የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡
ሰንበትን በመጠበቅ የሚገኙ በረከቶች፡፡
ሰማይ ሁሉ ሰንበትን የአራተኛው ትእዛዝ ፍላጎት የሚያውቁትንና (የሚገነዘቡትንና) ሰንበትን የሚጠብቁትን ሲመለከትና ሲጠባበቅ ታየኝ፡፡ መላእክት ይህን መለኮታዊ ድንጋጌ ማሰባቸውንና ከፍ ባለው አክብሮት መጠበቃቸውን ምልክት ሲያደርጉ ነበር፡፡ አጥብቀው ከልብ በመጸለይ በልባቸው እግዚአብሔርን አምላካቸውን የተቀደሱና በተቻላቸው መጠን ሰንበትን በመጠበቅ ረገድ የተቀደሱትን ሰዓታት ለማሻሻል የፈለጉትን፤ መላእክትን እነዚህን በብርሃንና በጤንነት በተለይ ባረኩዋቸ፤ የተለየም ኃይል ተሰጣቸው፡፡ ፲፱19 CCh 53.3
ከሰማይ አምላክ ፍላጎቶች ጋር አጥብቆ መስማማት፤ መንፈሳዊም ሆነ ሥጋዊ በረከቶችን ያመጣል፡፡ ፳20 CCh 54.1
‹‹ይህን የሚያደርግ ሰው የተመሰገነ ነው፡፡ የሰውም ልጅ ይሀነን የሚይዝ፡፡ ሰንበትን የሚጠብቅ እንዳያረክሰው እጁንም የሚጠብቅ ክፉን ነገር እንዳያደርግ››፡፡ ‹‹የመፃተኛ ልጆችም ከእግዚአብሔር ጋራ አንድ የሆኑ ያመልኩት ዘንድ የእግዚአብሔርንም ስም ይወዱ ዘንድ ባሮቹ ለመሆን፡፡ ሰንበትን የሚጠብቅ ሁሉ እንዳያረክሰው በቃል ኪዳኔም የሚያዝ፡፡ ወደ ተቀደሰው ተራራዬ አመጣቸዋለሁ፡፡ በጸሎቴም ቤት ደስ አሰኛቸዋለሁ፡፡ የሚቃጠለውን ቁርባናቸውን፣ የሚታረደውንም መሥዋዕታቸውን እቀበላቸዋለሁ፡፡ በመሠዋያዬ ላይ ቤቴ የጸሎት ቤት ይባላልና ለአሕዛብ ሁሉ››፡፡ ኢሳያ ፶፮፡፪፡፮፡፯፡፡ ፳፩ 21 CCh 54.2
ሰማያትና ምድር እስካሉ ጊዜ ድረስ፤ ሰንበት የፈጣሪ ኃይል ምልክት ሆኖ ይቀጥላል፡፡ ዔድን እንደገና በምድር ላይ ሲያብብ የተቀደሰው ያምላክ ዕረፍት ቀን ከፀሐይ በታች ባለው ሁሉ ይከበራል፡፡ ‹‹በሰንበትና በሰንበትም›› የተከበረችው ያዲሰሲቱ ምድር ነዋሪዎ፤ ‹‹ይመጣል በፊቴ ይሰግድ ዘንድ ይላል እግዚአብሔር››፡፡፳፪22 CCh 54.3