መልዕክት ለወጣቶች
ራስ ወዳድነት የሌለበት አገልግሎት
በተቻላቸው መጠን ለሌሎች ፍቅር እንዳላቸው የሚገልጽ ተግባራዊ መግለጫ በመስጠት መልካም የሚያደርጉ ሰዎች ሸክማቸውን እንዲሸከሙ በመርዳት የሰብዓዊ ሕይወትን ክፋቶች ፋታ እየሰጡ ብቻ ሳይሆን በአብዛኛው ለራሳቸው ነፍስና አካል ጤንነት አስተዋጽዖ እያደረጉ ነው፡፡ መልካም ማድረግ ሰጪውንም ተቀባዩንም የሚጠቀም ሥራ ነው፡፡ ለሌሎች ባለህ ፍቅር ምክንያት ራስህን ብትረሳ በድክመቶችህ ላይ ድልን ትቀዳጃለህ፡፡ መልካም በማድረግ የምታገኘው እርካታ ጤናማ የሆነ አስተሳሰብን በመመለስ በከፍተኛ ደረጃ ይረዳል፡፡ MYPAmh 138.1
መልካም ነገርን የማድረግ ደስታ አእምሮን ያነሳሳና በሁሉም የአካል ከፍሎች ይሰራጫል፡፡ የለጋስ ሰዎች ፊት በደስታ ሲያበራና የፊታቸው ገጽታ የአእምሮን የግብረገብ ከፍ ማለት ሲገልጽ የራስ ወዳድና ስስታም ሰዎች ፊት ደግሞ ያዘነ፣ ተስፋ የቆረጠና የጠቆረ ነው፡፡ MYPAmh 138.2
በእውነተኛና ከራስ ወዳድነት ነፃ በሆነ ልግስና የተነሳሳ ሰው በዓለም ውስጥ ካለ ፍትወት የተነሳ ከሚመጣው ጥፋት አምልጦ የመለኮታዊ ባሕርይ ተካፋይ ነው፡፡ ራስ ወዳዶችና ስስታሞች ራስ ወዳድነታቸው ማህበራዊ ርህራሄያቸውን እስኪያደርቀው ድረስ በልባቸው ስለያዙት ፊታቸው ንጽህናንና ቅድስናን ሳይሆን የወደቀው ጠላትን ምስል ያንፀባርቃል፡፡ Testimonies for the church, vol.2, p. 534. MYPAmh 138.3