መልዕክት ለወጣቶች

255/511

ክፍል 7—ጤናና ብቃት

አእምሮና ነፍስ የሚገለጹት በአካል ስለሆነ የአእምሮና የመንፈስ ጥንካሬ በከፍተኛ ደረጃ በአካል ብርታትና ሥራ ላይ ይደገፋሉ፡፡ ማንኛውም የአካል ጤንነትን የሚጨምር ነገር ጠንካራ አእምሮና ሚዛናዊ የሆነ ባሕርይን እድገት ይጨምራል፡፡ ያለ ጤንነት ማንም ሰው በትክክል ማስተዋል ወይም ለራሱ፣ ለመሰሎቹና ለፈጣሪው ያሉትን ግዴታዎች አሟልቶ መፈጸም አይችልም፡፡ ስለዚህ ጤንነት ልክ እንደ ባሕርይ በጥንቃቄ መጠበቅ አለበት፡፡ የአካል ክፍሎቻችንን አሰራርና ንጽህና አጠባበቅ ማወቅ የትምህርት ጥራታችን ሁሉ መሠረት መሆን አለበት፡፡ Education, P.195. MYPAmh 151.1