መልዕክት ለወጣቶች

213/511

ነፍስን ለማዳን ኃላፊነት

በወጣቶች ላይ ከባድ ኃላፊነቶች ተጥለውባቸዋል፡፡ ብርሃንና እውቀት በበዛበት በዚህ ትውልድ ከሚኖሩ ወጣቶች እግዚአብሔር ብዙ ይጠብቅባቸዋል፡፡ የብዙዎችን አእምሮ እያጨለመ ያለውን ስህተትና ጥንቆላ ለመግፈፍ ሊጠቀምባቸው ይፈልጋል፡፡ እያንዳንዱን ትንንሽ የእውቀትና የልምምድ አይነት በመሰብሰብ ራሳቸውን ማሰልጠን አለባቸው፡፡ እግዚአብሔር ለተሰጡአቸው እድሎች ተጠያቂ ያደርጋቸዋል፡፡ ከፊታቸው ያለው ሥራ ጊዜው በሚጠይቀው ሁኔታ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ለማሰራጨት የእነርሱን ልባዊ ጥረት እየጠበቀ ነው፡፡ MYPAmh 131.1

ወጣቶች አእምሮአቸውንና ልባቸውን ለጌታ አገልግሎት ቢቀድሱ ኖሮ እጅግ ከፍ ወዳለው የብቃትና ጠቃሚነት ደረጃ በደረሱ ነበር፡፡ ጌታ ወጣቶች እንዲደርሱ የሚፈልገው ደረጃ ይህ ነው፡፡ ከዚህ ያነሰ ማድረግ ማለት እግዚአብሔር የሰጠውን መልካም አጋጣሚ በተገቢ ሁኔታ ለመጠቀም ፈቃደኛ አለመሆን ማለት ነው፡፡ ይህ ደግሞ ለሰብዓዊ ዘር በጎነት ለመሥራት ባለመቻል በእግዚአብሔር ላይ እንደማመጽ ይቆጠራል፡፡ MYPAmh 131.2

ውድ ወጣቶች ሆይ፣ የእግዚአብሔር ቃል መሪያችሁ መሆኑንና የጅሆቫን ሕግጋት መጠበቅ ምን ያህል አስፈላጊ መሆኑን ለማሳወቅ ምን እያደረጋችሁ ነው? ሰዎች መዳን የሚችሉት ለእግዚአብሔር ቃል በመታዘዝ ብቻ መሆኑን በቃልና በሕይወት ምሳሌነት እያወጃችሁ ነው ወይ? ማድረግ የምትችሉትን የምታደረጉ ከሆናችሁ ለሌሎች በረከት ትሆናላችሁ፡፡ የችሎታችሁን ያህል በምትሠሩበት ጊዜ የበለጠ መሥራት እንድትችሉ መንገዶችና አጋጣሚዎች ይከፈቱላችኋል፡፡ The Youth’s Instructor, January 1, 1907. MYPAmh 131.3