መልዕክት ለወጣቶች
በእምነት ሥሩ
እናንተ በእግዚአብሔር አንድያ ልጅ ደም ለተዋጁት ነፍሳት ደህንነት ስትሰሩ መለኮታዊው የመንፈስ ቅዱስ ኃይል በነፍሶቻችሁ ላይ ይሠራል፡፡ ለክርስቶስ ነፍሳትን በማምጣት የተሳካልን መሆን የምንችለው ልብን የመለወጥና የማሳመን ሥራን እንዲሠራ በእግዚአብሔር ፀጋና ኃይል ስንደገፍ ነው፡፡ እናንተ የእግዚአብሔርን እውቀት ስታቀርቡላቸው አለማመንና ጥርጣሬ አእምሮን ለመቆጣጠር ጥረት ያደርጋሉ፡፡ ነገር ግን የእግዚአብሔር የቃል ኪዳኑ ቃል ጥርጣሬያችሁን ከልባችሁ ያስወግደው፡፡ MYPAmh 130.3
እግዚአብሔርን በቃሉ ያዙትና በእምነት ሥሩ፡፡ የሰማያዊ አባታችሁን ቃል እንድትጠራጠሩ ለማድረግ ሰይጣን የተለያዩ ሐሳቦችን ይዞ ይመጣል፡፡ ነገር ግን «ከእምነት ያልሆነው ነገር ሁሉ ኃጢአት ነው፡፡» የሚለውን አስታውሱ፡፡ በሰይጣን የጨለማ ጥላ ውስጥ በእምነት ወደፊት እየተጓዛችሁ ጥርጣሬአችሁን በስርየት መቀመጫው ላይ አኑሩት፤ አንድ ጥርጣሬ እንኳን እንዲገባ አትፍቀዱ፡፡ ይህ ልምድን ለማግኘትና ለሰላማችሁና ለመታመናችሁ አስፈላጊ የሆነ ማረጋገጫ ለማግኘት ብቸኛው መንገድ ነው፡፡ MYPAmh 130.4
ልምምዳችሁ እያደገ በመጣ ቁጥር ከክርስቶስ ጋር የዓላማ አንድነት ስለሚኖራችሁ የነፍስ ግለትና እግዚአብሔርን የማገልገል የጋለ ፍቅር ይኖራችኋል፡፡ ርህራሄአችሁ ከመንፈስ ቅዱስ የተገኘ ይሆናል፡፡ የክርስቶስን ቀንበር ትሸከሙና ከእርሱ ጋር ሠራተኞች ትሆናላችሁ፡፡ The Youth’s Instructor , August 9, 1894. MYPAmh 130.5