መልዕክት ለወጣቶች

242/511

መጽሐፍት ሻጭነት

ጌታ ወጣቶቻችንን እውነቱ ባልተሰማባቸው ቦታዎች የቤት ለቤት ሥራ በመሥራት እንደ መጽሐፍት ሻጮችና ወንጌላውያን ሆነው እንዲያገለግሉ እየጠራቸው ነው፡፡ ለወጣቶቻችን፡- «እናንተ የራሳችሁ አይደላችሁም፣ በዋጋ ተገዝታችኋል፣ ስለዚህ በአካላችሁና በመንፈሳችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ፣ እነርሱም የእርሱ የሆኑ ናቸው፡፡” እያለ ይናገራቸዋል፡፡ ሥራውን ለመሥራት በእግዚአብሔር መመሪያ ሥር የሚሄዱ በአስደናቂ ሁኔታ ይባረካሉ፡፡ Testimonies for the Church, vol. 8, P. 229. MYPAmh 145.1

ወጣቶች ለአገልግሎት ገጣሚነትን ከሚያገኙባቸው እጅግ ጥሩ መንገዶች አንዱ የመጽሐፍት ሻጭነት መስክ ነው፡፡ የወቅቱን እውነት የያዙ መጽሐፍትን ለመሸጥ ወደ ትላልቅና ትናንሽ ተማዎች ይሂዱ፡፡ በዚህ ሥራ ውስጥ የሕይወት ቃላትን ለመናገር አጋጣሚ ያገኛሉ፡፡ እነርሱ የዘሩአቸው ዘሮች ፍሬ ለማፍራት ይበቅላሉ፡፡ ሰዎችን በመገናኘትና ጽሁፎችን በመስጠት በስብከት አማካይነት የማያገኙትን ልምምድ ያገኛሉ…፡፡ MYPAmh 145.2

ለእውነተኛ አገልግሎት አጋጣሚ የሚሹና ራሳቸውን ሳይቆጥቡ ለእግዚአብሔር የሚሰጡ ሰዎች በመጽሐፍ ሻጭነት ሥራ ውስጥ ስለ ወደፊቱ ዘላለማዊ ሕይወት ብዙ ነገሮችን ለመናገር አጋጣሚ ያገኛሉ፡፡ Gospel Workers, p. 96. MYPAmh 145.3