሆን እርሱም በኃይልና በታላቅ ምሥጋና በተገለጸ ጊዜ እንደርሱ እንደምንሆን፤ ሌሎች ሊያዩ እንዲችሉ ብርሃናችን በግልጽ ሊያበራ ይገባል፡፡ ፳፩21 CCh 61.2