የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡
«በቅዳሜ መልካም መሥራት ይገባል»፡፡
በቤትና በቤተክርስቲያን የአገልግሎት መንፈስ መገለጽ አለበት፡፡ ሥጋዊ ሥራችንን እንሠራ ዘንድ ስድስት ቀን የሰጠን ሰባተኛውን ቀን ባረከው ፤ ቀደሰውም ለራሱም ለብቻ ለየው፡፡ በዚህ ቀን እርሱ ለአገለግሎቱ ራሳቸውን ቀድሰው የሚሰጡትን ሁሉ በተለየ አኳሆን ይባርካቸዋል፡፡ CCh 50.1
ሰማይ ሁሉ ሰንበትን ይጠብቃል ፤ ግን በቸልተኝነት ምንም በማያደርጉበት ጐዳና አይደለም፡፡ በዚህ ቀን የነፍስ ኃይል ሁሉ መንቃት አለበት ፤ ከእግዚአብሔርና ከመድኃኒታችን ከክርስቶስ ጋር የምንገናኝ አይደለንምን? በኃይማኖት ልናየው እንችላለን፡፡ እርሱ ነፈስን ሁሉ ለማለምለምና ለመባረክ ይናፍቃል፡፡ ፲፩11 CCh 50.2
መለኮታዊ ምሕረቱ ለበሽተኞችና ለሕሙማን እንድንጠነቀቅላቸው አመልክቶናል፤ እነሱን ለማጽናናት የሚያስፈልግ ሥራ የሚያሻ ሥራ ነው፤ ሰንበትንም ማፍረስ አይደለም፡፡ ነገር ግን የማያስፈልግ ሥራ ሁሉ ሊወገድ ይገባል፡፡ ብዙዎች በመዘጋጃ ቀን ሊደረጉ ይገቡ የነበሩትን ትናንሽ ነገሮች ሰንበት እስኪጀመር ባለመጠንቀቅ ያቆዩታል፡፡ ይህ ሊሆን አይገባም፡፡ የተቀደሰው ጊዜ እስኪጀመር ችላ የተባለው ማናቸውም ሥራ ሰንበት እስኪያልፍ ሳይሰራ መቆየት አለበት፡፡ ፲፪12 CCh 50.3
በሰንበት ምግብን መስራት ሊወገድ የሚገባ ሲሆን ቀዝቃዛ ምግብ መብላት የሚያሻ አይደለም፡፡ ምግቡ ከዚያን ቀን በፊት የተዘጋጀው በብርድ ጊዜ ይሞቅ ምግቡ ቀለል ያለም ቢሆን ጣዕም ያለውና የሚያስጐመጅ ይሁን፡፡ እንደ ብርቅ የሚመለከቱትን አንዳች ነገር ቤተሰቡ ሁሉ ቀን የማያገኘውን አንዳች ነገር አሰናዱ፡፡ CCh 50.4
ለታዛዡ ተስፋ የተሰጠውን በረከት ብንፈልግ ሰንበትን ይበልጥ አጥብቀን መጠበቅ ይገባናል፡፡ በዚህ ቀን አለመጓዝ የሚቻል ሲሆን ፤ ብዙ ጊዜ በዚሁ ቀን የምንጓዝ ስለ መሆናችን ያስፈራኛል፡፡ ጌታ ስለ ሰንበት አጠባበቅ ከሰጠው ብርሃን ጋር በመስማማት በዚህ ቀን በጀልባዎች ወይም በመኪናዎች በመጓዝ ረገድ ይበለጡን መጠንቀቅ ይገባናል፡፡ በዚህ ጉደይ በልጆቻችንና በወጣቶቻችን ፊት የቀና ምሳሌ ማሳየት አለብን፡፡ እርዳታችንን የሚፈልጉብንን ቤተ ክርስቲያናት ለመጐብኘት እግዚአብሔር እንዲሰሙ የሚፈልጋቸውን መልእክት ለመስጠት በሰንበት ቀን እንጓዝ ዘንድ የሚያስፈልገን ይሆናል፤ ግን በተቻለን ሁሉ በሌላ ጊዜ ቲኬታችንን ማግኘትና አስፈላጊውን ዝግጅት፤ (መሰናዶ) ሁሉ ማድረግ አለብን፡፡ ጉዞዋችንን ስንጀምረ ወደምንሔድበት ሥፍራ በሰንበት ቀን እንዳንደርስ ለማቀድ በተቻለን ሁሉ ጥረት ማድረግ አለብን፡፡ CCh 50.5
በሰንበት ዕለት ለመጓዝ ስንገደድ ሐሳባችንን ወደ ዓለማዊ ነገሮች የሚስቡንን ጓደኝነታቸውን ለማስወገድ መሞከር አለብን፡፡ ሐሳባችን በአምላክ ላይ የጸና እንዲሆን መጠበቅና ከርሱ ጋር መነጋገር አለብን፡፡ ምቹ ጊዜ ሲኖረን ፤ ስለ እውነቱ ለሌሎች መናገር አለብን፡፡ ሕመምተኞችን መርዳትና የተቸገሩትን እንረዳ ዘንድ ሁልጊዜ ዝግጁዎች መሆን ይኖርብናል፡፡ በእንዲህ ያለ ጉዳይ የሰጠንን እውቀትና ጥበብ እንድንጠቀምበት እግዚአብሔር ይፈልጋል፡፡ ዳሩ ግን ስለ ሥራ ጉዳዮች መነጋገር ወይም የተለመደውን ዓለማዊ ጭውውት መነጋገር አይገባንም፡፡ በሁሉ ጊዜያት በሁሉም ስፍራዎች ሰንበትን በማክበር ለርሱ ታዛዥነታችንን እንድናስረዳ እግዚአብሔር ይፈልገናል፡፡ ፲፫13 CCh 50.6