የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡
ምዕራፍ ፭—እግዚአብሔር ላንተ የምታደርገው ሥራ አለው፡፡
የቤተ ክርስቲያናችን አባሎች የሆኑ ወንዶችም ሴቶችም ለሥራ ታጥቀው ከሰባኮችና ከቤተ ክርስቲያን አለቆች ጋር ጥረቶቻቸውን እስኪያስተባብሩ በዚህ ምድር የእግዚአብሔር ሥራ ከቶ ሊፈጸም አይቻልም፡፡ ፩1 CCh 55.1
«ወደ ዓለም ሁሉ ሒዱ ወንጌልንም ስበኩ ለፍጥረት ሁሉ» ያለውን ቃላት (ማርቆስ ፲፯፡ ፲፭) ለክርስቶስ ተከታዮች ለእያንዳንዳቸው የተነገሩት ናቸው፡፡ ለክርስቶስ ሕይወት የታዘዙ ሁሉ ለባልንጀሮቻቸው ደህንነት ይሰሩ ዘንድ ታዝዘዋል፡፡ ነፍሳትን ለማዳን የተሰማው ያው የነፍስ ናፍቆት በውስጣቸው መገለጽ አለበት፡፡ ሁሉ ያንኑ ሥፍራ ሊመሉበት አይችሉም ፤ ነገር ግን ለሁሉ ሥፍራና ሥራ አለ፡፡ ያምላክ በረከቶች የተሰጣቸው ሁሉ በዓይነተኛ አገልግሎት ብድር መመለስ አለባቸው ስጦታውን ሁሉ ለመንግሥቱ ማስፈሪያ መጠቀም አለብን፡፡ ፪2 CCh 55.2
ስብከት ለነፍሳት ደህንነት የሚሠራው ትንሹ የሥራ ክፍል ነው፡፡ የእግዚአብሔር መንፈስ ስለ እውነት ኃጢአተኞችን ያስረዳቸዋል ፤ በቤተ ክርስቲያኒቱም ክንዶች ላይ ያኖራቸዋል፡፡ ሰባኮን ፋንታቸውን ይሰሩ ይሆናል ግን ቤተ ክርስቲያኒቱ ልታደርግ የሚገባትን ሥራ ሊሠሩ ከቶ አይችሉም፡፡ በኃይማኖትና በልምምድ ወጣቶች የሆኑትን ቤተክርስቲያኒቱ ትጠነቀቅላቸው ዘንድ እግዚአብሔር ይፈልጋል ፤ ወደ እነሱም እንድትሔድ ይፈልጋል ከነሱ ጋር ለማሾክሾክ ሐሳብ አይደለም ፤ ዳሩ ግን ለመጸለይ ፤” የወርቅ ቱፋህ በብር ፆሕል ላይ እንዲያምር» እንዲሁ ቃሎቹን እንድትነግራቸው ነው፡፡ ፫3 CCh 55.3
እግዚአብሔር በምድር ብርሃን ሆና እንድትቆም ጥንታዊቱ እስራኤልን እንደ ጠራት እንዲሁ በዚህ ቀን ያለችውን ቤተክርስቲያኑን ጠርቷል፡፡ በኃያሉ የእውነት ሰይፍ ማለት በመጀመሪያው ፤ በሁለተኛውና በሦስተኛው መላእክት መልእክቶች ወደ ተቀደሰው የራሱ አቅራቢያነት ያመጣቸው ዘንድ ከቤተ ክርስቲያናትና ከዓለም ለይቶአቸዋል፡፡ የሕጉ ማከማቻዎች (ማጠራቀሚያዎች) አድርጎአቸዋል፤ ለዚህም ጊዜ የሆነውንም ታላቁን እውነት ሰጥቶአቸዋል፡፡ ለጥንታዊት እስራኤል እንደ ተሰጣት የተቀደሱት ዓላማዎች ይህም እውነት ለዓለም የሚነገር የተቀደሰ እምነት ነው፡፡ CCh 55.4
የዮሐንስ ራእይ ምዕራፍ ፲፬ ሦስቱ መላእክት የእግዚአብሔርን መልእክቶች ብርሃን ተቀብለው በምድር ርዝመትና ስፋት ውስጥ ማስጠንቀቂያውን ያበስሩ ዘንድ ወኪሎቹ ሆነው በሚወጡት ሕዝብ ይመሰላሉ፡፡ ክርስቶስ «ለተከታዮቹ «እላንት የዓለም ብርሃን ናችሁ” ሲል ይናገራል፡፡ ማቴ. ፭፡፲፬ የሱስን ለሚቀበለ ነፍስ ሁሉ የቀራንዮ መስቀል «እነሆ የነፍስ ቤዛ ወደ ዓለም ሁሉ ሒዱ ወንጌልንም ስበኩ ለፍጥረት ሁሉ» ሲል ይናገራል፡፡ ማርቆስ ፲፯፡ ፲፭፡፡ ማንኛውም ነገር ይህን ሥራ ይከ ለክል ዘንድ አይፈቀድለትም፡፡ ለጊዜው የሚሆን ከሁሉም ጠቃሚ ሥራ ነው፡፡ እንደ ዘልዓለማዊነት የተስፋፋ ነው፡፡ ባልደረገው መሥዋዕት የሱስ ለሰዎች ነፍሳት የገለጸው ፍቅር ተከታዮቹን ሁሉ ያነቃቃል፡፡ ፬4 CCh 55.5
ክርስቶስ የተገዛለትን ሰብዓዊ ፍጥረት ሁሉ በታላቅ ደስታ ይቀበለዋል፡፡ ሥጋ ስለ ለበሰው የፍቅሩ ምሥጢሮች ለዓለም እንዲናገር ሰውን ከአምላክ ጋር ያስተባብረዋል፡፡ ስለርሱ ተነጋገር ጸልይ ፤ ዘምርም ዓለምንም በእውነቱ መልእክት ሙላው ወዲያ ማዶ ወዳሉትም አገሮች መገስገስህንም ቀጥል፡፡ ፭5 CCh 56.1
እውነተኞች የክርስቶስ ተከታዮች ለርሱ ይመሰክራሉ፡፡ ሁላችሁ ንቁዎች ወንጌላዊያን ብትሆኑ ኑሮ ለዚህ ጊዜ የሚሆን መልእክት ለሕዝብ ፤ ለወገን ፤ ለቋንቋም በሁሉ አገሮች ውስጥ በፍጥነት በታወጀ ነበር፡፡ ፮6 CCh 56.2
ወደ አምላክከተማ ለመግባት የሚፈልጉ ሁሉ በምድራዊ አኗኗራቸው ክርስቶስን በምግባራቸው መግለጽ አለባቸው፡፡ የክርስቶስ መልእክተኞች፤ ምስክሮቹም የሚያደርጋቸው ይኸው ነው፡፡ ኃጢአተኞችን የዓለምን ኃጢአት ወደሚያስወግደው የእግዚአብሔር በግ እያመለከቱ በክፉ ልምዶች ሁሉ ላይ ግልጽ ቁርጠኛ የሆነ ምስክርነት ማቅረብ አለባቸው፡፡ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ እርሱ ለሚቀበሉት ሁሉ ኃይል ይሰጣል፡፡ ወደ እግዚአብሔረ ከተማ ልንገባ የምንችልበት መንገድ ሁለተኛ ልደት ብቻ ነው፡፡ ጠባብ ነው፤ የምንገባበትም ደጅ የጨነቀ ነው፤ ግን በርሱ ላይ ወንዶችንም ሴቶችንም ልጆችንም መምራት አለብን፤ እንዲድኑም አዲስ ልብና አዲስ መንፈስ ሊኖራቸው እንደሚገባ እነሱን ማስተማር ነው፡፡ ያረጁ የተወረሱት ባሕርያት ሊሸነፉ ይገባል፡፡ የተፈጥሮው የነፍስ ምኞት ሊለወጥ ይገባል፡፡ ማታለል ፤ ውሸትም ክፉ ንግግርም ሁሉ ሊወገዱ ይገባል፡፡ ወንዶችም ሴቶችም ክርስቶስን እንዲመስሉ የሚያደርጋቸው አደስ ሕይወት ሊኖሩበት አለባቸው፡፡ ፯7 CCh 56.3
ወንድሞቼና እህቶቼ የሚይዛችሁን ወጥመድ ልትሰብሩት ትፈልጋላችሁን? ከዚህ የሞት ድንዛዜ (ስልምታ) ከሚመስለው ስንፍና ልትነቁ ትፈልጋላችሁን? የምትወዱት ፤ የማትወዱትም ሆኖ ቢሰማችሁም ወደ ሥራ ሒዱ፡፡ ነፍሳትን ወደ የሱስና እውነትን ወደ ማወቅ ታመጧቸው ዘንድ የግል ጥረት አድርጉ፡፡ በእንዲህ ያለ ሥራ ንቃትና ብርታት ታገኛላችሁ ፤ ያነቃቃል ፤ ያጠነክራልም፡፡ በበለጠው ክንውን አግኝታችሁ ለራሳችሁ ደህንነት ለመሥራት ትችሉ ዘንድ በልምምድ መንፈሳዊ ኃይላችሁ የበለጠውን የጠነከረ ይሆናል፡፡ በስም የክርስቶስ ነን በሚሉ በብዙዎች ላይ የሞት ድንጋጤ አርፎባቸዋል፡፡ ታነቋቋቸው ዘንድ ጥረት ሁሉ አድርጉ፡፡ አስጠንቅቋቸው ፤ ለምኑዋቸው፤ ምከሩዋቸውም፡፡ እንደ በረዶ የቀዘቀዘውን ጠባያቸውን የሚያቀልጠው የእገዚአብሔር ፍቅር እንዲያግለውና እንዲያለሰልሰው ጸልዩ፡፡ ለመስማት ባይፈቅዱም ሥራችሁ የሚጠፋ አይደለም፡፡ ሌሎችን ለመባረክ ባደረጋችሁ ጥረት ነፍሳችሁ ይባረካል፡፡ ፰8 CCh 56.4
ያልተማሩ (መሐይሞች) ስለሆኑ ማንኛውም በጌታ ሥራ ተካፋዮች ሊሆኑ እንደማይችሉ አይሰማችሁ፡፡ ለእግዚአብሔር የምታደርጉት ሥራ አለላችሁ፡፡ ለሰው ሁሉ ሥራውን ሰጥቶታል፡፡ ለራሳችሁ ቅዱሣት መጻሕፍትን ልትመረምሩ ትችላላችሁ፡፡ «ቃልህ ሲከሠት ደስ ይለኛል፡፡ የዋሃንንም አዋቆች ያደርጋል»፡፡ መዝሙር ፻፲፱፡፻፴ ፡፡ ለሥራው ልትጸልዩ ትችላላችሁ፡፡ በኃይማኖት ከልብ የተጸለየው ጸሎት በሰማይ ይሰማል፡፡ እንደ ችሎታችሁም መጠን መሥራት አለባችሁ፡፡ ፱9 CCh 56.5
ሰብዓዊ ፍጥረቶች ምን እንደሚሆኑና ሊጠፉ ዝግጁዎች ለሆኑት ነፍሳት መዳኛ በነሱ አርአያነት (አነቃቂነት) ምን እንደሚፈጽሙ ለዓለም ይገልጹ ዘንድ ሰማያዊ አስተዋዮች ከሰብዓዊ መሣሪያዎች (ሰራተኞች) ጋር አብረው ለመሥራት በመጠባበቅ ላይ ናቸው፡፡ CCh 57.1
በበረሃ ዳርቻ ላይ እንደ ተበታተኑት ፍራሾች በኃጢአታቸው ለሚጠፉት በምድሮች ሁሉ ተበታትነው ላሉት ብዙ ሺህ ሰዎች በትእግሥትና በጽናት እንሰራ ዘንድ ክርስቶስ ይጠራናል፡፡ በክርስቶስ ክብር ተካፋዮች የሚሆኑ ደካሞችን የተጐሣቆሉትንና ተስፋቢሶች የሆኑትን እየረዱ በአገልግሎቱ ደግሞ ተካፋዮች መሆን አለባቸው፡፡ ፲10 CCh 57.2
አማኝ ሁሉ ከቤተ ክርስቲያኒቱ ጋር ባለው ነክነት በሙሉ ልብ መሆን አለበት፡፡ ልማትዋ የመጀመሪያው ዓላማው መሆን አለበት ፤ ለራሱም ምርጫ ጠቃሚ በመሆኑ ከቤተ ክርስቲያኒቱ ጋር ግንኙነት ያደርግ ዘንድ በተቀደሰው ግዳጅነት ካልተሰማው ፤ ያለርሱ እጅግ በተሻለው አኳሆን ልትሰራ ትችላለች፡፡ አንዳች ነገር ለእግዚአብሔር ለማድረግ በሁሉ ኃይል ውስጥ አለ፡፡ በማያስፈልገው ቅምጥልና (መሽሞንሞን) ብዙ ገንዘብ የሚያባክኑ አሉ፤ አምሮታቸውንም ያስደስታሉ ቤተ ክርስቲያኒቱን ለመደገፍ ገንዘብ መስጠት ትልቅ ግብር እንደሆነ ይሰማቸዋል፡፡ ከመብትዋ ጥቅምን ሁሉ ለመቀበለ ይፈቅዳሉ፤ ግን ሌሎች የሂሳቡን ካርኔ እንዲከፍሉ ሊተውባቸው ይመርጣሉ፡፡ ፲፩11 CCh 57.3
የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን በጦር ሠራዊት ልትመሰል የሚገባት ናት፡፡ የወታደር ሁሉ ሕይወት የትጋት፤ የተጋድሎና የቆራጥነት ሕይወት ነው፡፡ በየአቅጣጫው በማያንቀላፋና ከቶ ሥራውን በማይለቅ በጨለማ ኃይላት አለቃ የሚመሩ ንቁዎች የሆኑ ጠላቶች አሉ፡፡ ክርስቲያኑ መትጋቱን ሲተው፤ ይህ ኃይለኛ ባለጋራ ድንገተኛና ብርቱ የሆነ አደጋውን ይጥልበታል፡፡ የቤተ ክርስቲያን አባሎች ቀልጣፎችና ትጉዎች ካልሆኑ በተንኰሎቹ ይሸነፋሉ፡፡ CCh 57.4
ተግባራቸውን እንዲፈጽሙ ታዝዘው ሳሉ በጦር ሠራዊት ውስጥ ያሉት ገሚሶቹ ወታደሮች ቢማግጡና ቢያንቀላፉ እንዴት ይሆን ነበር? ውጤቱ መሸነፍ መማረክ ወይም መሞት ነው፡፡ ማንኛቹውም ከጠላት እጅ ያመልጥ ይሆን ሽልማትስ የሚባቸው እንደሆነ ይታሰቡ ይሆን? የለም ፤ በፍጥነት የሞት ፈርድ ይፈረድባቸዋል፡፡ እንደዚሁም የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን የማትጠነቀቅ ወይም ያልታመነች ስትሆን ከዚህ የባሰ ውጤት ያገኛታል፡፡ የሚያንቀላፋ የክርስቲያን የክርስቲያናዊ ወታደሮች ጦር ሠራዊት ከዚህ የባሰ ምን የየሚያስፈራ ሊደርስበት ይችላል በጨለማ አለቃ መሪነት (አገታት) በሆነው ዓለም ላይ ምን ግስጋሤ ሉደረግ ይቻላል? ስለ ተጋድሎው ውጤት ምንም ከቁም ነገር ሳያደርጉና ኃላፊነት እንዳለባቸው ሳይሰማቸው ፤ በጦርነቱ ቀን ችላ ብለው ወደ ኋላ የሚያፈገፍጉ እርምጃቸውን መለወጥ ይሻላቸዋል፤ አለበለዚያ የያዙትን ረድፍ ወዲያው መተው ነው፡፡ ፲፪12 CCh 57.5