መልዕክት ለወጣቶች

229/511

በቤት ውስጥ መርዳት

በቤት ውስጥ ራስ ወዳድነት የሌለውን ፍላጎት በማሳየት ልጆችና ወጣቶች የአባቶቻቸውንና የእናቶቻቸውን ኃላፊነት በማቅለል መደሰት ይገባቸዋል፡፡ የእነርሱ ድርሻ የሆኑትን ሸክሞች በደስታ ሲያነሱ ለመታመንና ጠቃሚነትን ለሚያጎላ ኃላፊነት ገጣሚ የሚያደርጋቸውን ሥልጠና እየወሰዱ ናቸው፡፡ በየአመቱ የማያቋርጥ እድገት ማሳየት አለባቸው፡፡ በቀስታ ግን በርግጠኝነት የልጅነት የልምድ ማነስን እያስወገዱ ወደ ሙሉ ሰውነት ልምምድ ማደግ አለባቸው፡፡ በቤት ውስጥ ያሉትን ቀላል ተግባራት በመፈፀም ወንድና ሴት ልጆች ለአካል፣ ለአእምሮና ለመንፈሳዊ ብቃት መሠረት እየጣሉ ናቸው፡፡ MYPAmh 139.6