የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡

12/126

ስለ እውነተኛ ነቢይ የተረጋገጡ መፈተኛዎች፡፡

ከነዚሁ ዋና ዋናዎቹ አራቱ የመጽሐፍ ቅዱስ መፈተኛዎች ጭምር ጌታ ሥራው በርሱ መሪነት መሆኑን የሚገልጹ ማስረጃዎች ሰጥቷል፡፡ ከነዚሁ መኻከል የሚከተሉት ናቸው፡፡ CCh 30.7

፩፣ መልእክቱ የተሰጠበት ጊዜ፡፡ የእግዚአብሔር ሕዝብ በልዩ ፍላጎት ላይ ናቸው፤ ለሚስስ ኋይት መጀመሪያ የተሰጣት ራእይ እንዳደረገው መልክቱም ፍላጎቱን ለመሙላት ልክ በጊዜ መምጣቱ ነው፡፡ CCh 31.1

፪፣ የመልክቶቹ እውነተኛ ባሕርይ፡፡ ለሚስስ ኋይት በራእይ የተገለጸላት እንፎርሜሽን በውነቱ ጠቃሚነት ያለው ነው፣ እውነተኛ ፍላጎትንም የሚሞላ ነው፡፡ የምስክር ምክሮች በዕለት ሕይወታችን ውስጥ በጠቃሚነት ጎዳና እንዴት የሚገቡ መሆናቸውን እስቲ ተመልከት፡፡ CCh 31.2

፫፣ ከፍ ያለው መንፈሳዊው የመልእክቶቹ ዓላማ (አቋም)፡፡ የልጅነት ወይም ተራ የሆኑትን ጉዳዮች የሚያወሱ አይደለም፤ ግን ትላልቅና ከፍ ያሉትን ዓላማዎች (ሐሳቦች) ነው ንግግራቸውም ከፍ ያለ ነው፡፡ CCh 31.3

፬፣ ራእዮቹ የተሰጡበት አኳኋን፡፡ ከራእዮቹ ብዙዎቹ በዚህ መግቢያ በመጀመሪያዎች ምዕራፎች ውስጥ እንደ ተገለጸው ራእይ ስታይ የሰውነትዋ መለዋወጥ ይከተል ነበር፡፡ ራእይ ስታይ ሚስስ ኋይት ሁኔታዋ ከመጽሐፍ ቅዱስ ነቢያቶች ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ ይህም መፈተኛ ሳይሆን ከሌሎቹ ማስረጃዎች መኻከል ማስረጃ መሆኑ ነው፡፡ CCh 31.4

፭፣ ራእዮቹ የተረጋገጡ ሁኔታዎች ናቸው እንጂ ልበ ወለድ የሆኑ አይደለም፡፡ በራእይ ሚስስ ኋይት አየች፣ ሰማች ተሰማትና ከመላእክትም ምክር (ትምህርት) ተቀበለች፡፡ ራእዮቹ በስሜት ወይም በልበ ወለድነት ሊቆጠሩ አይቻልም፡፡ CCh 31.5

፮፣ ሚስስ ኋይት በአካባቢዋ ባሉት በአርአያቸው አልተመራችም (እንፍሉየንስ አልሆነችም) ላንድ ሰው ‹‹ሰዎች ሐሳቤን የመሩኝ ይመስልሃል፤ በዚህ ሁናቴ ከሆንሁ የእግዚአብሔር ሥራ በእምነት የተሰጠን ለመሆኔ ተገቢ አይደለሁም›› ስትል ጻፈች፡፡ CCh 31.6

፯፣ ሥራዋ በርስዋ ጊዜ አብረዋት በነበሩት ዘንድ የታወቀ ነው፡፡ በቤተክርስቲያን የነበሩ ከሚስስ ኋይት ጋር የኖሩና የሠሩ፣ ደግሞ ብዙዎች ከቤተ ክርስቲያን ውጭ የሆኑ ሚስስ ኋይት በውነቱ ‹‹የጌታ መልአክተኛ›› መሆንዋን አውቀዋል፡፡ እነዚያም በጣም የሚቃረቧት በጥሪዋና በሥራዋ ትልቅ እምነት ነበራቸው፡፡ CCh 31.7

እነዚህ አራቱ የመጽሐፍ ቅዱስ መፈተኛዎችና በመልእክቱና በመልእክተኛው ምሉ እምነት ይኖራቸው ዘንድ ጌታ ለህዝቡ የሰጣቸው ግልጽ የሆኑ ማስረጃዎች ሥራው ከእግዚአብሄር መሆኑንና የማይጠረጠረው እምነት ተገቢው መሆኑን ያረጋግጡልናል፡፡ CCh 31.8

ብዙዎቹ የኢ ጂ ኋይት መጻህፍት ለቤተ ክርስቲያኒቱ የዘወትር ጠቃሚነት ባለው ምክርና ትምህርት የተመሉ ናቸው፡፡ እነዚህ ምሥክሮች በጠቅላላ ባሕርያቸው ቢሆኑም ወይም ለቤተሰቦችና ለሰዎች የግል ምስክሮች ቢሆኑም ዛሬ የሚያገለግሉን ናቸው፡፡ ስለዚሁ ሐሳብ ሚስስ ኋይት እንዲህ ትላለች፡፡ CCh 31.9

ለሰዎች ጉዳዮች በምሥክሮቹ ውስጥ የተሰጠ ማስጠንቀቂያና ምክር በዚሁ አኳሆን በተለይ ላልተመለከተላቸውም ለብዙዎች ሌሎች ሰዎች እንደዚሁ በዚሁ ኃይል የተመለከተላቸው ስለሆነ፤ የግል ምስክሮችን ለቤተ ክርስቲያን ጥቅም አወጣ ዘንድ ተግባሬ እንደሆነ መሰለኝ፡፡ …እነዚህን ምስክሮች በመስጠት ካልሆኑ በስተቀር፣ ስለ ጠቅላላዎቹ አሥጊነትና ስሕተቶች፣ እግዚአብሔርንም ስለ ሚወዱና ትእዛዛቱን ስለሚጠብቁት ሁሉ ስለ ተግባራቸው አስተያየቶቼን የማቀርብበት የተሻለ ጎዳና መኖሩን አላውቅም፡፡ CCh 31.10

ጓድ ወንድምን ለማነወር አንድ ሐሳብ አውጥቶ በማንበብ ምሥክሮችን መጠቀም ስህተት ነው፡፡ አንዱን ወንድም ወይም አንድዋን እህት ነገሮችን እኛ እንደምናይ እንዲያዩ እናደርጋቸው ዘንድ ምሥክሮችን እንደ ክለብ (ክበብ) ከቶ ልንጠቀምባቸው አይገባም፡፡ ሰው ብቻውን ካምላክ ጋር ያደላድል ዘንድ ሊተውለት የተገቡ ነገሮች አሉ፡፡ CCh 32.1

ዛሬ በገዛ ሕይወታችን ውስጥ የሚሳተፉትን መሠረታዊ ፕርንስፕሎች እናገኝ ዘንድ ምሥክሮቹ ሊጠኑ ይገባል፡፡ አንዳንዶቹ መልእክቶች ለተለየ ጊዜ ወይም ሥፍራ ማስጠንቀቂያዎች ወይም ግሣጼዎች ሆነው ተሰጥተዋል፣ ሆኖም የተለገፁት ፕርንስፕሎች በአመለካከታቸው ለሁሉ የሚሆኑና በጠቀሜታቸውም በየጊዜው ላሉት የሚሆኑ ናቸው፡፡ ሰብዓዊ ልብ በዓለም ያው ነው፣ ያንዱ ችግሮች ብዙ ጊዜ የሌላው ችግሮች መሆኑ ነው፡፡ ያንዱን ስህተት ሲዘልፍ እግዚአብሔር ‹‹ብዙዎችን ለማረም›› አስቦ ነው ስትል ሚስስ ኋይት ጻፈች፣ ‹‹ሌሎችም እንዲሁ እንዲመከሩ ያንዳንዶቹን ስህተቶች ይገልጻል››፡፡ CCh 32.2

‹‹በሕይወቷ መጨረሻ ላይ ሚስስ ኋይት ተከታዩን ምክር ሰጠች በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ድምጽ በማስጠንቀቂያና በምክር ዘወትር መጥቶልናል፡፡ … ጊዜና ፈተና የተሰጠውን ምክር አልደመሰሰም፡፡ … መልእክቱ በወጣበት በቀደምት ቀናት ውስጥ የተሰጠው ምክር በነዚህ መጨረሻ ቀናት መከተል ደህና ምክር ሁኖ ሊጠበቅ አለበት››፡፡ CCh 32.3

‹‹የሚከተሉት ምክርች ከብዙዎቹ የኤ ጂ ኋይት መጻሕፍት የተቀዱ ናቸው፤ ማለት ከሶስቱ የምስክር መዝገቦች ከተባሉት ቮሊዩም (ተስትሞኒ ትረዥርስ) ለቤተ ክርስቲያኒቱ ታትመው የወጡ በዓለም ዕውቅ የሆኑ ምሥክሮች፤ ለቤተ ክርስቲያኒቱ እጅግ የሚረዱ የምክር መሥመሮች ሆነው ያመለክታሉ፤ ይኸውም የቤተ ክርስቲያን አባሎች በመጠኑ ባሉበት ሥፍራ መጠነኛ ከሆነው አንድ ቮሊዩም በላይ አትሞ ለማውጣት የማያስችል ይሆናል፡፡ እነዚህን ምክሮች ለመምረጥና ለማደራጀት ሥራው በትልቅ ኮሚቴ ነው የተሰራ፤ ይኸውም የትንቢት መንፈስን ምክሮች በጥንቃቄ ይዞ ለማስፋፋት ኃላፊነት ባለው በዔሌን ጂ ኋይት የትራስቲስ ቦርድ ፈቃድ የሚሰራ ኮሚቴ ነው፡፡ ተመርጠው የወጡት ምክሮች አጠር ያሉና መሠረታዊ ፕርንስፕል ባለው አነጋገር የወጡ ናቸው፣ ብዙዎችም አርዕስቶች አሉባቸው፡፡ CCh 32.4

‹‹በእግዚአብሔር ባምላካችሁ እመኑ ትጸኑማላችሁ በነቢያቱም እመኑ ነገሩም ሁሉ ይሰላላችኋል››፡፡ ዜና መዋዕል ካልዕ ፳፣፳፡፡ CCh 32.5

የዔሌን ጂ ኋይት መጻሕፍት አሳታሚ
ዋሽንግቶን ዲ ሲ ትራስቲስ ቦርድ፡፡
ሐምሌ ፳፪ ቀን ፲፱፻፶፯ ዓ.ም እ.ኤ.አ፡፡
CCh 32.6