መልዕክት ለወጣቶች

216/511

የተወደዱትን ለኢየሱስ መማረክ

ስለምትወዱአቸው ነፍሳት የሆነ ሥጋት ሊሰማችሁ መቻሉ እውነት ነው፡፡ የእውነትን መዝገብ ልትገልጡላቸው ትሹ ይሆናል፤ ካላችሁ ልባዊ ፍላጎት የተነሣ ስለ ደህንነታችው ልታነቡ ትችላላችሁ፡፡ ነገር ግን ቃላቶቻችሁ ያሳደሩት አሻራ በጣም አነስተኛ ሆኖ ሊታያችሁና ለፀሎቶቻችሁ ግልጽ መልስ ሰይኖር ሲቀር እግዚአብሔር ጥረቶቻችሁን ፍሬ ቢስ እንዲሆኑ እንዳደረገ ሊሰማችሁ ይችላል፡፡ የምትወዱአቸው የተለየ የልብ ድንዳኔ እንዳለባቸውና ለጥረቶቻችሁ ምላሽ እንዳልሰጡ ይሰማችኋል፡፡ ነገር ግን ስህተቱ ከእናንተ ሊሆን እንደሚችል በደንብ አስባችሁ ታውቃላችሁ? በአንዱ እጃችሁ ለመገንባት እያጣራችሁ ያላችሁትን ነገር በሌላኛው እጃችሁ እያፈረሳችሁት እንዳላችሁ አስባችኋልን? MYPAmh 132.4

አንዳንድ ጊዜ የእግዚአብሔር መንፈስ እንዲቆጣጠራችሁ ፈቅዳችኋል፡፡ ሌላ ጊዜ ደግሞ በስራችሁ እምነታችሁን ክዳችኋል፡፡ ለምትወዱአቸው ያላችሁን ጥረታችሁንም አበላሽታችኋል፡፡ ለዚህም ምክንያቱ ለእርሱ ያደረጋችሁት ጥረታችሁ በተግባራችሁ ውጤት አልባ በመሆኑ ነው፡፡ አሳባችሁ፣ በቃላት ያልተገለፀ ቋንቋችሁ፣ የአእምሮአችሁ ፀፀት፣ ክርስቲያናዊ መልካም መዓዛ ማጣት፣ መንፈሳዊነትን ማጣትና የፊታችሁ ገጽታ በእናንተ ላይ መስከረውባችኋል፡፡ MYPAmh 132.5

የትንንሽ ነገሮችን አስፈላጊነት በፍፁም አትናቁ፡፡ ትንንሽ ነገሮች እውነተኛውን የሕይወት መርህ ይሰጣሉ፡፡ በእነዚህ አማካይነት ነፍስ በክርስቶስ አምሳያነት ለመጎልበት ያድጋል፤ ወይንም የክፉ አምሳያነትን ይይዛል፡፡ እግዚአብሔር የአስተሳሰብ፣ የቃላት፣ የአስተያየትና የተግባር ልምምዶቻችንን በዙሪያችን ላሉ ሁሉ ከኢየሱስ ጋር እንደነበርንና ከእርሱ መማራችንን በሚገልጽ መልኩ እንድናሳድጋቸው ይረዳናል፡፡ The youth’s Instructor, March 9,1893. MYPAmh 133.1